Go to full page →

የመዝናናት ዋጋ MYPAmh 236

ክርስቲያኖች በሕይወት ካሉ ሰዎች መካከል እጅግ ደስተኛ መሆን አለባቸው። እግዚአብሔር አባታቸው ዘላለማዊ ወዳጃቸው ስለመሆኑ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይችላል። MYPAmh 236.1

ነገር ግን ብዙ ክርስቲያን ነን ባዮች የክርስትና ሃይማኖትን በሰዎች ፊት በትክክል አይወክሉም። ከዳመና ሥር ያሉ ይመስል ሐዘንተኞች ናቸው። ብዙ ጊዜ ክርስቲያን ለመሆን ስለ ከፈሉአቸው ታላላቅ መስዋዕትነቶች ያወራሉ። ኢየሱስን ላልተቀበሉ ሰዎች በምሳሌነታቸውና በንግግራቸው ሕይወትን የሚያስደስትና በፍስሐ የተሞላ የሚያደርጉ ነገሮችን በሙሉ እንዲተው ይማፀኑኣቸዋል። በተባረከው የክርስቲያን ተስፋ ላይ የጨለማ ከፈን ይሸፍናሉ። ከዚህም የተነሣ ድርጊታቸው ለሌሎች የሚያሳየው የእግዚአብሔር ህግጋት ለሚታዘዙአቸው ሰዎች እንኳን ሸክም እንደሆኑና ማንኛውም ደስታ የሚሰጥ ነገር ወይም ለስሜታችን ደስታ የሚያመጣ ነገር ሁሉ መስዋዕት መደረግ እንዳለበት ነው። MYPAmh 236.2

እግዚአብሔርን ፍቅር ነው የሚለው እውነተኛው ዓርፍተ ነገር በእነዚህ ክርስቲያን ነን ባዮች ሕይወት እንደሌለ ለመናገር አናመነታም። ማንም በእግዚአብሔር የሚኖር በፍቅር ይኖራል። ገርና ርህሩህ ከሆነው ሰማያዊ አባታችን ፍቅር ጋር በርግጠኝነት ተግባራዊ በሆነ እውቀት የተዋወቁ ሁሉ የትም ቢሆኑ ብርሃንንና ደስታን ለሌሎች ያጋራሉ። ከእግዚአብሔርና ከሰማይ ጋር የተገናኙ በመሆናቸው የእነርሱ መገኘትና ተፅእኖ ለጓደኞቻቸው እንደ መልካም የአበባ ሽታ ይሆናል! የሰማይ ንፅህናና የከበረው ውበት በእነርሱ አማካኝነት በተፅእኖኣቸው ሥር ለሚሆኑ ሁሉ ይደርሳል። ይህም እነርሱን የዓለም ብርሃንና የምድር ጨው እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። እነርሱ በርግጥም የሞት ሽታ ለሞት ሳይሆኑ የሕይወት ሽታ ለሕይወት ናቸው። MYPAmh 236.3