Go to full page →

ለወጣቶች አደገኛ መደሰቻዎች MYPAmh 241

ቀስቃሽና አስደሳች ለሆኑ መዝናኛዎች ያለ ፍላጎት ለእግዚአብሔር ሕዝብ በተለይም ለወጣቶች ፈተናና ወጥመድ ነው፡፡ ወደፊት ሊሆኑ ላሉ ክስተቶች እንዳይዘጋጁ አእምሮዎችን ለመሳብ ሰይጣን ያለ ማቋረጥ ማታለያዎችን እያዘጋጀ ነው፡፡ ያልተጠነቀቁ ሰዎች ከዓለም ደስታዎች ጋር አንድነት እንዲፈጥሩ ለማታለል በዓለማውያን ወኪሎች አማካይነት ቀጣይነት ያላቸውን ጊዜያዊ መደሰቻዎች ያዘጋጃል፡፡ ወደ ዓለም ፍቅር ለመምራት የተሰሉ ፍልሞች፣ የሚሰጡ ትምህርቶችና ማብቂያ የሌላቸው የተለያዩ ዓይነት መዝናኛዎች አሉ፡፡ በዚህ ከዓለም ጋር በሚፈጠር አንድነት ምክንያት እምነት ይደክማል፡፡ MYPAmh 241.1

ሰይጣን የማይደክም ሠራተኛ፣ ብልህና አደገኛ ጠላት ነው፡፡ ለመሸንገልም ሆነ ወጣቶች አንዳንድ ኃጢአቶችን በአነስተኛ ጥላቻ እንዲመለከቱ ለማድረግ ጥንቃቄ የጎደለው ንግግር በሚነገርበት ጊዜ ሁሉ ያንን አጋጣሚ በመጠቀም ሥር ሰዶ ብዙ ፍሬ እንዲያፈራ ክፉ ዘርን ይዘራና ያሳድጋል፡፡ ቃሉ በሚገልጸው በማንኛውም መልክ ቢሆን እርሱ አሳችና የሰለጠና(የተዋጠለት) አስመተኛ ነው፡፡ ወጣቶችንና ያልተጠነቀቁትን ለማጥመድ በብልሃት የተዘጋጁ ግን ሰላማዊ የሚመስሉና በጥበብ የተጠለፉ ብዙ መረቦች አሉት፡፡ የተፈጥሮ አእምሮ ወደ ደስታና ራስን ወደማስደሰት ያዘነብላል፡፡ የነፍስ ሁኔታ እንዴት ነው የሚለውን ጥያቄ ለማንሳት ጊዜ እንዳይኖር ለማድረግ አእምሮን በዓለማዊ መደሰቻዎች ፍላጎት መሙላት የሰይጣን መርህ ነው፡፡ MYPAmh 241.2