Go to full page →

ከወጣቶች ፊት ያለ የተለየ የፈተና ጊዜ MYPAmh 242

ለዓለም ተፅዕኖ የተሸነፉ ወጣት ሰንበት ጠባቂዎች ይፈተናሉ! ማንነታቸውም ተለይቶ ይታወቃል። የመጨረሻ ጊዜ አደጋዎች በላያችን ናቸው! ወጣቶች ከዚህ በፊት አስበውት የማያውቁት ፈተና ከፊት ለፊታቸው እየጠበቃቸው ነው። ተስፋ አስቆራጭ ወደሆኑና ግራ ወደሚያጋቡ ሁኔታዎች ውስጥ ስለሚገቡ የእምነታቸው ትከክለኛነት ይፈተናል። የሰውን ልጅ መገለጥ እንጠብቃለን ይላሉ፣ ነገር ግን አንዳንዶቻቸው የማያምኑ ሰዎች አሳዛኝ ምሳሌዎች ናቸው። ዓለምን ለመተው ፈቃደኞች አልነበሩም፣ ነገር ግን ደስታን ለመፈለግ፣ ሽርሽሮችንና ሌሎች ማህበራዊ ስብሰባዎችን በመሳተፍ ከዓለም ጋር አንድነት ፈጥረዋል። ይህንን ሲያደርጉም ክፋት በሌለበት መደሰቻ የተሳተፉ እንደሆነ በመናገር ራሳቸውን ያታልላሉ። ሆኖም እንደዚህ ዓይነት ነገሮች ከእግዚአብሔር ይለዩአቸውና የዓለም ልጆች ያደርጉአቸዋል። MYPAmh 242.2

አንዳንዶች ያለ ማቋረጥ በዓለም ላይ እየተደገፉ ናቸው። አመለካከታቸውና ፍላጎቶቻቸው ራሳቸውን ከካዱ የክርስቶስ ተከታዮች ጋር ከሚጣጣሙ ይልቅ ከዓለም መንፈስ ጋር የተጣጣሙ ናቸው። መንፈሳቸው ከመንፈሶቻቸው ከሚጣጣሙ ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር መምረጥ ፍፁም ተፈጥሮአዊ ነው። እንደ እነዚህ አይነቶች በእግዚአብሔር ህዝቦች መካከል እጅግ ብዙ ተፅዕኖ ያሳድራሉ። ከእነርሱ ጋር ይሳተፋሉ፣ በእነርሱ መካከልም ስም አላቸው። ነገር ግን እነዚህ ለማያምኑና በቤተክርስቲያን ውስጥ ላሉ ደካሞችና ላልተቀደሱ የሚጠቀሱ ጥቅሶች ናቸው። በዚህ የብጠራ ጊዜ እነዚህ ክርስቲያን ነን ባዮች አቋማቸውን ይለያሉ፡፡ ያውም ለእውነት በመታዘዝ ሙሉ በሙሉ ይለወጡና ይቀደሳሉ፣ ወይም ከዓለማዊያን ጋር ዋጋቸውን ለማግኘት ከዓለም ጋር ይቀራሉ። MYPAmh 242.3

እግዚአብሔር ደስታ ፈላጊን እንደ እርሱ ተከታይ አይቆጥረውም። የክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች የሚባሉት ራሳቸውን የካዱ፣ ራስን የማዋረድን፣ የቅድስናንና የንፅህናን ሕይወት የሚኖሩ ናቸው:: እንደ እነዚህ አይነቶቹን የዓለም ወዳጅ የሚናገራቸው ከንቱና ባዶ ንግግሮች አያስደስቷቸውም። MYPAmh 242.4