Go to full page →

ክርስቲያናዊ የደስታ ምንጮች MYPAmh 252

እግዚአብሔር ድሆችም ሆኑ ሃብታሞች በተመሳሳይ ሁኔታ ሊደሰቱበት የሚችሉትን ዓይነት ደስታ ሰጥቷል። እርሱም የአስተሳሰብ ንፅህናንና ራስ ወዳድነት የሌለውን ሥራ በማጎልበት የሚገኝ ደስታ ነው፣ የርህራሄ ቃላትን በመናገርና የደግነት ሥራዎችን በመሥራት የሚገኝ ደስታ ነው። እንደዚህ ዓይነት አገልግሎት ከሚሰጡ ሰዎች ውስጥ በብዙ ሃዘን የጨለሙ ሕይወቶችን ሊያበራ የሚችል የክርስቶስ ብርሃን ይበራል። Testimonies for the Church, Vol. 9, P. 57. MYPAmh 252.6