Go to full page →

በእግዚአብሔር ምህረት መከበብ MYPAmh 261

ሁልጊዜ የእግዚአብሔር ምህረት ይከባችኋል። በየቀኑ በረከቶቻችሁ እንዴትና መቼ እንደሚመጡ ማሰብ ትርፋማ ተግባር ነው። ውድ የሆኑ የእግዚአብሔር በረከቶች በውስጣችሁ አመስጋኝነትን ያነሳሱ። የእግዚአብሔር በረከቶች እንደ ዝናብ ነጠብጣቦች ብዙ ከመሆናቸው የተነሣ ለእናንተ የተደረገላችሁን የማያቋርጥ የአምላክን የፍቅር በጎነት መቁጠር አትችሉም። የምህረት ደመናዎች በእናንተ ላይ ለመውረድ እያንዣበቡ ናቸው። የደህንነትን ውድ ስጦታዎች የምታደንቁ ከሆናችሁ በየእለቱ የሚመጣላችሁ የኢየሱስ የጥበቃና የፍቅር መታደስ ይሰማችኋል። በሰላም መንገድ ትመራላችሁ። MYPAmh 261.3

በተፈጥሮ ውስጥ ያሉትን በግርማ የተሞሉ ነገሮችን ተመልከቱና እነዚህን ነገሮች ለሰጠው አምላክ ልባችሁ አመስጋኝ ይሁን። በተፈጥሮ መጽሐፍ ውስጥ ለአእምሮ ጠቃሚ የሆነ ጥናት አለ። ምሥጋና የለሽና ግድየለሽ አትሁኑ። የማስተዋል ዓይኖቻችሁን ክፈቱ! በተፈጥሮ ውስጥ ባሉ የእግዚአብሔር ህግጋት መካከል ያለውን ውብ መስማማት ተመልከቱና የሰማይና የምድር የበላይ ገዥ በሆነው ፈጣሪያችሁ ፊት በመደነቅና በአክብሮት ቅረቡ። በእምነት ዓይናችሁ በፍቅር ወደ እናንተ ጎንበስ በማለት በርህራሄ “ልጆቼ ሆይ ልባችሁን ስጡኝ” ሲል ተመልከቱት። ራሳችሁን ለኢየሱስ አሳልፋችሁ ስጡና አመስጋኝ በሆኑ ልቦች “የሚያድነኝ ሕያው እንደሆነ አውቃለሁ::” ማለት ትችላላችሁ። MYPAmh 261.4

በዚህ ሕይወት የሚኖራችሁ ደስታ፣ ሰላምና ስኬት ሁሉ የሚደገፈው በእግዚአብሔር በሚኖራችሁ እውነተኛና መታመን ባለበት እምነት ነው። ይህ እምነት ለእግዚአብሔር ትእዛዛት እውነተኛ መታዘዝን ያስከትላል። ስለ እግዚአብሔር ያላችሁ እውቀትና በእርሱ ላይ ያላችሁ እምነት ከእያንዳንዱ ክፉ ልምምድ የሚጠብቃችሁና መልካም ነገሮችን ሁሉ እንድታደርጉ የሚያነሳሳችሁ ነገር ነው። MYPAmh 261.5

ኢየሱስ ኃጢአቶቻችሁን ይቅር እንደሚልና ሊያዘጋጅላችሁ በሄደው ቤት በመኖር እንድትደሰቱ የሚፈልግ እንደሆነ እመኑ። በፊቱ እንድትኖሩ፣ የዘላለም ሕይወትና የክብር ዘውድ እንድታገኙ ይፈልጋል። The Youth’s Instructor, January 5,1887. MYPAmh 261.6