Go to full page →

የጥንካሬ መለኪያ MYPAmh 262

የባሕርይ ጥንካሬ ሁለት ነገሮችን ያጠቃልላል፦ የፈቃድ ኃይልንና ራስን የመቆጣጠር ኃይልን። ብዙ ወጣቶች ጠንካራና ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ፍላጎትን ከባሕርይ ጥንካሬ ጋር ያምታቱታል። እውነታው ግን ለፍላጎቱ የተሸነፈ ሰው ደካማ ሰው ነው። የአንድ ሰው እውነተኛ ጥንካሬና ክቡርነት የሚለካው በሚያሸንፉት ፍላጎቶች ኃይል ሳይሆን እርሱ ፍላጎቶቹን ለማሸነፍ ባለው ኃይል ነው። ከሰው ሁሉ የበለጠ ጠንካራ ሰው የሚባለው መበደሉን ቢያውቅም ስሜቱን መቆጣጠርና ጠላቶቹን ይቅር ማለት የሚችል ሰው ነው። MYPAmh 262.4

እግዚአብሔር የእውቀትና የግብረ ገብ ኃይልን ሰጥቶናል። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው በከፍተኛ ደረጃ የራሱ ባሕርይ አርክቴክት (ንድፍ ሰሪ) ነው። በየቀኑ የንድፍ ስራው ወደ መጠናቀቅ እየቀረበ ይሄዳል። የእግዚአብሔር ቃል ህንፃውን እንዴት መገንባት እንዳለብንና ህንፃችን በዘላለማዊ አለት ላይ መመስረቱን እንድናይ ያስጠነቅቀናል:: ስራችን እንዳለ በግልፅ የሚቆምበት ጊዜ እየመጣ ነው። ሁሉም ሰዎች እዚህም ሆነ ከዚህ በኋላ በሚመጣው ህይወት የሚጠቅሙ ባሕርያትን ለመመስረት እግዚአብሔር የሰጣቸውን ኃይሎች ማሳደግ ያለባቸው ጊዜ አሁን ነው። MYPAmh 262.5

ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝ መቀበል (ማመን) የባሕርይ ጥንካሬንና ፅናትን ይሰጣል። በኢየሱስ ላይ እውነተኛ እምነት ያላቸው ሰዎች የተረጋጋ አእምሮ ያላቸው፣ የእግዚአብሔር ዓይኖች እንደሚመለከቱአቸው የሚያስተውሉ፣ የሰዎች ሁሉ ፈራጅ የሞራል ብቃትን •የመዘነ መሆኑንና እየመሰረቱ ያሉት ባሕርይ ምን አይነት እንደሆነ የሰማይ ኃይላት እየተመለከቱ መሆናቸውን የሚገነዘቡ ይሆናሉ። MYPAmh 262.6

ወጣቶቻችን አሰቃቂ የሆኑ ስህተቶችን የሚፈፅሙበት ምክንያት ከእነርሱ የበለጠ እድሜ ካላቸው ሰዎች ልምድ ለመማር ፈቃደኛ ካለመሆናቸው የተነሳ ነው። ተማሪዎች የወላጆቻቸውንና የመምህራኖቻቸውን ማስጠንቀቂያዎችንና መመሪያዎችን በማሾፍና በማንቋሸሽ ማሳለፍ የሚያስከፍላቸው ዋጋ ታላቅ ነው። ማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ከሚሰጠው የበለጠ ጥልቅ ትምህርት እንደሚያስፈልጋቸው እየተገነዘቡ እያሉ በወላጆቻቸውና በመምህራን የሚሰጣቸውን እያንዳንዱን ትምህርት በልባቸው መያዝ አለባቸው። ክርስቶስ በእምነት በልብ ውስጥ በሚያድርበት ጊዜ የእርሱ መንፈስ ነፍስን የሚያነፃና ሕይወት የሚሰጥ ኃይል ይሆናል። በልብ ውስጥ ያለ እውነት በህይወት ላይ የማስከተል ተፅዕኖን ሳያሳርፍ አይቀርም…። MYPAmh 263.1

ከቤታቸው ርቀው ያሉና በወላጆቻቸው ቀጥተኛ ተፅእኖ ስር ያልሆኑ ወጣቶች የሰማያዊ አባታቸው ዓይኖች እነርሱን እየተመለከቱ እንዳሉ ያስታውሱ። እርሱ ወጣቶችን ይወዳል። የሚያስፈልጋቸውን ነገር ያውቃል! ፈተናዎቻቸውንም ይረዳላቸዋል። እነርሱ ፍላጎቶቻቸውን የሚገነዘቡ ከሆኑና ለእርዳታ እርሱን ከፈለጉት በእነርሱ ውስጥ ሊፈጽሙ የሚችሉአቸውን ታላላቅ ነገሮች በማየት ወደ ከፍተኛ ደረጃ መድረስ እንዲችሉ ሊረዳቸው ዝግጁ ነው። MYPAmh 263.2

ተማሪዎች ሆይ፣ ወላጆቻችሁ ስለ እናንተ ቀንና ማታ የሚፀልዩአቸው ፀሎቶች ወደ እግዚአብሔር እየወጡ ናቸው። በየቀኑ የፍቅር ፍላጎቶቻቸው ይከተሉአችኋል። ተማፅኖአቸውንና ማስጠንቀቂያዎቻቸውን ስሙና እናንተ ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ በማድረግ ዙሪያችሁን ከቦ ካለው ክፋት በላይ ለመሆን ራሳችሁን ገጣሚዎች አድርጉ። ጠላት አእምሮአችሁንና ባሕርያችሁን ለማበላሸትና በእናንተ ውስጥ ትክክለኛ ያልሆኑ መርሆዎችን ለማሳደግ ምን ያህል በስውር እየሰራ እንደሆነ እናንተ አታዩም። MYPAmh 263.3

ከንቱነትንና ደስታ ፍለጋን ለመከተል የወሰዳችሁት የመጀመሪያ እርምጃ ይህን ያህልም አደጋ ያለው አይመስላችሁም! መልካም ማድረግ ስትፈልጉ ያለ አንዳች ችግር መጀመሪያ ስህተትን ለመፈፀም እንዳደረጋችሁት ሁሉ በቀላሉ አቅጣጫችሁን መቀየር የምትችሉ እንደሆነ ታስባላችሁ:: ነገር ግን ይህ ስህተት ነው። ብዙዎች በመረጡአቸው ክፉ ጓደኞቻቸው አማካኝነት ከመልካም መንገድ ደረጃ በደረጃ በመውረድ ከዚህ በፊት በፍፁም አሁን ወደ አሉበት ጥልቀት መስመጥ እንደማይችሉ ወደሚያስቡት አለ መታዘዝና የግብረ ገብ ውድቀት ጥልቅ ወርደዋል። MYPAmh 263.4

በፈተና የሚሸነፍ ወጣት ለመልካም ያለውን ተፅእኖ ያዳክማል፣ በስህተት ድርጊቱ ለነፍሳት ጠላት ለሆነው ሰይጣን መሳሪያ የሚሆን ሰው በሌሎች መንገድ ላይ የማሰናከያ አለት ላስቀመጠበቱ ድርጊት ለጌታ ምላሽ ይሰጣል። ተማሪዎች ለምን እራሳቸውን ከታላቁ ከሃዲ ጋር ያገናኛሉ? ለምን ሌሎችን ለመፈተን የእርሱ መሳሪያ ይሆናሉ? ከዚህ ይልቅ መሰሎቻቸውንና መምህራኖቻቸውን ለመርዳት ለምን ጥረት አያደርጉም? ለመምህራን ተማሪዎቻቸው ሸክምን እንዲሸከሙና ሰይጣን እጅግ ተስፋ አስቆራጭና ፈታኝ አድርጎ የሚያመጣቸውን ግራ የሚያጋቡ ነገሮች እንዲጋፈጡ መርዳት መልካም እድል ነው። MYPAmh 263.5

ጠቃሚ የሆነና በደስታ የተሞላ ሁኔታን መፍጠር ይችላሉ። እያንዳንዱ ተማሪ ለስነስርዓት፣ ለትጋትና ለታዛዥነት አክብሮት ማሳየቱንና ለመልካምና ነፍስን ከፍ ለሚያደርግ ነገር ሁሉ ጠላት ለሆነው ከችሎታው ወይም ከተፅእኖው አንዲት ነጥብ እንኳን ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑን መረዳቱ ያስደስተዋል። MYPAmh 263.6

ለእውነት ልባዊ አክብሮት ያለውና ለኃላፊነቱ ትክክለኛ ግንዛቤ ያለው ተማሪ መሰሎቹ ክርስቶስን እንዲቀበሉ በከፍተኛ ደረጃ ተፅእኖ ማሳደር ይችላል። ከክርስቶስ ጋር የተጠመዱ ወጣቶች ከቁጥጥር ውጪ የሆኑ አይሆኑም! የራሳቸውን የራስ ወዳድነት ደስታ የማርካት መንገድን አይከተሉም። በመንፈስ ከክርስቶስ ጋር አንድ ስለሆኑ በተግባራቸውም ከእርሱ ጋር አንድ ይሆናሉ። በትምህርት ቤቶቻችን ያሉ በእድሜ ጠና ያሉ ተማሪዎች ከእነርሱ በእድሜ የሚያንሱትን ተማሪዎች ባሕርይና ተግባር የመቅረፅ አቅም እንዳላቸው ያስታውሱ:: ስለዚህ ያላቸውን እያንዳንዱን መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ያድርጉ:: እንግዲህ እነዚህ ወጣቶች በመጥፎ ተፅዕኖአቸው ምክንያት ጓደኞቻቸውን በጠላት እጅ አሳልፈው እንዳይሰጡ የግል ውሳኔ ያድርጉ። MYPAmh 263.7

ኢየሱስ በእርሱ የሚታመኑትን ሁሉ ይረዳል። ከእርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው በሙሉ ደስታ በእጃቸው ነው። ለእርሱ በማለት ሥጋን ከምኞቱና መሻቱ ጋር በመስቀል አዳኛቸው የሚመራቸውን መንገድ ይከተላሉ። ተስፋቸውን በክርስቶስ ላይ ስለ መሰረቱ ምድራዊ ማዕበሎች ከእውነተኛው መሰረት ላይ ጠራርገው ሊወስዱአቸው ኃይል አይኖራቸውም፡፡ MYPAmh 264.1