Go to full page →

የእኛ ሃላፊነት MYPAmh 265

ይህ ሃላፊነት ራሳችንን ነፃ ማድረግ የማንችልበት ሃላፊነት ነው። ቃላቶቻችን፣ ተግባሮቻችን፣ አለባበሳችን፣ ባሕርያችን፣ እንዲሁም የፊታችን ገፅታ በሌሎች ላይ ተጽእኖ ያሳድራል። እስካሁን በተገለፀው ሀሳብ ላይ ማንም ሰው ሊለካው የማይችል ለክፉ ወይም ለመልካም ውጤት የሚያበቃ ሁኔታ ተንጠልጥሎበታል። እያንዳንዱ ለሌሎች ያጋራነው ስሜት በመጨረሻ መከርን የሚያስከትል ዘር ነው። መዳረሻውን የማናውቀው በሰብዓዊ ዘር የክስተት ሰንሰለት ውስጥ ያለ መገናኛ ነው። በእኛ ምሳሌነት ሌሎች መልካም መርሆዎችን እንዲያሳድጉ ብንረዳቸው መልካም እንዲያደርጉ ኃይል እንሰጣቸዋለን። እነርሱም በተራቸው በሌሎች ላይ ተመሳሳይ ተጽእኖ ያሳድሩና ግንኙነቱ እየቀጠለ ይሄዳል። በመሆኑም እኛ አስበን ባላደረግነው ተጽእኖ በሺዎች የሚቆጠሩ ይባረካሉ። MYPAmh 265.3

በባህሩ ላይ ጠጠርን ስትወረውሩ ማዕበል ይፈጠራል። ማዕበሉ በጨመረ ቁጥር እስከ ባህሩ ዳር እስኪደርስ ድረስ እየሰፋ ይሄዳል። ተጽእኖአችንም የሚሰፋው እንደዚህ ነው ። ከእኛ እውቀትና ቁጥጥር ውጭ ለሌሎች በረከት ወይም እርግማን ሲሆን እናያለን። MYPAmh 265.4

ባሕርይ ኃይል ነው። እውነተኛ፣ ራስ ወዳድነት የሌለው፣ እግዚአብሔርን የሚመስል ህይወት ፀጥ ያለ ምስክርነት ማንም ሊቋቋመው የማይችል ተጽዕኖ አለው። በሕይወታችን የክርስቶስን ባሕርይ በመግለጥ ነፍሳትን በማዳን ሥራ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን:: ከእርሱ ጋር መተባበር የምንችለው በሕይወታችን የእርሱን ባሕርይ በመግለጥ ብቻ ነው። MYPAmh 265.5

የተጽእኖ ክበባችን በሰፋ ቁጥር የተሻለ እንሰራለን። እግዚአብሔርን እናገለግላለን የሚሉ የህግን መርሆዎች በዕለታዊ ሕይወታቸው በመለማመድ የክርስቶስን ምሳሌ ሲከተሉ እያንዳንዱ ተግባራቸው ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን እንደሚወዱና ባልንጀራቸውን ደግሞ እንደ ራሳቸው እንደሚወዱ ሲገልጥ ያኔ ቤተክርስቲያን ዓለምን ለማንቀሳቀስ ኃይል ይኖራታል።—Christ’s Object Lessons, 339, 340 MYPAmh 265.6