Go to full page →

ወርቃማው ህግ MYPAmh 267

ከሌሎች ጋር በሚኖራችሁ ግንኙነት ራሳችሁን በእነርሱ ቦታ አስቀምጡ። ስሜቶቻቸውን፣ ችግራቸውን፣ ተስፋ መቁረጣቸውን፣ ደስታቸውንና ሀዘናቸውን ተካፈሉ። ራሳችሁን እንደ እነርሱ አድርጋችሁ እናንተ በእነርሱ ቦታ ብትሆኑ ኖሮ እነርሱ እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር ለእነርሱም አድርጉላቸው። ይህ እውነተኛው የታማኝነት ህግ ነው። ይህ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ::” የሚለው ሌላኛው የህግ መግለጫ ነው። እንደዚሁም የነቢያት ትምህርት አንኳር ነው። የሰማይ መርህ ስለሆነ በእርሱ ቅዱስ ጓደኝነት ገጣሚዎች በሆኑ ሰዎች ሁሉ ውስጥ ያድጋል። MYPAmh 267.1

ወርቃማው ህግ የእውነተኛ ገርነት መርህ ስለሆነ እውነተኛው መግለጫ የታየው በኢየሱስ ባሕርይ ነው። በአዳኛችን ዕለታዊ ሕይወት የተንፀባረቀው ምንኛ ልስላሴና ውበት ነበር! ከፊቱ ይፈልቅ የነበረው ምንኛ ግሩም ጣፋጭነት ነበር! ተመሳሳይ መንፈስ በልጆቹ ይገለጣል። ክርስቶስ አብሮአቸው የሚኖር ሁሉ በመለኮታዊ ከባቢ አየር ይከበባሉ። የንፅህናቸው ነጭ ልብስ ከጌታ አትክልት ቦታ በሚገኝ ሽቶ መልካም መዓዛ ይሰጣል። ፊታቸው ከእርሱ ፊት ብርሃንን በማንፀባረቅ ለሚደናቀፉና ለደከሙ እግሮች መንገዳቸውን ያበራላቸዋል። MYPAmh 267.2

ፍፁም ባሕርይ በውስጡ ምንን እንደሚይዝ ትክክለኛ ግንዛቤ ያለው ማንኛውም ሰው ቢሆን የክርስቶስን ርህራሄና ገርነት ማንፀባረቅ አያቅተውም። የፀጋ ተጽእኖ ልብን ማለስለስ፣ ከሰማይ የሆነውን ውበትና የትክክለኛነት ስሜት በመፍጠር ስሜቶችን መሞረድና ማንፃት ነው።— Thoughts From the Mount of Blessing, 134, 135. MYPAmh 267.3