Go to full page →

የጦርነቱ ባሕርይ MYPAmh 42

የሰው ፈቃድ ለውጥ ፈላጊ በመሆኑ ሁሉንም ነገሮች ወደ ዓላማው ለማዘንበል ያለማቋረጥ እየጣረ ነው፡፡ ይህ ጥረቱ በእግዚአብሔርና ትክክል በሆነው ወገን ከተደረገ በሕይወት ውስጥ የመንፈስ ፍሬዎች ይታያሉ፡፡ እግዚአብሔር መልካም ለሚሰሩ «ግርማ፣ ክብርና ሰላም” ወስኖላቸዋል፡፡ MYPAmh 42.1

ፈቃድን ሰይጣን እንዲቀርፀው ከተፈቀደለት የራሱን ፈቃድ ለመፈፀም ይጠቀማል፡፡ ያለማመን መላምቶችን በማምጣት ሰብዓዊ ልቦች የእግዚአብሔርን ቃል እንዲዋጉ ያነሳሳል፡፡ በማያቋርጥና ከባድ ጥረት ሰዎች እሱ ራሱ ለእግዚአብሔር ያለውን የጥላቻና የተቃርኖ ኃይሎች እንዲጋሩ ይፈልጋል፡፡ በዚህም በሰማይ ተቋማት መስፈርቶች ላይና በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ላይ በመቃወም እንዲሰለፉ ያደርጋቸዋል፡፡ በሥሩ ክፉ ወኪሎችን በሙሉ በማሰለፍ በእርሱ ጄኔራልነት ክፉ በመልካም ላይ ጦርነት እንዲከፍት ወደ ጦር ሜዳው ያመጣቸዋል፡፡ MYPAmh 42.2