Go to full page →

ያለመታዘዝ ውጤቶች MYPAmh 279

ልብ ለሰብዓዊ ፍቅር ይጓጓል። ነገር ግን ይህ ፍቅር የክርስቶስን ፍቅር ቦታ ሊተካ እስከሚችል ድረስ ብርቱ፣ ንፁህ ወይም ክቡር አይደለም። ሚስት የህይወትን ተግባሮች፣ ሃላፊነቶችና ጭንቀቶች ለመጋጠም የሚያስችላት ጥበብ፣ ብርታትና ፀጋ ማግኘት የምትችለው ከአዳኝዋ ብቻ ነው። እርሱን ብርታትዋና መሪዋ ማድረግ አለባት። ሴት ራስዋን ለማንኛውም ምድራዊ ጓደኛ ከመስጠትዋ በፊት ለክርስቶስ ትሰጥ። ይህንን ከሚቃረን ከማንኛውም ግንኙነት ትለይ። እውነተኛ ደስታ የሚያገኙ ሁሉ ባላቸው ንብረትና በሚያደርጉት ነገር ሁሉ ሰማያዊ በረከት መኖር አለበት። ብዙ ቤቶችንና ልቦችን በሐዘን የሚሞላው ለእግዚአብሔር አለመታዘዝ ነው። እህቴ ሆይ፣ ጨለማው የማይገፈፍ ቤት እንዲኖርሽ ካልፈለግሽ በስተቀር የእግዚአብሔር ጠላት ከሆነ ሰው ጋር አትጣመሪ። MYPAmh 279.4

ከእነዚህ ቃላት ጋር በፍርድ ቀን ለመገናኘት እንደሚጠብቅ ሰው ለመውሰድ እያሰላሰልሽ ባለው እርምጃ ላይ እንድታስቢበት እማፀንሻለሁ:: እራስሽን “የማያምን ባል ሃሳቤን ከኢየሱስ አያርቅብኝምን? ከክርስቶስ ይልቅ ደስታን ወዳጅ ነው። እርሱ የሚደሰትባቸውን ነገሮች እኔም እንድደሰትባቸው አይመራኝምን?» ብለሽ ጠይቂ። ወደ ዘላላማዊ ሕይወት የሚመራ መንገድ ጥልቅና ጠመዝማዛ ነው። ጉዞሽን የሚያጓትትብሽን ተጨማሪ ሸክም አትጨምሪ። MYPAmh 279.5

ጊዜ ሳያልፍብሽ ከፊትሽ ሰላለው አደጋ አስጠነቅቅሻለሁ። ለስላሳና አስደሳች ቃላትን አድምጠሽ ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል ብለሽ ለማመን ተመርተሽ ይሆናል። ነገር ግን እነዚህን ጥሩ ቃላትን ለመናገር የገፋፋውን ከኋላው ያለውን ግፊት ማንበብ አትችይም። ከክስተቱ በስተጀርባ ሰይጣን ለነፍስሽ ያጠመደውን ወጥመድ ማየት አትችይም። በቀላሉ ሊጥልሽ እንዲችል የዚህን ዓይነት እርምጃ እንድትወስጂ ይመራሻል። ትንሽ እድል እንኳን አትስጭው:: እግዚአብሔር በባሪያዎቹ አእምሮ ሲንቀሳቀስ ሰይጣን ደግሞ በአመፃ ልጆች አማካኝነት ይሰራል። በክርስቶስና በሰይጣን /በብልያል/ መካከል አንድነት የለም። ሁለቱም አይጣጣሙም:: ከማያምን ሰው ጋር ራስሽን ማጣመር ራስሽን ለሰይጣን ማስገዛት ነው። የእግዚአብሔርን መንፈስ አሳዝነሽ ጥበቃው እንዲወገድብሽ ታደርጊያለሽ። MYPAmh 280.1