Go to full page →

የጤናንና የጨዋነትን ህግ መጣስ MYPAmh 289

አብዛኛውን የሌሊት ጊዜያቶች አብረው ለማውራት የሚሰው ሰዎችን የሰይጣን መላእክት በጥንቃቄ ይመለከቱአቸዋል። ዓይኖቻቸው ተከፍተው ቢሆን ኖሮ የእግዚአብሔር መልአክት ቃላቶቻቸውንና ተግባራቸውን ሲመዘግቡ ያዩ ነበር። የጤናና የጨዋነት ህግ ተጥሶአል:: ከጋብቻ በፊት ባለው ጊዜ የሚደረጉ ግንኙነቶች ከጋብቻ በኋላ ላለው ጊዜ ቢቆዩ ጥሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ጋብቻ በአጠቃላይ ከጋብቻ በፊት የነበረውን መስዋዕትነት ሁሉ ወደ ፍፃሜ ያመጣል። MYPAmh 289.5

በዚህ የህገ ወጥነት ዘመን እነዚህ በእኩለሌሊት የሚባክኑ ሰዓቶች ብዙ ጊዜ ሁለቱንም ግለሰቦች ወደ ጥፋት ይመራሉ። ወንዶችና ሴቶች ራሳቸውን ሲያዋርዱ እግዚአብሔር ይዋረድና ሰይጣን ከፍ ከፍ ይላል። በዚህ ዓይነት ልቅ ፍቅር ምክንያት የከበረ መልካም ስም መስዋት ይሆናል፣ ለእንደዚህ አይነት ጋብቻዎች እግዚአብሔር ለትክክለኛነታቸው ማረጋገጫ አይሰጥም። የተጋቡት ስሜት አንቀሳቅሶአቸው ስለሆነ የጋብቻ አዲስነት ሲያበቃ ያደረጉት ነገር ምን እንደሆነ ማስተዋል ይጀምራሉ። ቃለ-መሃላቸውን በፈፀሙ በስድስት ወራት ውስጥ ለእርስ በርስ ያላቸው አመለካከት ተለውጧል። እያንዳንዳቸው በጋብቻው ህይወት በቆዮባቸው ጊዜያቶች የትዳር ጓደኛቸውን ፀባይ አጥንተዋል። በጭፍን ግንኙነታቸው ጊዜ ያልተገነዘቧቸውን ስህተቶች በእርስ በርስ ላይ ያገኛሉ። በመሰዊያው ላይ የገቡአቸው መሃላዎች አያቆራኙአቸውም። በችኮላ በሚፈፀሙ ጋብቻዎች ምክንያት የእግዚአብሔር ህዝብ ነን በሚሉ ሰዎች መካከል በቤተክርስቲያን እንኳን መለያየት፣ መፋታትና ታላቅ ግራ መጋባት ይታያል። MYPAmh 290.1