Go to full page →

ፈተናን መቋቋም MYPAmh 59

የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች የሆኑ ለፈተና መንገድ አይከፍቱም፡፡ ክርስቲያናዊ ሕይወትን ለመኖር ጥረት የሚያደርጉትን ለማሸነፍ ጠላት ባለው ኃይሉ ሁሉ እየሰራ ነው፡፡ ለማሸነፍ ተስፋ በማድረግ ፈተናዎችን ይዞ ወደ እነርሱ ይመጣል፡፡ ስለሆነም ተስፋ ሊያስቆርጣቸው ተስፋ ያደርጋል፡፡ ነገር ግን እግሮቻቸውን በዘመናት አለት ላይ አጽንተው ያቆሙ በማታለያዎቹ አይሸነፉም፡፡ እግዚአብሔር አባታቸውና ኢየሱስ ረዳታቸው መሆኑን ያስታውሳሉ፡፡ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣው እርሱ እንዳሸነፈ ሁሉ ለእያንዳንዱ ለተፈተነ ነፍስ የማሸነፍ ብርታት ለማምጣት ነበር፡፡ የፈተናን ኃይል አውቃለሁ፣ በመንገድ ላይ ያሉትን አደጋዎችንም አውቃለሁ፤ ነገር ግን ፈተናን ለማሸነፍ እየታገሉ ላሉ ሁሉ ለእያንዳንዱ አስፈላጊ ጊዜ የሚሆን በቂ ብርታት እንደተሰጣቸውም አውቃለሁ፡፡ MYPAmh 59.1