Go to full page →

ወደ ፊትና ወደ ላይ MYPAmh 66

የክርስቲያን ሕይወትን ውበት ማሳየት በቻልኩ ብዬ እመኛለሁ፡፡ በሕይወት ማግስት በመጀመር፣ በተፈጥሮና በእግዚአብሔር ህግጋት ቁጥጥር ሥር በመሆን ክርስቲያን ያለማቋረጥ ወደ ፊትና ወደ ላይ ይጓዛል፡፡ በጉዞውም የሕይወት አክሊልና «ከሚሰጠው ሰው በቀር ማንም የማያውቀው ስም» MYPAmh 66.1

የተጸፈበት አዲስ ስም ወደሚጠብቀው ወደ ሰማያዊ ቤት በየዕለቱ እየቀረበ ይሄዳል፡፡ ያለማቋረጥ በደስታ፣ በቅድስናና በጠቃሚነቱ እያደገ ይሄዳል፡፡ የእያንዳንዱ ዓመት ለውጥ ካለፈው ዓመት ለውጥ ይበልጣል፡፡ MYPAmh 66.2

እግዚአብሔር ለወጣቶች የሚወጡበት መሰላል ሰጥቷቸዋል፤ ከምድር ወደ ሰማይ የሚደርስ መሰላል፡፡ ከመሰላሉ በላይ እግዚአብሔር አለ፡፡ በእያንዳንዱ የመሰላሉ ማገር ላይ የእግዚአብሔር ክብር ብሩህ ጮራዎች ያርፋሉ፡፡ በመሰላሉ ላይ እየወጡ ያሉት አያያዛቸው ሲላላና እርምጃቸው ሲደናቀፍ እርዳታን ለመላክ በንቃት እየተመለከታቸው ነው፡፡ አዎን ማንም በትዕግስት መሰላሉን የሚወጣ ወደ ሰማያዊ ከተማ የመግባት እድል እንደማያጣ ደስታ በተሞሉ ቃላት ተናገሩ፡፡ MYPAmh 66.3

ሰይጣን ለወጣቶች ብዙ ፈተናዎችን ያቀርባል፡፡ የእነርሱን ነፍስ ለማጥፋት የሕይወት ቁማር እየተጫወተ ስለሆነ እነርሱን ለማታለልና ለማጥፋት ሳይሞክረው የሚቀር ዘዴ አይኖረውም፡፡ ነገር ግን ያለ እርዳታ ብቻቸውን ፈታኝን እንዲዋጉ እግዚአብሔር አይተዋቸውም፡፡ ኃይል ሁሉ ያለው ረዳት አለላቸው፡፡ MYPAmh 66.4

በዚህ ዓለም ላይ በሰብዓዊ ተፈጥሮ ሰይጣንን ተጋፍጦ ያሸነፈውና የዛሬ ወጣቶችን የሚያገኛቸውን እያንዳንዱን ፈተና የተቋቋመው ጌታ ከጠላታቸው ይልቅ እጅግ ብርቱ ነው፡፡ እርሱ ታላቅ ወንድማቸው ነው፡፡ ለእነርሱ ጥልቅና በርህራሄ የተሞላ ስሜት አለው፡፡ ሁል ጊዜ ሊጠነቀቅላቸው ነቅቶ ይጠብቃል፤ እነርሱ ሊያስደስቱት ሲሞክሩም ደስ ይሰኛል፡፡ ሲፀልዩ ከፀሎቶቻቸው ጋር የጽድቁን እጣን በመደባለቅ ፀሎቶቻቸውን ለእግዚአብሔር ጥሩ መዓዛ እንዳለው መስዋዕት ያቀርባል፡፡ ወጣቶች በእርሱ ብርታት እንደ መልካም የመስቀል ወታደሮች ችግርን ይታገሳሉ፡፡ በእርሱ ኃይል በመበረታታት እግዚአብሔር ወደ ሚጠብቅባቸው ከፍ ያለ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡ በቀራኒዮ የተፈፀመው መስዋዕት MYPAmh 66.5