Go to full page →

ሕያው እምነት MYPAmh 75

የልብ ቅድስናንና የሕይወት ንፅህናን ከልባቸው የሚሹ ብዙዎች ግራ የተጋቡና ተስፋ የቆረጡ ይመስላል። ያለማቋረጥ ወደራሳቸው እየተመለከቱ እምነት በማጣታቸው ያላዝናሉ። እምነት ስለሌላቸውም የእግዚአብሔርን በረከት መጠየቅ እንደሚችሉ አይሰማቸውም። እነዚህ ግለሰቦች ስሜታቸውን እንደ እምነት ያዩታል። ከእውነተኛ እምነት ትህትና በላይ ስለሚመለከቱ በነፍሳቸው ላይ ታላቅ ጨለማ ያመጣሉ። በእግዚአብሔር ምህረትና በጎነት ላይ ለማረፍና ባርኮቶቹን በመቁጠር እርሱ ቃል ኪዳኑን እንደሚፈፅም ዝም ብለው እንዲያምኑ አእምሮን ከራስ መመለስ አለባቸው። MYPAmh 75.1

በራሳችን እምነት ሳይሆን በእግዚአብሔር ተስፋዎች መታመን አለብን። ላለፈው ህግ መተላለፋችን ንስሐ ስንገባና ወደፊት ለመታዘዝ ስንወስን እግዚአብሔር ስለ ክርስቶስ ይቅር እንደሚለንና እንደሚቀበለን ማመን አለብን። MYPAmh 75.2

አንዳንድ ጊዜ ጨለማና ተስፋ መቁረጥ በነፍሳችን ላይ በመምጣት ሊያሸንፉን ያስፈራሩናል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ ያለንን መታመናችንን መጣል የለብንም። ቢሰማንም ባይሰማንም ዓይናችንን በኢየሱስ ላይ ማተኮር አለብን። እያንዳንዱን የምናውቀውን ተግባር በታማኝነት ለመፈፀምና በፀጥታ በተስፋዎቹ ላይ ለማረፍ መሻት አለብን። MYPAmh 75.3