Go to full page →

ለኢየሱስ ምፃት መዘጋጀት MYPAmh 86

እግዚአብሔር ትዕቢትን፣ ትዕቢተኞችንና ክፉ የሚያደርጉትን ሁሉ እንደሚጠላቸውና እንደገለባ ሆነው የሚመጣውም ቀን እንደሚያቃጥላቸው አየሁ። የሦሥተኛውን መልአክ መልእክት እንደሚያምኑ በሚናገሩ በብዙ ልቦች ውስጥ እንደ እርሾ መሥራት እንዳለበትና ኩራታቸውን፣ ራስ ወዳድነታቸውን፣ መጥፎ ምኞታቸውንና የዓለም ፍቅርን ማጠብ እንዳለበት አየሁ። MYPAmh 86.2

ኢየሱስ እየመጣ ነው። ሲመጣ የሚያገኛቸው ሰዎች ከዓለም ጋር ስምምነት የፈጠሩ ሰዎች ይሆኑ ይሆን? ለራሱ እንዳነፃቸው ሕዝቡ አድርጎ ይቀበላቸው ይሆን? ኦ! በፍፁም አያደርገውም። እርሱ እንደ ራሱ ህዝብ አድርጎ እውቅና የሚሰጣቸው ለንፁሃንና ቅዱሳን ነው። በመከራ ውስጥ የነፁና የጠሩ ፣ራሳቸውንም ከዓለም የለዩና ያልጎደፉትን ብቻ እንደ ራሱ ህዝብ አድርጎ ይወስዳቸዋል። MYPAmh 86.3

ትሁትና ገር በሆነው በኢየሱስ ደቀ መዛሙርትና በማያምኑ መካከል በስም ካልሆነ በስተቀር ልዩነት እንደሌለና የእግዚአብሔር ህዝቦች ከዓለም ጋር ተስማምተው የመኖራቸውን አሰቃቂ እውነት በተመለከትኩ ጊዜ ነፍሴ ጥልቅ ሃዘን ተሰማት። ኢየሱስ ቆስሎና በግልፅ ተዋርዶ አየሁ። መልአኩም የፋሽኑ ተከታዮች የሆኑትን በሐዘኔታ እየተመለከታቸው እንዲህ አለ፡- “ተለዩ! ተለዩ! ያለበለዚያ እድላችሁን ከከተማዋ ውጪ ካሉ ግብዞችና ከማያምኑ ጋር ያደርጋል። የስም እምነታችሁ የሚያመጣላችሁ ነገር ቢኖር የበለጠ ሐዘን ነው፤ ፈቃዱን አውቃችሁ ስላልተገበራችሁት ቅጣታችሁ ከሌሎች የበለጠ ይሆናል።” MYPAmh 86.4

የሦስተኛውን መልአክ መልእክት እንደሚያምኑ የሚናገሩ ብዙ ጊዜ በቸልተኝነት፣ በፌዝና በቀልድ የእግዚአብሔርን ሥራ ይጎዱታል። ይህ ክፋት በሁሉም ደረጃ እንዳለ እንዳይ ተደርጌያለሁ። በጌታ ፊት ራስን ዝቅ ማድረግ እንዳለብን አይቻለሁ። የእግዚአብሔር የዘመኑ እስራኤል ልብሳቸውን ሳይሆን ልባቸውን መቅደድ አለባቸው። እንደ ህፃናት ያለ ራስን ዝቅ ማድረግ (የዋህነት) አይታይም፡፡ ከእግዚአብሔር አለመደሰት ይልቅ የሰዎች እውቅና የበለጠ ግምት ተሰጥቶታል፡፡ MYPAmh 86.5

መልአኩ እንዲህ አለ፡- «ጌታ በፍርድ እንዳይጎበኛችሁና የህይወት ተሰባሪ ክር እንዳይበጠስ፣ እናንተም ለፍርዱ ሳትዘጋጁ ያለ ጥበቃ መቃብር ውስጥ እንዳትጋደሙ ልባችሁን አስተካክሉ፡፡ በመቃብር ውስጥ አልጋችሁን ካላዘጋጃችሁ፣ ከእግዚአብሔር ጋር በፍጥነት ሰላም ካልፈጠራችሁና እራሳችሁን ከዓለም ካልለያችሁ ልባችሁ እየጠነከረ ይሄድና ጌታን ለመገናኘት መዘጋጀት በሚል በውሸት መደገፊያ ላይ ትደገፉና ፅኑ መሰረት ያለውን ተስፋ ለማግኘት ጊዜው ካለፈባችሁ በኋላ ስህተታችሁን ትገነዘባላችሁ፡፡ Testimonies for the Church Volume 1, p. 127 -134. MYPAmh 86.6