Go to full page →

የመጀመሪያ እርምጃዎች MYPAmh 88

የእግዚአብሔርን መንፈስ ጥልቅ አንቀሳቃሽነት መደሰት የእያንዳንዱ ክርስቲያን መልካም ዕድል ነው፡፡ ጣፋጭ ሰማያዊ ሰላም አእምሮአችሁን ይሞላውና በእግዚአብሔርና በሰማይ ለማሰላሰል ፍቅር ይኖራችኋል፡፡ በቃሉ የከበሩ ተስፋዎች ትደሰታላችሁ፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያ የክርስቲያን ጉዞ መጀመራችሁን እወቁ፡፡ በዘላለማዊ ሕይወት መንገድ ላይ የመጀመሪያዎቹ እርምጃዎች መኬዳቸውን እወቁ፡፡ አትታለሉ፡፡ ኃይማኖት ወይም እምነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ብዙዎቻችሁ ስለማታውቁ እፈራለሁ፡፡ የሆነ ፍላጎት፣ የሆነ ውስጣዊ ስሜት ተሰምቷችኋል፤ ነገር ግን ኃጢአትን በአስከፊነቱ በፍፁም አላያችሁትም፡፡ ጠፍታችሁ እንዳላችሁ ተሰምቷችሁ ስለማያውቅ በመራራ ሀዘን ከክፉ መንገዶቻችሁ አልተመለሳችሁም፡፡ በፍፁም ለዓለም አልሞታችሁም፡፡ አሁንም የዓለምን ደስታዎች ትወዳላችሁ፤ በዓለማዊ ጉዳዮች ንግግርም መጠመድ ትወዳላችሁ:: ነገር ግን የእግዚአብሔር እውነት ወደ ሕይወታችሁ ሲገባ የምትሉት ይጠፋባችኋል፡፡ ዝምታው ለምንድን ነው! በአለማዊ ጉዳዮች ይህንን ያህል እየተናገራችሁ እጅግ በሚመለከታችሁ ጉዳይ፣ ሙሉ ነፍሳችሁን ሊይዝ በሚገባው ጉዳይ ላይ ይህንን ያህል ዝም የሚባለው ለምንድን ነው? የእግዚአብሔር እውነት በውስጣችሁ አያድርም፡፡ Testimonies for the Church, Vol. 1, P. 158 -159. MYPAmh 88.5