Go to full page →

እነዚህ ሐሳቦች ባህሪያትን በመመስረት MYPAmh 95

ላይ የሚሠሩት ብዙ ነገር አላቸው። አስተሳሰቦቻችን በጥብቅ መጠበቅ አለባቸው:: አንድ ንጹህ ያልሆነ ሐሳብ በነፍስ ላይ ጥልቅ አሻራን አሳርፎ ስለሚያልፍ አስተሳሰቦቻችን በጥብቅ መጠበቅ አለባቸው፡፡ ክፉ ሐሳብ በአእምሮ ውስጥ ክፉ አሻራን ይተዋል፡፡ አሳቦች ንጹህና ቅዱስ ከሆኑ ግለሰቡ እነርሱን በመለማመዱ የተሻለ ይሆናል፡፡ በእነርሱ አማካይነት መንፈሳዊ ምት ይነቃቃና መልካም የማድረግ ኃይል ይጨምራል። አንድ የዝናብ ጠብታ መሬቱን በማራስ ለሌላኛው እንደሚያዘጋጅ ሁሉ አንድ መልካም ሐሳብ ለሌላኛው መንገድ ያዘጋጃል። MYPAmh 95.4

ረጅም ጉዞ የሚደረገው አንድ ጊዜ አንድ እርምጃን በመሄድ ነው። ተከታታይ እርምጃዎች ወደ መንገዱ ፍፃሜ ያደርሱናል። ረጅም ሰንሰለት ከተናጥል ማገናኛዎች የተሰራ ነው። ከነዚህ መገናኛዎች አንዱ ጉድለት ካለበት ሰንሰለቱ ዋጋ ቢስ ነው። ባሕሪይም እንደዚሁ ነው። በደንብ ሚዛኑን የጠበቀ ባህሪይ የሚመሰረተው በደንብ ከተፈፀሙ የተናጥል ተግባሮች ነው። አንድ ጉድለት መሸነፍ ሲገባው እንክብካቤ ከተደረገለት ግለሰቡን ጉድለት ያለበት ያደርገውና የተቀደሰችውን ከተማ በር ይዘጋበታል። ወደ ሰማይ የሚገባ ሰው ከእንከን ወይም ከፊት መጨማደድ ወይም ከማንኛውም ይህንን ከሚመስል ነገር የፀዳ ባህሪይ ሊኖረው ይገባል። የሚያረክስ ከንቱነት እዚያ መግባት አይችልም። በዳኑት ሠራዊት ሁሉ መካከል አንዲት ጉድለት እንኳን መታየት የለባትም። MYPAmh 95.5