Go to full page →

በየቀኑ የታማኝነት ሕይወት መኖር MYPAmh 96

የእግዚአብሔር ሥራ በአጠቃላይ ፍፁም የሆነበት ምክንያት የፈለገውን ያህል ትንሽም ቢሆን እያንዳንዱ ክፍል ፍፁም በመሆኑ ነው። አምላክ ትንሽዋን የብርጭቆ ቅንጣት የሰራው ልክ ዓለምን ለመስራት የተጠነቀቀውን ያህል በመጠንቀቅ ነው። የሰማዩ አባታችን ፍፁም እንደሆነ እኛም ፍፁማን መሆን ከፈለግን ትንንሽ ነገሮችን በማድረግ ታማኞች መሆን አለብን። ሊሰራ የሚገባው ነገር ሁሉ በደንብ ሊሰራ ይገባል። ሥራችሁ ምንም ቢሆን በታማኝነት ሥሩት። ትናንሽ ነገሮችን በተመለከተ እውነትን ተናገሩ። MYPAmh 96.1

በየዕለቱ የፍቅር ተግባራትን ፈጽሙ፣ ደስታ የሚያመጡ ቃላትንም ተናገሩ። በዚህ መንገድ ስትሠሩ ሳለ እግዚአብሄር ሥራችሁን ያረጋግጥላችሁና ክርስቶስ አንድ ቀን “አንተ መልካምና ታማኝ ባሪያ በጥቂት ታምነሃልና በብዙ እሾመሃለሁ፣ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” ይላችኋል። በፍርድ ቀን በየዕለቱ ሕይወታቸው ታማኝ የነበሩ፣ ምስጋናንና ትርፍን ሳያስቡ ሥራቸውን ለማየትና ለመተግበር ፈጣን የነበሩ «እናንተ የአባቴ ብሩካን ዓለም ሳይፈጠር ወደ ተዘጋጀላችሁ ደስታ ግቡ::” MYPAmh 96.2

የሚሉ ቃላትን ይሰማሉ። ኢየሱስ ያመሰገናቸው በህዝብ ፊት በአንደበተ ርቱዕነት ስላቀረቡት ንግግር ወይም ስላሳዩት የአእምሮ ችሎታ ብቃት ወይም ስለሰጡት የልግስና እርዳታ አይደለም። እነርሱ የተሸለሙት በአጠቃላይ ችላ የተባሉትን ትናንሽ ተግባራትን በመፈፀማቸው ነው። “ተርቤ ነበር አበላችሁኝ::” ይላል:: “ከነዚህ ከታናናሽ ወንድሞቼ ላንዱ ያደረጋችሁትን” ለእኔ አድርጋችኋል።’’ The Youth’s Instructor ,January 17,1901. MYPAmh 96.3