Go to full page →

የእግዚአብሔርና የሰው ፈቃድ ሲተባበሩ MYPAmh 101

እምነትን ተናገር:: በእግዚአብሔር ወገን ባለው ሰልፍ ላይ ሁን። እግርህን በጠላት ወገን አታቁም፡ እግዚአብሔር ረዳትህ ይሆናል። አንተ ለራስህ ማድረግ የማትችለውን እርሱ ያደርግልሃል። ውጤቱም አንተ “እንደ ሊባኖስ ግራር” ትሆናለህ። ሕይወትህ የከበረ ይሆናል! ሥራህ በእግዚአብሔር ይሠራልሃል። ባንተ ውስጥ በእግዚአብሔር እጅ እንደተወለወለ እቃ የሚያደርግህ ኃይል፣ ትጋትና የዋህነት ይኖራል። በእግዚአብሔር ውስጥ ያለውን ደስታና ፍሰሐ ምስጢር ማስተዋል እንድትችል በየዕለቱ ከእውነት ምንጭ መጠጣት አለብህ። ነገር ግን ፈቃድህ የተግባርህ ሁሉ ምንጭ መሆኑን ማስታወስ አለብህ። ይህ በሰው ባህሪይ ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ነገር የሆነው ፈቃድ በውድቀት ለሰይጣን ቁጥጥር አልፎ ተሰጥቷል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እርሱ በሰው ውስጥ የራሱን ደስታ እንዲፈልግና እንዲፈጽም ሲሰራ ቆይቷል። ይህም ለሰው አሰቃቂ ጥፋትና ሥቃይ ለማምጣት ነው። MYPAmh 101.2

ነገር ግን እግዚአብሔር የተወደደውን አንድያ ልጁን የኃጢአት መስዋዕት እንዲሆን የሰጠው ወሰን የለሽመስዋዕትነት የመንግሥቱን አንዲቷንም መርህ ሳይጥስ እንዲህ እንዲል ያስችለዋል፦ ” ራስህን ለኔ ስጥ! ፈቃድህን ስጠኝ! ከሰይጣን ቁጥጥር ነፃ አድርገውና እኔ እቆጣጠረዋለሁ! ከዚያ በኋላ የእኔን መልካም ደስታ እንድትፈልግና እንድታደርግ ባንተ ውስጥ እሰራለሁ።” እርሱ የክርስቶስን አእምሮ ሲሰጥህ ፈቃድህ እንደ እርሱ ፈቃድ ይሆናል! ባሕሪይህም ወደ ክርስቶስ ባህሪይ ይለወጣል። የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈፀም ዓለማህ ነውን? ቃሉን መታዘዝ ፍላጎትህ ነውን? “ማንም ሰው ሊከተለኝ ቢወድ ራሱን ይካድ፣ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።” MYPAmh 101.3

ዝንባሌያችሁን ማጉላትን ካልተዋችሁና እግዚአብሔርን ለመከተል ካልወሰናችሁ በስተቀር ክርስቶስን መከተል የሚባል ነገር ሊኖር አይችልም። የእግዚአብሔር ልጅ የሚያደርጉህ ስሜቶችህና ውስጣዊ ፍላጎቶችህ ሳይሆኑ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማድረግህ ነው። ፈቃድህ ከሆነ ጠቀሜታ ያለው ሕይወት ከፊትህ ነው። ያኔ የመልካም ሥራዎች ምሳሌ በመሆን እግዚአብሔር በሰጠህ ሙሉ ሰውነት ትቆማለህ:: MYPAmh 101.4

ቀጥሎም ራስን የማሰልጠን ደንቦችን ከመጣስ ይልቅ ለመጠበቅ ትረዳለህ:: ከዚያ በኋላ ሥርዓትን ከመናቅና በድርጊትህ ሥርዓተ አልበኝነትን ከማነሣሣት ይልቅ እንዲጠበቅ ትረዳለህ። MYPAmh 101.5

ፈቃድህ በእግዚአብሔር ወገን ቢሆን ኖሮ ምን እንደምትሆን እንደማውቅ በእግዚአብሔር ፍርሃት እነግርሃለሁ። “እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ሠራተኞች ነን።” ሥራህ የፍርድ ፈተናን ማለፍ እንደሚችል አድርገህ ለአሁንና ለዘላለም እየሰራህ ሊሆን ይችላል። ትሞክራለህን? ወደ ኋላ ትዞራለህን? አንተ የክርስቶስ ፍቅርና ምልጃ ዕላማ ነህ ። ራስህን ለእግዚአብሔር አሳልፈህ በመስጠት የእርሱን ፍላጎት ለመጠበቅ እንደ እላማ የተቀመጡትን ከማሳዘንና ተስፋ ከማስቆረጥ ይልቅ ትረዳቸዋለህን? Testimonies for the Church, Vol 5, P. 513-516 MYPAmh 101.6