Go to full page →

መለኮታዊ ምሪት MYPAmh 103

እግዚአብሔር ሊመራን ራሱን ለእኛ የሚገልጽባቸው ሦስት መንገዶች አሉ ። MYPAmh 103.1

እግዚአብሔር ፈቃዱን ለኛ በቃሉ ማለትም በመጽሐፍ ቅዱስ አማካይነት ይገልጽልናል:: MYPAmh 103.2

እንደዚሁም ድምፁ በእጅ ሥራዎቹ አማካኝነት ተገልፆልናል። በራሳችን መንገዶች ከመሄድ፣ እንደ ራሳችን ፍቃድ ከማድረግና ስሜቶቻችን ተረብሸው ዘላለማዊ ነገሮችን ለይተው ለማወቅ እስኪሳናቸውና የሰይጣን ድምፅ ተሸፍኖ የእግዚአብሔር ድምፅ እስኪመስል ድረስ ያልተቀደሰ ልብን ፍላጎት በመከተል ነፍሳችንን ከእርሱ ካልለየን በስተቀር በእጅ ሥራዎቹ ውስጥ እግዚአብሔርን ልናይ እንችላለን። MYPAmh 103.3

ሌላኛው የእግዚአብሔር ድምፅ የሚሰማበት መንገድ በመንፈስ ቅዱስ ተማፅዕኖ አማካይነት ነው። መንፈስ ቅዱስ በባህሪይ ውስጥ የሚገለፅን አሻራ በልብ ውስጥ በመፍጠር ስለ እግዚአብሔር ይገልጽልናል። በማንኛውም ትምህርት ላይ ጥርጣሬ ካላችሁ መጽሐፍ ቅዱሳችሁን አማክሩት:: በእውነት የእምነትን ሕይወት ጀምረህ ከሆነ፣ የጌታ ለመሆን ራስህን ሙሉ በሙሉ ሰጥተህ ከሆነና እርሱም እንደ ራሱ ዓላማ የክብር ዕቃ እንድትሆን ሊቀርፅህና ሊሰራህ ተቀብሎህ ከሆነ በእርሱ እጆች ለመሰራትና እርሱ ወደሚመራህ ማንኛውም ቦታ ለመከተል ልባዊ ፍላጎት ሊኖርህ ይገባል። ይህንን ስታደርግ እርሱ የራሱን ንድፍ በተግባር ላይ እንዲያውል እየተማመንክበት ሲሆን ደህንነትህን በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ በመሥራት ከእርሱ ጋርም እየተባበርክ ነህ። Testimonies for the Church, vol. 5, P.512. MYPAmh 103.4