Go to full page →

ወላጆች እንደጠበቁ ሆኖ መገኘት MYPAmh 115

ትክክል ስለሆነ ትክክለኛ ነገርን ማድረግ ሁልጊዜም የተሸለና ከአደጋ ነጻ የሆነ ነው፡፡ አሁን አንድ አስፈላጊ የሆነ አሳብ አታስብምን? ትክክለኛ አሳብ መሰረቱ ትክክለኛ ድርጊት ነው፡፡ ወላጆች ካንተ የሚጠብቁትን ሆነህ ለመገኘት ወስን፡፡ ያውም ከሁሉ በልጠህ ለመገኘት በታማኝነት የተሞላ ጥረትን ማድረግና ባንተ ላይ የወጣው ወጪ ያለ ቦታው ጥቅም ላይ የዋለ እና ያለአግባብ የባከነ አለመሆኑ እንዲታይ ነው፡፡ ከወላጆችና መምህራን ጥረት ጋር ለመተባበርና ወደ ከፍተኛ የእውቀትና የባሕርይ ደረጃ ለመድረስ ቁርጥ አላማ አድርግ፡፡ ሙሉ እምነት እስኪጣልብህ ድረስ የሚወዱህን ላለማሳዘን (ተስፋ ላለማስቆረጥ) ወስን፡፡ ትክክል የሆነውን ነገር ትክክል ስለሆነ ለማድረግ ከፈለግክ ኢየሱስ እንድታደርገው ይረዳሃል፡፡ Fundamentals of Christian Education, p. 248. MYPAmh 115.3