Go to full page →

የትምህርት ቤት እርምት ዋጋ MYPAmh 119

በዚህ ዘመን ያለው የብዙ ወጣቶች ጋጠ-ወጥና ግድየለሽ ባሕርይ ልብ የሚያሳምም ነው፡፡ ወጣቶች በትምህርት ቤቶቻችን ላሉ ህጎችና ሥነ-ሥርዓቶች ተገዥ ቢሆኑ ኖር በማህበረሰቡ መካከል ያላቸውን አቋም እያሻሻሉ፣ ባሕርያቸውን ከፍ እያደረጉ፣ አእምሮአቸውን የከበረ እያደረጉና ደስታቸውን እጨመሩ መሆናቸውን በማየት በእነዚህ ህጎችና ምሉእ በሆኑ መስፈርቶች ላይ ማመፃቸውን ያቆማሉ፤ በእነዚህ ተቋማት ላይ የጥርጣሬም ሆነ የተሳሳተ ድምዳሜ በመፍጠር ላይ አይሳተፉም ነበር፡፡ MYPAmh 119.5

ወጣቶቻችን የሚፈለግባቸውን ነገር በኃይል በታማኝነት መፈፀም አለባቸው፡፡ ይህ የስኬት ዋስትና ይሆናቸዋል፡፡ በዓለማዊ ሥራቸው ስኬትን አግኝተው የማያውቁ ወጣቶች በመንፈሳዊ ተግባራት ላይ ለመሰማራትም ያልተዘጋጁ ናቸው፡፡ መንፈሳዊ ልምምድ የሚገኘው በግጭት፣ በተስፋ መቁረጥ፤ ጥብቅ በሆነ ራስን መግራትና ተግቶ በመፀለይ ውስጥ ነው፡፡ ወደ ሰማይ የሚወሰደው እርምጃ በአንድ ጊዜ አንድ ደረጃ መሆን አለበት፤ እያንዳንዱ ወደ ፊት የምናደርገው ጉዞ ለቀጣዩ እርምጃችን ብርታት ይሆነናል፡፡ Counsel to Parents, Teachers and Students.98-100. MYPAmh 119.6