Go to full page →

ሌሎችን መርዳት MYPAmh 120

ኋላ ቀር የሆነ አንተን መሰል ተማሪ ቢኖር የማያስተውለውን ትምህርት አስረዳው፡፡ ይህን ማድረግ የአንተን ማስተዋልም ይረዳል፡፡ ቀላል ቃላትን ተጠቀም፤ አሳቦችህን ግልፅ በሆነና ለመረዳት ቀላል በሆነ ቋንቋ ግለጽ፡፡ MYPAmh 120.3

እንዳንተ ያለ ተማሪን በመርዳትህ መምህራኖችህን ትረዳለህ፡፡ ብዙ ጊዜ የረጋ ተማሪ ከመምህሩ ይልቅ ከመሰል ተማሪዎች ሃሳቦችን በፍጥነት የሚቀበል ይመስላል፡፡ ክርስቶስ የሚያመሰግነው ዓይነት መተባበር ይህ ነው፡፡ ኋላ ቀር የሆነውን ተማሪ እንድትረዳ ሊረዳህ ክርስቶስ በአጠገብህ ይቆማል፡፡ MYPAmh 120.4

በትምህርት ቤት ህይወትህ ለድሆችና ላልተማሩ የእግዚአብሔርን ቃል አስደናቂ እውነቶች የመናገር አጋጣሚ ሊኖርህ ችላል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን እያንዳንዱን አጋጣሚ ተጠቀምበት፡፡ በዚህ መንገድ ጥቅም ላይ የዋለውን እያንዳንዱን ጊዜ እግዚአብሔር ይባርከዋል፡፡ Testimonies for the Church vol. 7, P. 275-276. MYPAmh 120.5