Go to full page →

ችሎታን ለእግዚአብሔር መቀደስ MYPAmh 121

ወጣት ወንዶችና ሴቶች በትምህርት ቤቶቻችን እውቀትና ሥነ-ሥርዓት ሊገኝ በሚችልበት መስመር ራሳቸውን ማስቀመጥ አለባቸው፡፡ ችሎታቸውን ለእግዚአብሔር መቀደስ አለባቸው፡፡ ከስህተት አስተምሮዎች ለመጠበቅና በኃጢአተኞች ስህተት እንዳይወሰዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትጉህ ተማሪዎች መሆን አለባቸው፡፡ የእውነትን እውቀት ማግኘት የምንችለው መጽሐፍ ቅዱስን ተግተን በማጥናት ነው፡፡ የምናውቀውን እውነት ስንለማመድ ከቅዱሳት ጽሁፎች ውስጥ የበለጠ ብርሃን በላያችን ይበራል፡፡ MYPAmh 121.3

በእውነት ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ሰዎች እንዲሰሩ ወደ ተጠሩበት ሥራ ሌሎች ሰዎች ወደ ዓለማዊ ሥራ ዝም ብሎ እንጀራን ለማግኘት ብለው በሚገቡበት አሳብ አይገቡም፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሥራ የተቀደሰ መሆኑን በመገንዘብ ወደ ሥራው የሚገቡት ማንኛውም ዓለማዊ ጉዳይ እንዲቆጣጠራቸው ባለመፍቀድ ነው፡፡ MYPAmh 121.4