Go to full page →

ለመሻሻል መመኘት MYPAmh 123

እያንዳንዱ ግለሰብ በግሉ ስለሚያሳድረው ተጽእኖ በእግዚአብሔር ዘንድ ተጠያቂ መሆኑን ቢገነዘብ ኖሮ በምንም መንገድ ሥራ ፈት አይሆንም ነበር፡፡ ነገር ግን በራሱ ደም የገዛውን ማገልገል እንዲችል ችሎታውን ያሳድግ፣ እያንዳንዱን ኃይልም ያሰልጥን ነበር፡፡ MYPAmh 123.1

ወጣቶች ውድ ሕይወቱን ለእነርሱ ለሰጠው ተቀባይነት ያለው አግልግሎት ለመስጠት በተለይ አእምሮአቸውን ማሰልጠንና አዋቂ እንዲሆኑ የሚያደርጋቸውን እያንዳንዱን መልካም አጋጣሚ መጠቀም እንዳለባቸው ሊሰማቸው ይገባል፡፡ ማንም ሰው በደንብ የተማረ ከመሆኑ የተነሳ ከመጽሐፍትም ሆነ ከተፈጥሮ መማር እንደማያስፈልገው የመቁጠር ስህተትን ከመፈጸም ይጠንቀቅ፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ በሳይንስ ውስጥም ሆነ እግዚአብሔር በገለጣቸው ነገሮች ውስጥ ሊገኝ የሚችለውን ሁሉ ለማግኘት እንዲችል በእግዚአብሔር ፈቃድ የተሰጠውን እያንዳንዱን መልካም አጋጣሚ መጠቀም አለበት፡፡ MYPAmh 123.2

እግዚአብሔር ለሰጠን የአካልና የአእምሮ ኃይሎች ተገቢ የሆነ ግምት መስጠትን መማር አለብን፡፡ አንድ ወጣት በመሰላሉ ታችኛው መውጫ ላይ መጀመር ካለበት ተስፋ መቁረጥ የለበትም፡፡ ነገር ግን የክርስቶስን ድምጽ «ልጄ ሆይ ወደ ላይ ውጣ፡፡ አንተ መልካምና ታማኝ ባሪያ፣ በትንሽ ነገር ላይ የታመንህ ስለሆንክ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፡፡» ሲል እስኪሰማ ድረስ እያንዳንዱን መርገጫ ተራ በተራ በመርገጥ እስከ ጫፉ ለመውጣት መወሰን አለበት፡፡ Fundamentals of Christian Education, P. 213. MYPAmh 123.3