Go to full page →

ከፍ ያለ መስፈርት ማስቀመጥ MYPAmh 126

እግዚአብሔር ለሥራው የተዘጋጀን እንድንሆን እያንዳንዱን መልካም አጋጣሚ እንድንጠቀም ይሻል፡፡ ያሉንን የአካልና የአእምሮ ኃይሎች በሞላ በስራ ላይ እንድናውልና ልቦቻችንን ለሥራው ቅዱስና ግሩም ለሆኑ ኃላፊነቶቹ ህያው አድርገን እንድንጠብቅ ይጠብቅብናል፡፡ MYPAmh 126.1

እጅግ ትልቅ ሥራ ለመስራት የተመረጡ ብዙ ሰዎች ጥረት ስለማያደርጉ በጣም ትንሽ ሥራ ይሠራሉ፡፡ በሺሆች የሚቆጠሩ በህይወታቸው ውስጥ ታላቅ ዓላማ እንደሌላቸው፣ ለራሳቸው ሊደርሱበት የሚገባም ከፍ ያለ መስፈርት እንደሌላቸው አድርገው በመቁጠር ያልፋሉ፡፡ ለዚህ አንዱ ምክንያት ለራሳቸው ያላቸው ዝቅተኛ ግምት ነው፡፡ ክርስቶስ ለሕይወታችን ገደብ የለሽ ዋጋ ስለከፈለልን ለራሳችን ዋጋ እንድንሰጥ የሚፈልገው እርሱ በከፈለልን ዋጋ መጠን ነው፡፡ MYPAmh 126.2

ወደ ዝቅተኛ ደረጃ በመድረስ አትርኩ፡፡ መሆን የሚገባንን ያህል አይደለንም፤ ወይንም እግዚአብሔር እንድንሆን የሚፈልግብንን ያህል አይደለንም፡፡ ባለንበት ረክተን እንዳንቀር ወይንም ምድራዊ ተራ ነገሮችን በማሳደድ መስመራችንን እንዳንስት፣ ነገር ግን መድረስ ወደ ሚገባን ከፍተኛ ደረጃ እንድንደርስ፣ የተስተካከልን፣ የተቀደስን፣ የተከበርንና የእግዚአብሔርን መንግስት ፈቃድ በማስፋፋት ጥቅም ላይ የምንውል እንድንሆን እግዚአብሔር የማገናዘብ ኃይሎች ሰጥቶናል፡፡ MYPAmh 126.3