Go to full page →

ለሥራ የተጠሩ ወጣቶች MYPAmh 130

በክርስቶስ ትምህርት ቤት ከታላቁ መምህር ትምህርት ቢያገኙ ኖሮ ጥሩ ሥራ መስራት የሚችሉ ብዙ ክርስቲያን ወጣቶች አሉ፡፡ ቀሳውስት፣ ወንጌላውያንና መምህራን የጠፉትን መፈለግን ችላ ቢሉ እንኳን ልጆችና ወጣቶች ቃሉን በተግባር ላይ ማዋልን ችላ ማለት የለባቸውም፡፡ MYPAmh 130.1

ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች ልጆች በኢየሱስ ስም ለመስራት ይሂዱ፡፡ በሥራው እቅድና አተገባበር አንድነት ይፍጠሩ፡፡ የሰራተኞች ቡድን ፈጥራችሁ ጌታ ፀጋን እንዲሰጣችሁ ለመፀለይ ጊዜ ወስናችሁ እንደወጣቶቻችን ያለ በትክክል የሰለጠነ ሠራተኛ ሠራዊት ቢኖረን የተሰቀለው፣ የተነሣውና በቶሎ የሚመጣው አዳኝ መልእክት እንዴት ባለ ፍጥነት ወደ ዓለም ሁሉ በተዳረሰ ነበር! እንዴት ባለ ፍጥነት የፍፃሜው መከር፣ የሐዘንና የኃጢአት ፍፃሜ በመጣ ነበር! ከስቃዩና ከእንከኑ ጋር ካለው ምድራዊ ሃብት ፋንታ ልጆቻችን ጻድቃን የሚወርሱአትንና ለዘላለም የሚኖሩባትን ምድር የሚወርሱበት ጊዜ ምንኛ ቅርብ ይሁን! እዚህ «ነዋሪዎችዋ አመመኝ አይሉም፡፡» «የለቅሶ ድምፅም ለዘላለም አይሰማም፡፡” የተባበረ ሥራ ለመስራት ወደፊት መቀጠል አትችሉምን? በእግዚአብሔር መንፈስ አንቀሳቃሽነት ለውጤት ከልባችሁ መሥራት እንድትችሉ በስራው ልምድ ያላቸውን እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚወዱ ሰዎችን አማክሩ፡፡ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ችሎታዎች ለስሙ ክብር የሚጠቀሙትን ጌታ ይረዳቸዋል፡፡ እውነትን የሚያምኑ ወጣት ወንዶችና ሴቶቻች ሚስዮናውያን ለመሆን ፈቃደኛ ይሆናሉን? MYPAmh 130.2