Go to full page →

የትጋት ሽልማት MYPAmh 139

ሰነፎች የየዕለቱን የህይወት ተግባራት በታማኝነት በመፈፀም የሚገኘውን ጠቃሚ የሆነ ልምምድ እንደሚያጡ ወጣቶች ያስታውሱ፡፡ ሰነፍ የሆነና በምርጫው መሃይም የሆነ ሰው በመንገዱ ላይ ሁል ጊዜ እንቅፋት የሚሆነውን ነገር እያስቀመጠ ነው፡፡ በታማኝነት ከመስራት የሚመጣውን በረከት አይቀበልም፡፡ ለሰብአዊ ዘር የእርዳታ እጁን ለመዘርጋት ባለመቻሉ እግዚአብሔርን ይዘርፋል፡፡ ሥራው እግዚአብሔር እንዲሰራ ካስቀመጠለት ሥራ እጅግ የተለየ ነው፡፡ ጠቃሚ የሆነ ሥራን መናቅ ተራ የሆኑ ፍላጎቶችን በማደፋፈር የአንድን ግለሰብ እጅግ ጠቃሚ የሆነውን ኃይል ሽባ ያደርጋል፡፡ MYPAmh 139.1

ጥቂቶች ሳይሆኑ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚኖሩት እግዚአብሔር በምህረቱ የሰጣቸውን ጥቅሞች በመጠቀም ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር የምድር ፍሬን በመስጠት ለሰጣቸው ብልጽግና የምስጋና ስጦታ ማምጣትን ይረሳሉ፡፡ እግዚአብሔር በተውሶ የሰጣቸውን መክሊቶች በጥበብ በመነገድ አምራቾችና ተመጋቢዎች እንዲሆኑ እንደሚፈልግባቸው ይረሳሉ፡፡ እግዚአብሔር እንደ ረዳቶቹ ሆነው እንዲሰሩ የሚፈልግባቸውን ሥራ ቢገነዘቡ ኖሮ ኃላፊነትን ሁሉ ሸሽቶ መጠበቅ እንደ መልካም እድል አይሰማቸውም ነበር፡፡ MYPAmh 139.2