Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    (ሐ) የመንፈስ ነጻነት (ጥገኛ አለመሆን)

    የግል ነጻ መሆን (ጥገኛ አለመሆን) አደጋዎች።--እንደ እግዚአብሔር የተለየ ሕዝብ ሁል ጊዜ ለክርስቲያናዊ ሙያችን የሚገባውን ነገር አስቡ፤ የግል ነጻነታችሁን ስትለማመዱት ተጽእኖአችሁ ከእግዚአብሔር ዓላማ ተቃራኒ የሆነ ሥራ እንዳይሰራና፣ እናንተ፣ በሰይጣን ዘዴዎች አማካይነት፣ ደካሞችና ተጠራጣሪዎች በሆኑት መንገድ ላይ በቀጥታ የማሰናከያ ዓለት እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ። ጠላቶቻችን እግዚአብሔርን እንዲሳደቡና እውነቱን በሚያምኑ ላይ እንዲያፌዙባቸው ዕድል የመስጠት አደጋ አለ።--5T 477, 478 (1889). {1MCP 266.1}1MCPAmh 218.2

    የመንፈስ ነጻነት።--በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ወደ ግል ነጻነት ያዘነበሉ ሰዎች ሁል ጊዜም ነበሩ። የመንፈስ ነጻነት ሰብአዊ ወኪል የወንድሞችን ምክር፣ በተለይም ሕዝቡን እንዲመሩ እግዚአብሔር በቢሮዎች ውስጥ የሾማቸውን ሰዎች፣ ከማክበርና ለውሳኔያቸው ከፍተኛ ቦታ ከመስጠት ይልቅ ከመጠን በላይ በራስ ወደ መተማመንና በራስ ውሳኔዎች ላይ ወደ መታመን ለመምራት የተጋለጠ ነው። እግዚአብሔር ማንም ሰው ባይቀበልና ቢንቅ ከበደለኝነት ነጻ ሊሆን የማይችልበትን ልዩ ስልጣንና ኃይል ለቤተ ክርስቲያኑ ሰጥቷል፤ ይህን የሚያደርግ ሰው የእግዚአብሔርን ድምጽ ይንቃል።--AA 163, 164 (1911). {1MCP 266.2}1MCPAmh 218.3

    የተግባር ቅንጅት።--አንድ መጠበቅ ያለበት ነጥብ አለ፣ እርሱም የግል ነጻነት ነው። በክርስቶስ ሰራዊት ውስጥ እንዳሉ ወታደሮች በሥራው የተለያዩ ክፍሎች የተግባር ቅንጅት መኖር አለበት…። እያንዳንዱ ሰራተኛ ሌሎችን ባገናዘበ መልኩ መተግበር አለበት። የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች የሚያደርጉትን ነገር አንዱን ከሌላው ነጥለው አያደርጉም። ወደ ከበረና ትኩረት ወዳለው ተግባር እንዲለወጥ ጥንካሬያችን በእግዚአብሔር መሆን አለበት፣ ብክነት በሌለበት ሁኔታ ጥቅም ላይ መዋል አለበት። ትርጉም በሌላቸው እንቅስቃሴዎች መባከን የለበትም።--5T 534, 535 (1889). {1MCP 266.3}1MCPAmh 219.1

    የራስ ብቃት ለሰይጣን ማታለያዎች ያጋልጠናል።--በመጨረሻ ዘመን አደጋዎች ውስጥ ስለምንኖር፣ በራስ ብቃት የመተማመንና በማንም ላይ ጥገኛ ያለመሆን መንፈስ ካለን፣ራሳችንን ለሰይጣን ማታለያዎች በማጋለጥ እንሸነፋለን።--3T 66 (1872). {1MCP 266.4}1MCPAmh 219.2