Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    (መ) የግብረገብ ነጻነት (ጥገኛ አለመሆን)

    እርስ በርሳችን የመደጋገፍ ሕግ።--ሁላችንም በታላቁ የሰብአዊነት መረብ በአንድነት ስለተሸመንን ሌሎችን ለመጥቀምና ከፍ ለማድረግ ማድረግ የምንችለው ማንኛውም ነገር በኛው ላይ መልሶ በረከትን በማምጣት ይንጸባረቃል። እርስ በርሳችን የመደጋገፍ ሕግ በሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ ይገኛል። ድሆች በሀብታሞች ላይ የሚደገፉት ሀብታሞች በድሆች ላይ ከሚደገፉት አይበልጥም። አንዱ ክፍል እግዚአብሔር ሀብታም ለሆኑ ጎሮቤቶቻቸው ከሰጣቸው በረከቶች ለመካፈል ሲጠይቅ ሌላው ደግሞ ታማኝነት ያለበትን አገልግሎት፣ የድሆች መነሻ ንብረት የሆኑትን የአእምሮ፣ የአጥንትና የጡንቻ ጥንካሬን ይፈልጋል።--PP 534, 535 (1890). {1MCP 267.1}1MCPAmh 219.3

    የግል የሆነ ኃይማኖታዊ ጽኑ እምነትን የመታዘዝ ሀላፊነት።--ሰይጣን ምርኮኞቹን ለማሳወር በሰብአዊ ተጽእኖ አማካይነት የሚሰራባቸው መንገዶች ብዙ ናቸው። እጅግ በርካቶችን የክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ከሆኑት ጋር በፍቅር የሀር ገመዶች በማስተሳሰር ለራሱ ያደርጋቸዋል። ይህ ግንኙነት ምንም ዓይነት ቢሆን--የወላጅና የልጅ፣ የባልና የሚስት፣ ወይም ማህበራዊ-- ውጤቱ ተመሳሳይ ነው፤ የእውነት ተቃዋሚዎች ህሊናን ለመቆጣጠር ኃይላቸውን ስለሚጠቀሙ በእነርሱ ምርኮ ሥር ያሉ ነፍሳት ለተግባራቸው ያላቸውን የራሳቸውን ጽኑ እምነት ለመታዘዝ በቂ ድፍረት ወይም ነጻነት የላቸውም።-- GC 597 (1911). {1MCP 267.2}1MCPAmh 219.4

    የግል ውሳኔ ታፈነ።--ምንም እንኳን አእምሮና ህሊና እንዲያምኑ ቢደረጉም እነዚህ የተታለሉ ነፍሳት [ታዋቂ በሆኑ ቤተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉ ኃይማኖተኞች ነን ባዮች] ከአገልጋዮቻቸው በተለየ ሁኔታ ለማሰብ አይደፍሩም፤ የግል ውሳኔያቸውና ዘላለማዊ ፍላጎቶቻቸው ለሌላ ሰው አለማመን፣ ኩራትና ሚዛናዊ ላልሆነ አመለካከት መስዋዕት ይሆናሉ።-- GC 597 (1911). {1MCP 267.3}1MCPAmh 220.1

    በማንም ተጽእኖር ሥር ሳይወድቁ ለእውነት ለመቆም።--ከክርስቲያኑ ዓለም የኃይማኖት መስፈርት በላይ ለመነሳት ድፍረትንና ከሌሎች ጥገኝነት ነጻ መሆንን ይጠይቃል። የአዳኙን ራስን የመካድ ምሳሌ አይከተሉም፤ መስዋዕትነትን አይከፍሉም፤ ክርስቶስ የደቀ መዝሙርነት ምልክት እንደሆነ የሚናገረውን መስቀል ለማስወገድ ያለማቋረጥ በመፈለግ ላይ ናቸው።--5T 78 (1882). {1MCP 268.1}1MCPAmh 220.2

    ዓለምን በመቃወም ከሞራል ጥገኝነት ነጻ መሆን።-- ዓለምን ስንቃወም የሞራል ነጻነት ሙሉ በሙሉ ቦታውን ይይዛል። ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ሙሉ በሙሉ ስንስማማ፣ ከፍ ካለ ቦታ ላይ እንሆንና ከዓለም ወጎችና ልምምዶች የመለየት አስፈላጊነትን እንመለከታለን። መስፈርታችንን ከዓለም መስፈርት ትንሽ ብቻ ከፍ ማድረግ አይጠበቅብንም፤ ነገር ግን የመለያ መስመሩን በደንብ ግልጽ ማድረግ አለብን።--RH, Jan 9, 1894. (FE 289.) {1MCP 268.2}1MCPAmh 220.3

    የግብረገብ ከጥገኝነት ነጻ መሆን ጥሩ ምግባር ነው።--ብቸኛው ደህንነታችን እንደ እግዚአብሔር የተለየ ሕዝብ መቆም ነው። ለዚህ የተበላሸ ዘመን ወጎችና ፋሽኖች አንዲት ስንዝር እንኳን መሸነፍ የለብንም፣ ነገር ግን ከዘመኑ ብልሹና ጣዖታዊ ልምምዶች ጋር በፍጹም አትደራደሩ።--5T 78 (1882.) {1MCP 268.3}1MCPAmh 220.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents