Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 32—የወረት ፍቅርና እውር ፍቅር

    [ክፍል 5፣ ‹‹የህይወት ጉልበት ሰጭ ኃይል›› የሚለውን ይመልከቱ።]

    የተቃራኒ ፆታዎች መቀራረብ--ጥሩ የሆነ ግንዛቤ የሚያስፈልገው ነገር።--ወጣቶች ስሜታቸውን ከልክ በላይ ያምኑታል። በፍቅረኛቸው በሚስብ ውጫዊ ገጽታ በቀላሉ መማረክ ወይም መወሰድ የለባቸውም። በዚህ ዘመን እየሆነ ባለው ሁኔታ የተቃራኒ ፆታዎች መቀራረብ እግዚአብሔር ከሚያደርገው የበለጠ የነፍሳት ጠላት እጅግ ብዙ ነገር ማድረግ የሚችልበት የማታለልና የግብዝነት ዘዴ ነው። ከማንኛውም ቦታ ይልቅ በዚህ ላይ ጥሩ ግንዛቤ ያስፈልጋል፤ ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ የሚያመጣው ለውጥ አነስተኛ ነው።--RH, Jan 26, 1886. (MYP 450.) {1MCP 295.1}1MCPAmh 240.3

    የከበሩ ባሕርያት መጎልበት አለባቸው።--የተቃራኒ ፆታዎች የመቀራረብ ሀሳቦች መሰረታቸው ጋብቻን በሚመለከት ያሉ የስህተት ሀሳቦች ናቸው። ስሜትንና እውር የፍቅር ፍላጎትን ይከተላሉ። የተቃራኒ ፆታዎች መቀራረብ እየተፈጸመ ያለው በማሽኮርመም መንፈስ ነው። ቅርርብ እየፈጠሩ ያሉ ወገኖች ብዙ ጊዜ የጨዋነትንና የቁጥብነትን ደንቦች ስለሚጥሱ የእግዚአብሔርን ሕግ ባይጥሱ እንኳን የጥንቃቄ ጉድለት ጥፋት አለባቸው። በጋብቻ ተቋም ውስጥ ከፍ ያለ፣ የከበረ፣ ግብረገብነት ያለው የእግዚአብሔር እቅድ አልታየም፤ ስለዚህ ከልብ የሆነ ንጹህ ፍቅርና የከበሩ የባሕርይ መገለጫዎች አልጎለበቱም። --MS 4a, 1885. (MM 141.) {1MCP 295.2}1MCPAmh 240.4

    ንጹህ ፍቅር ከምድራዊ ይልቅ ሰማያዊ ነው።--ቅዱሳን መላእክት ተመልክተው በላይ ባሉት መጻሕፍት እንዲመዘግቡት የማትፈቅደው አንድ ቃል እንኳን መነገር የለበትም፣ አንድ ተግባር እንኳን መፈጸም የለበትም። በእግዚአብሔር ክብር ላይ የሚያተኩር ዓይን ሊኖርህ ይገባል። ልብ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ሊኖራቸው የሚገባ፣ በባህርዩ ከፍ የሚያደርግ፣ ከምድራዊ ይልቅ ሰማያዊ የሆነ ንጹህና ቅዱስ ፍቅር ሊኖረው ይገባል። በተቃራኒ ፆታዎች መቀራረብ ውስጥ ከዚህ የተለየ ማንኛውም ነገር የሚያዋርድ፣ ዝቅ የሚያደርግ ነው፤ ጋብቻ ከፍ ካለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ ጋር አብሮ የማይሄድ ከሆነ ንጹህና ቅዱስ በሆነው እግዚአብሔር ፊት የተቀደሰና የተከበረ መሆን አይችልም። --MS 4a, 1885. (MM 141.) {1MCP 296.1}1MCPAmh 241.1

    የረፋድ ሰዓቶች አደጋ።--ማታ እስከ ረፋድ ድረስ መቀመጥ የተለመደ ነው፤ ነገር ግን ሁለታችሁም ክርስቲያን ብትሆኑ እንኳን ይህ ድርጊት እግዚአብሔርን አያስደስተውም። እነዚህ ጊዜያቸውን ያልጠበቁ ሰዓቶች ጤናን ይጎዳሉ፣ አእምሮ ለቀጣዩ ቀን ሥራ ገጣሚ እንዳይሆን ያደርጋሉ፣ ክፋት እንዲኖር ያደርጋሉ። ወንድሜ ሆይ፣ የዚህን ዓይነት የተቃራኒ ፆታዎች መቀራረብ ለመራቅ የሚያስችልህ በቂ የሆነ የራስ አክብሮት እንደሚኖርህ ተስፋ አደርጋለሁ። በእግዚአብሔር ክብር ላይ የሚያተኩር ዓይን ካለህ በጥንቃቄ ትንቀሳቀሳለህ። እንደ ክርስቲያን እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልግብህን ከፍ ያለ ነገር እንዳታይ እይታህን በሚጋርድ የፍቅር ሕመምተኛነት ስሜት አትሰቃይም። --3T 44, 45 (1872). {1MCP 296.2}1MCPAmh 241.2

    ለጋብቻ የወረት ፍቅር ጥሩ መነሻ አይደለም።--በዚህ ሕገወጥነት በበዛበት ዘመን በአልባሌ ነገር የሚባክኑ የእኩለ ሌሊት ሰዓቶች ብዙ ጊዜ በጉዳዩ ላይ የተሳተፉትን ሁለቱንም ግለሰቦች ወደ ጥፋት ይመራሉ። ወንዶችና ሴቶች ራሳቸውን ሲያዋርዱ ሰይጣን ከፍ ከፍ ይልና እግዚአብሔር ይዋረዳል። ክብር ያለው መልካም ስም በዚህ የወረት ፍቅር ጥንቆላ ሥር መስዋዕት ስለሚሆን እነዚህ ግለሰቦች የሚፈጽሙት ጋብቻ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት በማግኘት አይፈጸምም። የተጋቡት ስሜት ስላንቀሳቀሳቸው ስለሆነ የፍቅር ግንኙነታቸው አዲስነት ሲያልቅ ያደረጉትን ነገር መገንዘብ ይጀምራሉ።--RH, Sept 25, 1888. (AH 56.) {1MCP 296.3}1MCPAmh 241.3

    የውሸት ፍቅር ሊቆጣጠሩት የማይቻል ነው።--ዝም ብሎ ስሜትን ከማርካት ውጭ የተሻለ መሰረት የሌለው ፍቅር ግትር፣ እውር እና ሊቆጣጠሩት የማይቻል ነው። ክብር፣ እውነትና እያንዳንዱ የከበረና ከፍ ያለ የአእምሮ ኃይል በስሜት ባርነት ሥር ይወድቃል። በዚህ የወረት ፍቅር ሰንሰለት የታሰረ ሰው ብዙ ጊዜ የአእምሮንና የህሊናን ድምጽ አይሰማም፤ ክርክርም ሆነ ልመና እየተከተለ ያለውን መንገድ ሞኝነት ወደ ማየት ሊመራው አይችልም። -- ST, July 1, 1903. (AH 51.) {1MCP 296.4}1MCPAmh 242.1

    ያልተቀደሰ ፍቅር ወደ ስህተት ይመራል።--ያልተቀደሰ ሰብአዊ ፍቅር እግዚአብሔር ከሚያመለክተው መንገድ በተቃራኒ ወደ ሌሎች መንገዶች ስለሚያመለክት ሁል ጊዜ ወደ ስህተት ይመራል።--Lt 34, 1891. {1MCP 297.1}1MCPAmh 242.2

    ኃጢአትን መደጋገም የመቋቋም ኃይልን ይቀንሳል።--አንድ ጊዜ ለፈተና የተሸነፈ ሰው ለሁለተኛ ጊዜ በቀላሉ ይሸነፋል። እያንዳንዱ የኃጢአት ድግግሞሽ የመቋቋም ኃይሉን ይቀንሳል፣ ዓይኖቹን ያሳውራል፣ በጥፋተኝነቱ እንዳያምን ያፍናል። እያንዳንዱ ፍላጎትን ለማርካት የተዘራው ዘር ፍሬ ያፈራል። መከሩን ለመከልከል እግዚአብሔር ተአምር አይሰራም።-- PP 268 (1890). {1MCP 297.2}1MCPAmh 242.3

    ስሜት ሁሉንም ነገር ያበላሻል።--የክርስቶስ ቃላት ሁል ጊዜ በአእምሮአችን ውስጥ መሆን አለባቸው፡-‹‹በኖህ ዘመን እንደነበረ በሰው ልጅ ዘመንም እንዲሁ ይሆናል። ይበሉ ይጠጡም ነበር›› (ሉቃስ 17፡ 26፣ 27)። በዚህ ዘመን የምግብ ፍላጎት በአእምሮና በህሊና ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል። ሆዳምነት፣ ሁል ጊዜ ወይንን መጠጣት፣ አስካሪ መጠጥን መጠጣት፣ ትንባሆን መጠቀም በስፋት ይታያል፣ ነገር ግን የክርስቶስ ተከታዮች በሚበሉትና በሚጠጡት መሻታቸውን ይገዛሉ። ጤንነታቸውንና መንፈሳዊ እድገታቸውን በመጉዳት የምግብ ፍላጎታቸውን አያሟሉም። {1MCP 297.3}1MCPAmh 242.4

    ‹‹ኖህ ወደ መርከብ እስኪገባና የጥፋት ውኃ መጥቶ ሁሉን እስከሚያጠፋ ድረስ ያገቡ ይጋቡም ነበር (ቁጥር 27)። ጋብቻን በተመለከተ አሁንም የምናየው ተመሳሳይ መገለጫን ነው። ወጣቶችም ሆኑ ጠቢብና ነገሮችን መለየት የሚገባቸው ወንዶችና ሴቶች በዚህ ጥያቄ ላይ እየፈጸሙ ያሉት፣ አስማት እንደተደረገባቸው ሰዎች ነው። ሰይጣናዊ ኃይል የተቆጣጠራቸው ይመስላል። እጅግ ምስጢር የማይቋጥሩ ጋብቻዎች ይመሰረታሉ። እግዚአብሔርን አያማክሩም። ዕጣው እስኪጣል ድረስ ሰብአዊ ስሜቶች፣ ፍላጎቶች እና የፍቅር ስሜቶች ሁሉንም ነገር አሸንፈዋል። የእነዚህ ነገሮች ውጤቱ ሊነገር የማይችል ስቃይ ሲሆን እግዚአብሔር ተዋርዶአል። የጋብቻ ቃል ኪዳን እያንዳንዱን ዓይነት አስጸያፊ ፍትወተኝነትን ያካትታል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ ቆራጥ የሆነ ለውጥ መኖር የለበትምን? --Lt 74, 1896. (SpTMWI 41.) {1MCP 297.4}1MCPAmh 242.5

    እውር ፍቅር በእያንዳንዱ የአካል ክፍል ላይ ተጽእኖ ያሳድራል።--በዚህ ተላላፊ በሽታ--እውር ፍቅር-- ተጠቂ የሆኑ ሰዎች እያንዳንዱ የአካል ክፍላቸው ለእርሱ ተገዥ ይሆናል። የማገናዘብ ችሎታ የከዳቸው ይመስላል፣ የሚሄዱበት መንገድም ለሚያዩአቸው በሙሉ የሚያስጠላ ነው። ወንድሜ ሆይ፣ ራስህን የወሬ ተገዥ ስላደረግክ ለአስተያየታቸው ዋጋ መስጠት በሚገባህ ሰዎች ግምት ራስህን አውርደሃል። {1MCP 298.1}1MCPAmh 243.1

    በብዙዎች ላይ የበሽታው ችግር የደረሰባቸው ብስለት በሌለው ጋብቻ ስለሆነ አዲስነቱ ሲያልፍና ፍቅር የመስራት የአስማት ኃይሉ ሲያልቅ ከሁለቱ አንዱ ወይም ሁለቱም ስላሉበት እውነተኛ ሁኔታቸው ይነቃሉ። ከዚያ በኋላ የማይጣጣሙ ግን ለሕይወት ዘመን የተጣመሩ መሆናቸውን ይገነዘባሉ። {1MCP 298.2}1MCPAmh 243.2

    እርስ በርሳቸው እጅግ ክቡር በሆነ መሃላ ስለታሰሩ ወደ ፊት ሊመሩት የሚገባውን አስከፊ ሕይወት በተሰበረ ልብ ይመለከታሉ። ካሉበት ሁኔታ የተሻለ ነገር ማውጣት ነበረባቸው፤ ነገር ግን ብዙዎች ይህን አያደርጉም። ከዚህ የተነሣ ለጋብቻ ቃል ኪዳናቸው የማይታመኑ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፤ ጥቂት የማይባሉ ፈሪዎች በአንገታቸው ላይ ለማስቀመጥ ተግተው የሰሩለትን ቀንበር ሕይወታቸውን ወደማጥፋት እስኪደርሱ ድረስ እጅግ አስጨናቂ ያደርጉታል። --5T 110, 111 (1882). {1MCP 298.3}1MCPAmh 243.3

    በወጣትነት እድሜ ጅምር ላይ የሚከሰት ፍቅር።--ሰይጣን በአጠቃላይ የወጣቶችን አእምሮዎች ይቆጣጠራል። ሴት ልጆቻችሁ ራስን መካድንና መቆጣጠርን አልተማሩም። እሹሩሩ ተብለዋል፣ ትዕቢታቸው ተበረታትቷል። ግትሮችና በራሳቸው ፈቃድ የሚሄዱ እስኪሆኑ ድረስ በፈለጉት መንገድ እንዲሄዱ ተትተዋል፣ እነርሱን ከጥፋት ለማዳን የትኛውን መንገድ መከተል እንዳለብህ እንድታውቅ ነገሮችን በፍጥነት በምታስተውልበት ጫፍ ላይ ተቀምጠሃል። ከድፍረታቸው የተነሣ እና ቁጥብነትንና የሴትነት ጨዋነትን ከማጣታቸው የተነሣ የማያምኑ ሰዎች መተረቻ እንዲሆኑ ለማድረግ ሰይጣን እየመራቸው ነው። {1MCP 298.4}1MCPAmh 243.4

    ትናንሽ ወንዶችም በተመሳሳይ ሁኔታ የራሳቸውን መንገድ እንዲከተሉ ተትተዋል። የወጣትነት ዕድሜ መጀመሪያ ላይ ከመድረሳቸው በፊት የዕድሜ አቻዎቻቸው ከሆኑ ትናንሽ ሴት ልጆች ጎን ሆነው ወደ ቤታቸው መሸኘትንና ፍቅር መስራትን ተምረዋል። ወላጆችም የራሳቸውን ፍላጎት በመፈጸምና ለልጆቻቸው ካላቸው የተሳሳተ ፍቅር የተነሣ ሙሉ በሙሉ በግዞት ውስጥ ስለሆኑ ለውጥ ለማምጣትና በዚህ ፈጣን በሆነ ዘመን እጅግ ፈጣን የሆኑ ልጆችን ለመቆጣጠር ጽኑ አቋም የመያዝ ድፍረት የላቸውም። --2T 460 (1870). {1MCP 298.5}1MCPAmh 243.5

    ምስጢራዊ የሆነ የተቃራኒ ፆታዎች መቀራረብ።--ልጆች መማር ያለባቸው ብዙ ትምህርቶች አሉ፣ ከእነዚህ ውስጥ እጅግ አስፈላጊ የሆነው ራሳቸውን እንዲያውቁ መማር ነው። ለወላጆቻቸው ስላሉአቸው ግዴታዎችና ተግባሮች ትክክለኛ የሆኑ አመለካከቶች ኖሮአቸው በክርስቶስ ትምህርት ቤት የዋህና ትሁት የመሆንን ትምህርት ያለ ማቋረጥ መማር አለባቸው። ወላጆቻቸውን ማፍቀርና ማክበር ያለባቸው ቢሆንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገናኙአቸውን ልምድ ያላቸውን ሰዎች ውሳኔ ማክበርም ይጠበቅባቸዋል። {1MCP 299.1}1MCPAmh 244.1

    ወላጆቿ ሳያውቁ ከአንዲት ወጣት ሴት ልጅ ጋር አብሮ የሚሆንና ጓደኛው የሚያደርግ ወጣት ልጅ እሷንም ሆነ ወላጆቿን በተመለከተ የከበረ ክርስቲያናዊ ሚና እየተጫወተ አይደለም። ምስጢራዊ በሆኑ ንግግሮችና ግንኙነቶች አማካይነት አእምሮዋ ላይ ተጽእኖ ሊፈጥር ይችላል፤ ነገር ግን ይህን በማድረጉ እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ሊኖረው የሚገባውን ክቡርነትና ታማኝነት ሊያሳይ አይችልም። ዓላማቸውን ለማሳካት ግልጽ ያልሆነና የመጽሐፍ ቅዱስን መስፈርት ያልተከተለ ሚና ይጫወቱና ለሚወዱአቸውና ታማኝ አሳዳጊ ሊሆኑላቸው ለሚሞክሩ ሰዎች ታማኝ አለመሆናቸውን ያረጋግጣሉ። እንደዚህ ባሉ ተጽእኖዎች የሚፈጸሙ ጋብቻዎች የእግዚአብሔር ቃል በሚያዘው መሰረት ያልተፈጸሙ ናቸው። ሴት ልጅ ተግባሯን እንዳትፈጽም የሚያደርጋት፣ ወላጆቿን ማክበር እንዳለባት የሚናገረውን የእግዚአብሔርን ግልጽና አዎንታዊ ትዕዛዝ በተመለከተ አመለካከቶቿን የሚያውክ ወንድ ልጅ ለጋብቻ ግዴታዎች ታማኝ መሆን የሚችል አይደለም። -- RH, Jan 26, 1886. (FE 101, 102.) {1MCP 299.2}1MCPAmh 244.2

    ከልቦች ጋር ዕቃ ዕቃ መጫወት አያስፈልግም።--ከልቦች ጋር ዕቃ ዕቃ መጫወት ቅዱስ በሆነው አምላክ ዕይታ ቀላል ነገር አይደለም። ሆኖም አንዳንዶች ሴት ልጆችን ይመርጡና እንዲያፈቅሩአቸው ካደረጉ በኋላ የራሳቸውን መንገድ በመሄድ ስለተናገሩአቸው ቃላትና ስለሚያስከትሉት ተጽእኖ ይረሳሉ። አዲስ ፊት ይስባቸውና ተመሳሳይ ቃላት ይናገራሉ፣ ለሌላዋም ተመሳሳይ ትኩረት ይሰጣሉ። --RH, Nov 4, 1884. (AH 57.) {1MCP 299.3}1MCPAmh 244.3

    አእምሮዎች ስለሚያስቡአቸው ርዕሶች መናገር።--ለብዙ ወጣት ሴቶች የንግግራቸው ዋናው ሀሳብ ስለ ወንዶች ነው፤ ወንዶችም የሚያወሩት ስለ ሴቶች ነው። ‹‹በልብ የሞላውን አፍ ይናገራል›› (ማቴ. 12፡ 34)። በአብዛኛው አእምሮዎቻቸው ስለሚያስቡአቸው ርዕሰ ጉዳዮች ያወራሉ። የእነዚህን ክርስቲያን እንደሆኑ የሚናገሩ ወንድና ሴት ልጆችን ቃላት መዝጋቢ መላእክት እየመዘገቡአቸው ነው። በእግዚአብሔር ቀን ሲገናኙአቸው ምንኛ ግራ ይገባቸውና ያፍሩ ይሆን! ብዙ ልጆች ኃይማኖተኛ የሆኑ ግብዞች ናቸው። ክርስቲያን ያልሆኑ ወጣቶች በእነዚህ ግብዞች ይሰናከሉና እነርሱ እንዲድኑ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ለሚያደርጉት ለማንኛውም ጥረት ልበ ደንዳናዎች ይሆናሉ። --2T 460 (1870). {1MCP 300.1}1MCPAmh 245.1

    ለምን ወጣቶች ከወጣቶች ጋር መሆንን እንደሚመርጡ።-- ወጣቶች በዕድሜ የገፉ ሰዎች አብረዋቸው በማይሆኑበት ጊዜ ነጻነት የሚሰማቸው ከመሰሎቻቸው ጋር ስለሆኑ ነው። እያንዳንዱ እንደ ሌላኛው ሁሉ ጥሩ እንደሆነ ያስባል። ሁሉም ጉድለት አለባቸው፣ ነገር ግን ራሳቸውን የሚለኩት በራሳቸው ስለሆነ እና ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ስለሚያነጻጽሩ ፍጹምና እውነተኛ የሆነ መስፈርትን ችላ ይላሉ። ኢየሱስ እውነተኛ ምሳሌ ነው። የእርሱ ራስን መስዋዕት የማድረግ ሕይወት ምሳሌያችን ነው።--1T 154, 155 (1857). {1MCP 300.2}1MCPAmh 245.2

    ፍቅሯን በጥንቃቄ እንድትጠብቅ የተመከረች ወጣት ሴት።--በፍቅር አገላለጽሽ ከመጠን በላይ ነጻ ስለሆንሽ አሁን በምትሄጅበት መንገድ እንድትሄጂ ከተተውሽ የዕድሜ ልክ ስህተት ትፈጽሚያለሽ። ራስሽን በርካሽ ገበያ ላይ አትሽጪ። ለእያንዳንዱ ወንድ ተማሪ ነጻ አትሁኚ። ለጌታ ሥራ ለመስራት እየተዘጋጀሽ እንደሆነ አስቢ፣ ድርሻሽን በደንብ እንድትወጪ፣ መክሊቶችን ለሰጠሽ መልሰሽ መስጠት እንድትችዪና ‹‹አንተ መልካምና ታማኝ ባሪያ›› (ማቴ. 25፡ 23) የሚሉ ውድ ቃላትን ከከናፍሩ እንድትሰሚ ማድመጥና በግንኙነቶችም ግድ የለሽነትን ማስወገድ አለብሽ። {1MCP 300.3}1MCPAmh 245.3

    በእግዚአብሔር አገልግሎት ውስጥ ድርሻሽን መወጣት እንድትችዪ በተቻለ መጠን የአእምሮ ስልጠናን በጥልቀት ለመውሰድ ያለሽን መልካም አጋጣሚዎች በደንብ መጠቀም አለብሽ። ለእግዚአብሔር እውነተኛ ሰራተኛ ለመሆን ብርቱና የተስተካከለ የአእምሮ ችሎታዎች እድገት፣ በጸጋ የተሞላ፣ ክርስቲያናዊ፣ ሁሉን ያካተተ የባሕርይ እድገት ያስፈልግሻል። ፍላጎትሽና አስተሳሰብሽ መታረምና መገራት፣ ስሜቶችሽም በተለምዶአዊ ራስን መቆጣጠር ንጹህ መሆን አለበት። አንድን ነገር እንድታደርጊ የሚያነሳሳሽ ምክንያት ከፍ ያለ መሆን አለበት። እግዚአብሔር ሊያስቀምጥሽ የሚፈልገውን ማንኛውንም ቦታ ለመሙላት ልታገኚ የምትችዪውን ብቃት ሁሉ ሰብስቢ፣ ልታገኝአቸው የምትችዪአቸውን መልካም አጋጣሚዎች በሙሉ ለባሕርይ ትምህርትና ስልጠና አውዪ። ብልህነት ያለበትን ምክር በተመለከተ ሚዛንን መጠበቅ ያስፈልግሻል። ምክርን አትናቂ። --Lt 23, 1893. {1MCP 301.1}1MCPAmh 245.4

    ራስሽን ሥነ-ሥርዓት አስተምሪ።--በሁሉም ነገር ከአንቺ ያነሱ ሰዎችን ትኩረት ለማግኘት ልታዘነብዪ ትችያለሽ። በክርስቶስ ፀጋ ጠቢብ መሆን አለብሽ። እያንዳንዱን እርምጃሽን መመልከት ያለብሽ የራስሽ እንዳልሆንሽ በሚያሳይሽ ብርሃን ነው፤ በዋጋ ተገዝተሻል። ጌታ አማካሪሽ ይሁን። ብቃትን የሚያበላሽ ወይም ሽባ የሚያደርግ ምንም ነገር አታድርጊ። ራስሽን በታማኝነት ያዥ፣ ልፋትን በሚጠይቅ ጥረት ራስሽን ሥነ-ሥርዓት አስተምሪ። ለመማር ፈቃደኛ ከሆንሽና ለሰው አሳቢ ከሆንሽ የክርስቶስ ፀጋ በእያንዳንዱ እርምጃሽ ይረዳሻል። {1MCP 301.2}1MCPAmh 246.1

    ያለፈው ሕይወትሽ ስህተት በፊቴ ስለቀረበልኝ አሁን ይህን እጽፍልሻለሁ፣ ወደ ፊትም በድጋሚ እጽፋለሁ፣ ራስሽን ጥብቅ የሆነ ሥነ-ሥርዓት ማስተማር እንዳለብሽ የቀረቡትን እጅግ ጽኑ የሆኑ ተማጽኖዎችን ለማስቀረት አልደፍርም።. . . {1MCP 301.3}1MCPAmh 246.2

    ወደ ማንኛውም የውሸት መንገድ አትመሪ፣ መልካም ስምሽንና የወደፊት ተስፋዎችሽን መጉዳት ብቻ ሳይሆን አብረሻቸው ለመሆን በምትመርጪያቸው ወንዶች አእምሮ ውስጥ ተስፋ እንዲያደርጉና ይሆናል ብለው እንዲጠብቁ በማድረግ በፍቅር በሽተኛነት ስሜት ተለክፈው የተማሪነት ሕይወታቸውን እንዲያበላሹ ስለምታደርጊ ከወጣት ወንዶች ጋር አብረሽ የመሆን ምርጫ አታሳዪ። አንቺና እነርሱ በትምህርት ቤት ውስጥ ያላችሁት በዚህ ሕይወት ለሚበልጥ ጠቃሚነትና ለወደፊቱ ዘላለማዊ ሕይወት ብቁ እንድትሆኑ በአእምሮና በባሕርይ ብቁ የሚያደርጋችሁን ትምህርት ለማግኘት ነው። ከማንኛውም ወጣት ትኩረት በማግኘትም ሆነ እርሱ እንዲቀርብሽ በማደፋፈር ስህተት አትፈጽሚ። ጌታ መስራት ያለብሽን ሥራ አስቀምጦልሻል። የራስሽን ዝንባሌ በመከተል የወደፊት መዳረሻሽ የብረት ሰንሰለት በሚመስሉ ገመዶች እንዲታሰር ከማድረግ ይልቅ ለእግዚአብሔር አእምሮና ፈቃድ መልስ መስጠት ዓላማሽ ይሁን።--Lt 23, 1893. {1MCP 301.4}1MCPAmh 246.3

    ትክክል ያልሆነ ቅርርብ የአእምሮ ኃይሎችን ያደክማል (የአሥራ ስምንት ዓመት ዕድሜ ላላት ሴት ልጅ የተሰጠ ምክር)።--የአባትሽንና የእናትሽን ሙሉ ማረጋገጫ ሳታገኚ ማንኛውንም ወጣት የማፍቀር መብት የለሽም። አንቺ ገና ልጅ ስለሆንሽ ያለ አባትሽ ሙሉ እውቅናና ማረጋገጫ ማንኛውንም ወጣት መምረጥ አባትሽን አለማክበር ነው። ከዚህ ወጣት ጋር ቅርርብ መፍጠርሽ ያለሽን ሰላማዊ አእምሮና ጤናማ እንቅልፍ መቀማት ነው። አእምሮሽን በሞኝነት ፈጠራዎችና ስሜቶች መሙላት ነው። በጥናቶችሽ እንድታዘግሚ እያደረገሽና ለአእምሮና ለአካል ኃይሎችሽ አሳሳቢ የሆነ ክፋት እየፈጠረ ነው። ተቃውሞ ቢደርስብሽ የምትቆጭና ድብርታም ትሆኚያለሽ። -- Lt 9, 1904. {1MCP 302.1}1MCPAmh 246.4

    የትምህርት ቤት ሥነ-ሥርዓቶች።--የዚህ ኮሌጅ ደንቦች [በሰሜን ካሊፎርኒያ በኮሌጅ ሲቲ ያለ] በትምህርት ጊዜ የወጣት ወንዶችንና ሴቶችን ግንኙነት በጥብቅ ይጠብቃል። አንዳንድ ጊዜ እንደሚሆነው ከሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ወንዶች ሴቶችን እንዲሸኙ የሚፈቀደው እነዚህ ደንቦች በጊዜያዊነት ሲነሱ ነው። {1MCP 302.2}1MCPAmh 247.1

    በባትል ክሪክ ያለው የራሳችን ኮሌጅ የዚህን ያህል ጥብቅ ባይሆንም ተመሳሳይ የሆኑ ደንቦች አሉት። ወጣቶች ያለ ዕድሜያቸው ከተቃራኒ ፆታ ጋር እንዳይቀራረቡና ጥበብ የጎደለው ጋብቻ እንዳይፈጽሙ ለመከልከል የዚህ ዓይነት ደንቦች በጣም አስፈላጊ ናቸው። ወጣቶች ወደ ትምህርት ቤት የሚላኩት ትምህርት እንዲያገኙ እንጂ ከተቃራኒ ፆታ ጋር እንዲላፉ አይደለም። የህብረተሰቡ ጥቅምም ሆነ የተማሪዎች ከፍተኛ ፍላጎት የሚጠይቀው ነገር ቢኖር ባህርያቸው ገና ሳይጎለብት፣ ፍርድ አሰጣጣቸው ወደ ብስለት ደረጃ ሳይደርስ እና የወላጅ ጥንቃቄና ምሪት ተነፍጎአቸው ሳለ፣ የሕይወት አጋርን እንዳይመርጡ ነው። --ST, Mar 2, 1882. (FE 62.) {1MCP 302.3}1MCPAmh 247.2

    የዕድሜ፣ የሁኔታዎችና የተለየ የአስተሳሰብ መንገድ ምክንያቶች።--ከተማሪዎች ጋር በምንሰራቸው ሥራዎች ሁሉ ዕድሜና ባሕርይ ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው። ወጣቶችንና አዛውንትን በተመሳሳይ ሁኔታ ማስተናገድ አንችልም። ጤናማ የሆነ ልምድና ጥሩ አቋም ያላቸው ወንዶችና ሴቶች ለወጣት ተማሪዎች ያልተሰጡ አንዳንድ መልካም ዕድሎች ሊሰጡአቸው የሚችሉባቸው ሁኔታዎች አሉ። ዕድሜ፣ ሁኔታዎችና የተለየ የአስተሳሰብ መንገድ ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው። በሥራዎቻችን ሁሉ ጥበብ በተሞላ ሁኔታ ለሌሎች የምናስብ መሆን አለብን። ነገር ግን በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ካሉ ተማሪዎች ጋር ስንሰራ ጽናታችንንና ንቁነታችንን ወይም ወጣትና ያልበሰሉ ተማሪዎች የሚፈጥሩአቸውን ትርፍ የሌላቸውንና ጥበብ የጎደላቸውን ግንኙነቶች በተመለከተ ያለንን ጥብቅነት መቀነስ የለብንም።-- CT 101 (1913). {1MCP 303.1}1MCPAmh 247.3

    የወረት ፍቅር አደጋዎች።--ኮሌጅን እየተከታተሉ ካሉ ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ ጊዜያቸውን በአግባቡ አይጠቀሙም። በወጣትነት ደስተኛነት ተሞልተው እንዲሸከሙት የመጣውን ገደብ በዘለፋ ይመልሱታል። በተለይ ወጣት ወንዶች በወጣት ሴቶች ላይ ትኩረታቸውን እንዲያደርጉ በማይፈቅዱ ደንቦች ላይ ያምጻሉ። በዚህ በተበላሸ ዘመን የዚህ ዓይነት እርምጃ የሚያመጣው ክፋት በደንብ ይታወቃል። {1MCP 303.2}1MCPAmh 247.4

    ብዙ ወጣቶች አንድነት በሚፈጥሩበት ኮሌጅ ውስጥ በዚህ ረገድ የዓለምን ወግ መቅዳት፣ አስተሳሰቦቻቸውን በእውቀት ፍለጋቸውና በኃይማኖታዊ ነገሮች ላይ ያላቸውን ፍላጎት ወደሚገድብ መስመር ይመልሳል። ወጣት ወንዶችና ሴቶች በወረት ፍቅር ውስጥ በመሆን በትምህርት ቀናት ፍቅራቸውን በእርስ በርሳቸው ላይ ማድረጋቸው ጥሩ ውሳኔ የማድረግ ችግር እንዳለባቸው ያሳያል። በአንተ ላይ እንደታየው፣ እውር ስሜት የማሰብና ውሳኔ የመስጠት ችሎታን ይቆጣጠራል። በዚህ አስማት ባለበት ማታለያ ሥር እያንዳንዱ እውነተኛ ክርስቲያን የሚሰማውን በጣም አስፈላጊ ኃላፊነት ወደ ጎን ስለሚተው፣ መንፈሳዊነት ይሞትና ፍርድና ዘላለማዊነት በጣም ክቡር የሆነ ትርጉማቸውን ያጣሉ። --5T 110 (1882). {1MCP 303.3}1MCPAmh 248.1

    ሰብአዊ ፍቅር ቅድሚያ ሲሰጠው።--በብዙዎች ዘንድ ለሰብአዊው ያለው ፍቅር ለመለኮታዊው ያለውን ፍቅር ይጋርዳል። ግልጽ የሆነውን የጌታን ትዕዛዝ ችላ ለማለት በመድፈር ወደ ኋላ ለማፈግፈግ የመጀመሪያውን እርምጃ ይወስዳሉ፤ ብዙ ጊዜ የዚህ ውጤት ፍጹም ክህደት ነው። ሰዎች የእግዚአብሔርን መስፈርቶች በመቃወም የራሳቸውን ፈቃድ መፈጸም ሁል ጊዜ አደገኛ ነገር መሆኑ ተረጋግጦአል። ሆኖም እግዚአብሔር አንድን ነገር ሲናገር በእርግጠኝነት ማለቱ እንደሆነ መማር ለሰዎች ከባድ ትምህርት ነው። እንደ መርህ አድርገን ስንመለከት፣ ጓደኞቻቸውና ወዳጆቻቸው እንዲሆኑ ክርስቶስን የማይቀበሉትንና የእግዚአብሔርን ሕግ የሚረግጡትን የሚመርጡ ሰዎች በመጨረሻ እነርሱም ከእነዚያ ጋር ተመሳሳይ የሆነ አእምሮና መንፈስ ያላቸው ይሆናሉ። --ST, May 19, 1881. (SD 165.) {1MCP 303.4}1MCPAmh 248.2

    ድብልቅ ጋብቻዎች።--ወንድሜ ሆይ፣ ልጅ ከሆነች፣ ልምድ ከጎደላት፣ ተራ እና ተግባራዊ ለሆኑ የየዕለቱ የህይወት ተግባራት ትምህርት ከጎደላት ልጃገረድ ጋር አብረህ ለመኖር አንድ ለመሆን ተታለህ ከሆነ ስህተት ትሰራለህ፤ ነገር ግን ይህ ጉድለት ለእግዚአብሔር ስላላት ግዴታዎች እውቀት ከማጣቷ ጋር ሲነጻጸር ትንሽ ነው። የብርሃን እጦት የለባትም፤ ከኃይማኖት ጋር የመተዋወቅ ዕድሉ ነበራት፣ ነገር ግን ያለ ክርስቶስ ስለሆነች አሳዛኝ ኃጢአተኛነቷ አልተሰማትም። በወረት ፍቅር ከመነደፍህ የተነሣ ለእግዚአብሔር ፍቅር ከሌላትና ኃይማኖታዊ ሕይወት ከማይስባት ጋር አብረህ ለመሆን እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ከሚገናኝበት የጸሎት ስብሰባ በተደጋጋሚ መቅራት ከቻልክ እግዚአብሔር የዚህን ዓይነት አንድነት የተሳካ እንዲያደርግ እንዴት ትጠብቃለህ? --3T 44 (1872). {1MCP 304.1}1MCPAmh 248.3

    ክርስቲያኖች ከማያምኑት ጋር የሚፈጽሙት ጋብቻ።--ክርስቲያኖች ከማያምኑት ጋር የሚፈጽሙትን ጋብቻ በተመለከተ በክርስቲያኑ ዓለም የእግዚአብሔር ቃል ለሚያስተምረው ነገር አስገራሚና አስደንጋጭ የሆነ ግድ የለሽነት አለ። እግዚአብሔርን እንደሚወዱና እንደሚፈሩ የሚናገሩ ብዙዎች ገደብ የለሽ ጥበብና ምክር ከመቀበል ይልቅ የራሳቸው አእምሮ ወደ መራቸው ለመከተል ይመርጣሉ። የሁለቱንም ክፍሎች ደስታና ደህንነት በዚህ ዓለምና በሚመጣውም በዋናናት በሚመለከት ጉዳይ ላይ የማሰብ ችሎታን መጠቀም፣ ውሳኔ መስጠትና ፈሪሃ-እግዚአብሔር ወደ ጎን ተትቶ እውር ስሜትና ግትር ቆራጥነት እንዲቆጣጠር ተፈቅዶአል። {1MCP 304.2}1MCPAmh 249.1

    ለምክር ጆሮአቸውን የሚደፍኑ ወንዶችና ሴቶች የማያስተውሉና ግንዛቤ የጎደላቸው ናቸው፤ የእነዚህ ሰዎች ጆሮ ለጓደኞች፣ ለዘመዶችና ለእግዚአብሔር አገልጋዮች ልመናና ተማእጽኖ የተደፈነ ነው። የጥንቃቄ ወይም የማስጠንቀቂያ መግለጫ አግባብነት እንደሌለው ጣልቃ ገብነት ስለሚቆጠር የተቃውሞ ሀሳብን በታማኝነት የሚናገር ጓደኛ እንደ ጠላት ይታያል። ይህ ሁሉ ሰይጣን እንዲሆን የሚፈልገው ነገር ነው። የጥንቆላ ድግምቱን በነፍስ ዙሪያ ስለሚሸምን አስማት ይሆንበታል፣ በወረት ፍቅርም ይነደፋል። የማሰብ ችሎታ ራስን የመቆጣጠር ልጓምን በፍትወት አንገት ላይ ይጥላል፤ የዚህ ሰለባ የሆነ ሰው ጊዜው ካለፈ በኋላ የስቃይና የባርነት ሕይወት ለመምራት መገደዱን ለማወቅ እስኪነቃ ድረስ ያልተቀደሰ የፍቅር ስሜት ይቆጣጠራዋል። ይህ በምናብ የተሳለ ስዕል ሳይሆን የእውነታዎች ትዕይንት ነው። እግዚአብሔር በግልጽ ለከለከላቸው አንድነቶች ፈቃድ አይሰጥም። --5T 365, 366 (1885). {1MCP 304.3}1MCPAmh 249.2

    የማያምን ሰው ትርጉም።--ምንም እንኳን የመረጥሽው ጓደኛሽ በሌላ በሁሉም መልኩ የሚገባው ቢሆንም የወቅቱን እውነት አልተቀበለም፤ እርሱ አማኝ ስላልሆነ ከእርሱ ጋር አንድነት እንድትፈጥሪ ሰማይ አልፈቀደልሽም። ነፍስሽን ለአደጋ ሳታጋልጪ ይህን መለኮታዊ ትዕዛዝ ችላ ማለት አትችይም።-- 5T 364 (1885). {1MCP 305.1}1MCPAmh 249.3

    ቅዱስ ያልሆኑ ፈጠራዎች የተከለከለ ቦታ (ለአገልጋይ የተሰጠ ምክር)።--በከፍተኛ አደጋ ውስጥ እንዳለህ ሆኖ ቀርቦልኛል። ሰይጣን ዱካህን እየተከተለ ስለሆነ አንዳንድ ጊዜ አስደሳች የሆኑ ተረቶችን ሹክ በማለት ከወጣትነት ሚስትህ፣ ከልጆችህ እናት፣ ይልቅ እጅግ ተስማሚ ጓደኛ አድርጎ የሚያቀርብልህን ሴት ውብ ፎቶዎች አሳይቶሃል። {1MCP 305.2}1MCPAmh 249.4

    ሰይጣን ብልሃት በተሞላባቸው ፈተናዎቹ አማካይነት በድብቅ፣ ያለመታከት እየሰራ ነው። አስተማሪህ ለመሆን ቁርጠኛ ስለሆነ አሁን እርሱን ለመቋቋም ኃይል ማግኘት በምትችልበት ቦታ ራስህን ማስቀመጥ ያስፈልግሃል። መናፍስትን ወደ መጥራት ድንግዝግዝ ሊመራህ ተስፋ ያደርጋል። ለሚስትህ ያለህን ፍቅር አስትቶ ሌላ ሴትን እንድትወድ ለማድረግ ተስፋ ያደርጋል። ቅዱስ ባልሆነ ፍቅር አማካይነት ይህቺ ሴት አምላክህ እስክትሆን ድረስ አእምሮህ በእሷ ላይ እንዲያርፍ ለማድረግ ይሻል። {1MCP 305.3}1MCPAmh 250.1

    የነፍሳት ጠላት ከያህዌህ ምርጥ ጥበቃዎች መካከል የአንዱን አስተሳሰብ በመስረቅ ሊመጣ ባለው ዓለም ከሚወዳቸው ከአንዳንድ ሴቶች ጋር ሕብረት የመፍጠርና እዚያ ቤተሰብ የመመስረት ዕድል አለ ብሎ እንዲያስብ በመምራት እጅግ ጥቅም አግኝቶበታል። የዚህን ዓይነት አስደሳች ስዕሎች አንፈልግም። የዚህ ዓይነት አመለካከቶች ሁሉ የሚመነጩት ከፈታኙ አእምሮ ነው። . . . {1MCP 305.4}1MCPAmh 250.2

    መንፈሳዊ አፈ ታሪኮች ብዙዎችን እየማረኩአቸው እንደሆነ ተነግሮኛል። አእምሮአቸው ዓለማዊ ስለሆነ፣ ለውጥ ካልመጣ በቀር ይህ መጥፋታቸውን እርግጠኛ ያደርጋል። እነዚህን ቅዱስ ያልሆኑ ፈጠራዎችን እየፈጸሙ ላሉ ሁሉ አቁሙ እላለሁ፤ ስለ ክርስቶስ ብላችሁ ባላችሁበት አቁሙ። ቆማችሁ ያላችሁት በተከለከለ ቦታ ነው።ንስሃ ግቡ፣ ተለወጡም ብዬ እማጸናችኋለሁ። --Lt 231, 1903. (MM 100, 101.) {1MCP 306.1}1MCPAmh 250.3

    ነጻ ፍቅር።--በክህደት ውስጥ፣ ሙታንን በመጥራት ልምምድ ውስጥ እና በነጻ ፍቅር ውስጥ የዚህ ምናባዊ አመለካከትን [መናፍስትን የመጥራትንና ብዙ አማልክትን የማምለክን] ውጤቶች አይቻለሁ። በእነዚህ ትምህርቶች ውስጥ ያለው የነጻ ፍቅር ዝንባሌ እጅግ ድብቅ ከመሆኑ የተነሣ በመጀመሪያ እውነተኛ ባሕርዩን ግልጽ ለማድረግ ከባድ ነበር። ጌታ እስኪያሳየኝ ድረስ ምን ብዬ እንደምጠራው አላወቅኩም ነበር፣ ነገር ግን ቅዱስ ያልሆነ መንፈሳዊ ፍቅር ብዬ እንድጠራው መመሪያ ተሰጥቶኛል። --8T 292 (1904). {1MCP 306.2}1MCPAmh 250.4

    ፍቅር ስሜታዊነት አይደለም።--ኢየሱስ ለሌሎች እንድንሰጥ የሚፈልገው ፍቅርና ርኅራኄ ለነፍሳት ወጥመድ የሆነው የስሜታዊነት መልክ የለውም፤ ክርስቶስ በሕይወት ምሳሌነቱና በቃሉ ያሳየው ሰማያዊ መነሻ ያለው ፍቅር ነው። ነገር ግን ይህን ፍቅር ከማሳየት ይልቅ ራሳችንን ከእርስ በርሳችን የለየነውና እንግዳ ያደረግነው ምን ያህል ጊዜ ነው…። ውጤቱም ከእግዚአብሔር መለየት፣ የቀጨጨ ልምምድ፣ የክርስትና እድገትን ማበላሸት ነው። --YI, Oct 20, 1892. (SD 147.) {1MCP 306.3}1MCPAmh 250.5

    አስመሳዩ ታወቀ።--ሐዋርያው እንዲህ በማለት አስጠንቅቋል፡- ‹‹ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ። እርስ በርሳችሁ በወንድማማች ፍቅር ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ›› (ሮሜ 12፡ 9፣ 10)። ጳውሎስ በክርስቶስ መንፈስ በተነሳሳው ንጹህና ራስ ወዳድነት በሌለው ፍቅር እና ዓለምን በሞላው ትርጉም የለሽና አታላይ ማስመሰል መካከል እንድንለይ ይነግረናል። {1MCP 306.4}1MCPAmh 251.1

    ይህ የወረደ ውሸት ብዙ ነፍሳትን ወደ ስህተት መርቶአቸዋል። ለሕግ ተላላፊ በታማኝነት ስህተቶቹን ከማሳየት ይልቅ ከእርሱ ጋር በመስማማት ትክክል በሆነውና ስህተት በሆነው መካካል ያለውን ልዩነት ያጠፋል። የዚህ ዓይነት እርምጃ በፍጹም ከእውነተኛ ወዳጅነት አይመነጭም። ይህ የተነሳሳበት መንፈስ የሚኖረው ሥጋዊ በሆነ ልብ ውስጥ ብቻ ነው። ክርስቲያን ሁል ጊዜ ደግ፣ ርኅሩኅና ይቅር ባይ ሲሆን ከኃጢአት ጋር ስምምነት ሊኖረው አይችልም። እግዚአብሔርን ከማያምኑ ጋር ያለውን ወዳጅነትና ህብረት መስዋዕት በማድረግ ክፉን ይጠላል፣ መልካም ከሆነው ጋር ይጣበቃል። ኃጢአተኛን ለማዳን ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ፈቃደኛ ስንሆን የክርስቶስ መንፈስ ኃጢአትን ወደ መጥላት ይመረናል። --5T 171 (1882). {1MCP 307.1}1MCPAmh 251.2

    ጓደኛን መምረጥ።--አንዲት ሴት አንድን ወንድ እንደ ሕይወት ጓደኛዋ አድርጋ መቀበል ያለባት ንጹህ የሆነ፣ የወንድነት ባሕርይ ያለው፣ ትጉህ፣ የተሻለ ነገርን የሚመኝ፣ ታማኝ፣ እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚወድ ሲሆን ነው። አንድ ወጣት ወንድ መፈለግ ያለበት በጎኑ የምትሆንና ከሕይወት ሸክሞች ድርሻዋን ለመሸከም ገጣሚ የሆነችን፣ በተጽእኖዋ የምታስከብረውንና የምታስተካክለውን፣ በፍቅሯ ደስተኛ የምታደርገውን ሴት ነው። --MH 359 (1905). {1MCP 307.2}1MCPAmh 251.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents