Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 33—ወጣቶችን የመጋፈጥ አደጋዎች

    ልማዶች መዳረሻን ይወስናሉ።--ባሕርይ እጅግ የሚቀረጸው በልጅነትና በወጣትነት ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ራስን የመቆጣጠር ኃይል መገኘት አለበት። በምድጃ ዙሪያና በቤተሰብ ጠረጴዛ ዙሪያ ውጤቶቻቸው እንደ ዘላለማዊነት ጸንተው የሚኖሩ ተጽእኖዎች ይፈጠራሉ። ከማንኛውም የተፈጥሮ ስጦታ ይልቅ በልጅነት ጊዜ የተመሰረቱ ልማዶች የአንድን ሰው በሕይወት ጦርነት አሸናፊነት ወይም ተሸናፊ መሆን ይወስናሉ። ወጣትነት የዘር ጊዜ ነው። በዚህ ሕይወትም ሆነ በሚመጣው ሕይወት የሚሰበሰበውን የመከሩን ባሕርይ ይወስናል። --DA 101 (1898). {1MCP 308.1}1MCPAmh 252.1

    ራስን መግራትና ራስን ማሞላቀቅ (የራስን ፍላጎት ማሟላት)።--ዓለም የራስን ፍላጎት በማሟላት ላይ ይገኛል። ስህተቶችና አፈ ታሪኮች ተበራክተዋል። ነፍሳትን የሚያጠፉ የሰይጣን ወጥመዶች ተባዝተዋል። በፈሪሀ-እግዚአብሔር ቅድስናን የሚፈጽሙ ሁሉ መሻትን የመግዛትንና ራስን የመቆጣጠርን ትምህርት መማር አለባቸው። የምግብ ፍላጎቶችና የፍቅር ስሜቶች ከፍተኛ ለሆኑ የአእምሮ ኃይላት መገዛት አለባቸው። የእግዚአብሔርን ቃል ቅዱስ እውነቶች መረዳትና መለማመድ እንድንችል ይህ ራስን መግራት ለአእምሮ ብርታትና ለመንፈሳዊ ግንዛቤ አስፈላጊ ነው። ከዚህ የተነሣ መሻትን መግዛት ለክርስቶስ ዳግም ምጻት ለመዘጋጀት በሚሰራው ሥራ ውስጥ ቦታውን ያገኛል።--DA 101 (1898). {1MCP 308.2}1MCPAmh 252.2

    እንደ ሰዎች ራሳችሁን እርግፍ አድርጋችሁ ተው፣ በርቱ።”--ወጣቶች መልካም ዕድሎቻቸውን በደንብ እንዲጠቀሙ፣ ሐዋርያትን ያነሳሳውን መገለጥና ድፍረት እንዲይዙ ሰፊ አመለካከቶች፣ ጥበብ የተሞላባቸው ዕቅዶች ሊኖሩአቸው ይገባል። ዮሐንስ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ጎበዞች ሆይ፣ ብርቱዎች ስለሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸናፋችሁ እጽፍላችኋለሁ›› (1 ዮሐ. 2፡ 14)። በወጣቶች ፊት ከፍ ያለ መስፈርት ስለቀረበ ለእርሱ እርግጠኛ አገልግሎት እንዲሰጡ እግዚአብሔር እየጋበዛቸው ነው። በክርስቶስ ትምህርት ቤት ውስጥ ተማሪዎች ለመሆን የሚደሰቱ እውነተኛ ልብ ያላቸው ወጣቶች ለጌታ ታላቅ ሥራ መስራት የሚችሉት፣ ‹‹ጎልምሱ ጠንክሩ›› (1 ቆሮ. 16፡ 13) በማለት መስመሮቹን ተከትሎ እስከ ዘመናችን ድረስ ድምጹን የሚያሰማውን የጦር አዛዡን ትዕዛዝ ከሰሙ ብቻ ነው።--RH, June 16, 1891. (MYP 24.) {1MCP 309.1}1MCPAmh 252.3

    ስልጠናንና የተለየ ዝግጅትን ችላ የማለት አደጋ።-- ወደ ሥራው መስክ እንደ አገልጋይ፣ እንደ መጻሕፍት ሻጮች ወይም የጽሁፍ ወንጌላዊያን ሆነው መግባት የሚፈልጉ ወጣቶች በመጀመሪያ በቂ የሆነ የአእምሮ ስልጠና ማግኘት እና ለጥሪያቸው የተለየ ዝግጅት ማድረግ አለባቸው። ያልተማሩ፣ ያልሰለጠኑና ያልተሞረዱ ወጣቶች የመክሊትና የትምህርት ኃይለኛ ተጽእኖዎች የእግዚአብሔርን ቃል እውነቶች ወደሚዋጉበት መስክ ለመግባት ዝግጁዎች አይደሉም። ሳይንሳዊውንም ሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እውነት እውቀት የሚጠይቁትን እንግዳ የሆኑ የስህተት ዓይነቶችን፣ ኃይማኖታዊውና ፍልስፍናዊው ተጣምረው፣ በተሳካ ሁኔታ ለመጋፈጥና ለማጋለጥ አይችሉም። --5T 390 (1885). {1MCP 309.2}1MCPAmh 252.4

    የአእምሮ ብሩህነት የስኬት መተማመኛ አይደለም።--ብሩህ የሆኑ ወጣቶች ሁል ጊዜ ከታላቅ ስኬት ላይ ይደርሳሉ የሚለው አባባል እውነት አይደለም። ብዙ ጊዜ መታመንን በሚጠይቁ ኃላፊነቶች ላይ የተቀመጡ መክሊትና ትምህርት ያላቸው ሰዎች ሳይሳካላቸው ቀርቷል። እንደ ወርቅ ያብረቀርቃሉ፣ ነገር ግን ሲፈተን ብልጭልጭ ወረቀትና ዋጋ ቢስ መሆኑ ታውቋል። ታማኝ ስላልሆኑ በሥራቸው አልተሳካላቸውም። {1MCP 309.3}1MCPAmh 253.1

    ትጉህና ትዕግስተኛ ስላልሆኑ እስከ ነገሮች ሥር ድረስ አልሄዱም። በመሰላሉ ሥር በመጀመር ጫፍ ላይ እስከሚደርሱ ድረስ ትዕግስት ባለበት ልፋት ደረጃ በደረጃ ለመውጣት ፈቃደኞች አልነበሩም። እራሳቸው ባቀጣጠሉት ብልጭታ ተራምደዋል። እግዚአብሔር ብቻ ሊሰጥ በሚችለው ጥበብ አልተደገፉም። ያልተሳካላቸው ዕድሉ ስላልነበራቸው ሳይሆን የተረጋጋ አእምሮ ስላልነበራቸው ነው። የትምህርት ዕድሎቻቸው ዋጋ እንዳለው ስላልተሰማቸው በኃይማኖትና በሳይንስ እውቀት ወደ ፊት መሄድ የሚገባቸውን ያህል አልሄዱም። አእምሮዎቻቸውና ባህሪዮቻቸው ትክክለኛ በሆኑ ከፍተኛ መርሆዎች ሚዛናዊ አልሆኑም።-- RH, Dec 8, 1891. (FE 193.) {1MCP 309.4}1MCPAmh 253.2

    ባለማወቅ ውስጥ ምንም መልካም ነገር የለም።--የተለያዩ ዓይነት ሳይንሶችን መማር እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጥቅም እንዳለው አስበሃል። ባለማወቅ ውስጥ ምንም መልካም ነገር የሌለው ሲሆን እውቀት ክርስቲያናዊ እድገትን አያቀጭጨውም፤ በፊትህ ትክክለኛ የሆነ ዓላማ በማስቀመጥ ለሌሎች መልካም ለማድረግና የእግዚአብሔርን ክብር ለማሳወቅ ችሎታዎችህን የመጠቀም ግዴታ እንዳለብህ እየተሰማህ እውቀትን ከመርህ አንጻር ብትፈልገው እውቀት ይህን ዓላማ እንድትፈጽም ይረዳል፤ እግዚአብሔር የሰጠህን ኃይሎች ሥራ ላይ እንድታውላቸውና ለእርሱ አገልግሎት እንድትጠቀምባቸው ይረዳሃል።--3T 223 (1872). {1MCP 310.1}1MCPAmh 253.3

    ያለማመንን ወገን መምረጥ።--በታላቁ የመጨረሻ ቀን እያንዳንዳችን በእግዚአብሔር ቃል እንፈረዳለን። ወጣቶች ስለ ሳይንስ ይናገራሉ፣ ስለተጻፈው ነገርም ጠቢባን ናቸው፤ የእግዚአብሔር መንገዶችና ሥራ ከእነርሱ መረዳት ጋር እንዲገጥም ለማብራራት ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን ይህ ሙሉ በሙሉ አሳዛኝ የሆነ ውድቀት ነው። {1MCP 310.2}1MCPAmh 254.1

    እውነተኛ ሳይንስና መገለጥ ፍጹም የተጣጣሙ ናቸው። የውሸት ሳይንስ በእግዚአብሔር ላይ አይደገፍም። ማስመሰል ያለበት ድንቁርና ነው። ይህ አታላይ ኃይል የብዙዎችን አእምሮዎች በመያዝ ባሪያ አድርጎአቸዋል፣ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን መርጠዋል። መጠራጠር እግዚአብሔርን በፍጥረት ሥራዎቹ ውስጥ ማየት እስከማይቻል ድረስ እጅግ የደከመና ጠባብ የሆነ አእምሮ ምልክት ሆኖ ሳለ መልካም ነገርና የትልቅ አእምሮ ምልክት እንደሆነ አድርገው በማየት ከአለማመን ወገን ቆመዋል። ያላቸውን ኃይል ሁሉ በመጠቀም ለዕድሜ ልክ ቢማሩም እርሱ የሰራቸውን ነገሮች ምስጢር ሙሉ በሙሉ መረዳት አይችሉም። ውስን አእምሮዎች የእግዚአብሔርን ሥራዎች ማብራራት ስለማይችሉ ሰይጣን በብልጠት የተዘጋጁ ማታለያዎቹን እንዲቀበሉ በማምጣት ባለማመን መረብ ውስጥ ያጠላልፋቸዋል። እነዚህ ተጠራጣሪዎች ከእግዚአብሔር ጋር የቀረበ ግንኙነት ቢፈጥሩ ኖሮ እርሱ ዓላማዎቹን መረዳት እንዲችሉ ግልጽ ያደርግላቸው ነበር። --4T 584, 585 (1881). {1MCP 310.3}1MCPAmh 254.2

    የጥርጣሬ አውዳሚ ኃይል።--ለጥርጣሬና ላለማመን ምንም ሰበብ የለም። መረጃዎችን መዝነው መወሰን የሚፈልጉ ሰዎችን ሁሉ እምነት ለማጽናት እግዚአብሔር በቂ የሆነ መረጃ ሰጥቷል። ነገር ግን ከማመናቸው በፊት ተቃውሞ የሚመስል ነገር ሁሉ እስኪወገድላቸው ድረስ ከጠበቁ በፍጹም መርጋት፣ መተከልና በእውነት መመስረት አይችሉም። እግዚአብሔር አስቸጋሪ የሚመስሉንን ነገሮች ሁሉ ከመንገዳችን ላይ አያስወግድም። መጠራጠር የሚፈልጉ ሰዎች የመጠራጠር ዕድል ሊያገኙ ይችላሉ፤ ማመን የሚፈልጉ ሰዎችም እምነታቸውን መመስረት የሚችሉበትን በቂ መረጃ ያገኛሉ። {1MCP 311.1}1MCPAmh 254.3

    አንዳንዶች የያዙት አቋም ራሳቸው እንኳን ሊያብራሩት የማይችሉት አቋም ነው። እርግጠኛ ባለመሆን ጭጋግ ውስጥ መልህቅ ሳይኖራቸው ያለ ዓላማ በመጓዝ እየሰመጡ ናቸው። ሰይጣን ወዲያውኑ የመርከቡን መሪ በመያዝ ደካማ የሆነ ጀልባቸውን ለእርሱ ደስ ወደሚለው ቦታ ይወስደዋል። የእርሱ ፈቃድ ተገዦች ይሆናሉ። እነዚህ አእምሮዎች ሰይጣንን ባይሰሙ ኖሮ በእርሱ ማታለያ አይታለሉም ነበር፤ ሚዛናቸው ወደ እግዚአብሔር ወገን አድልቶ ቢሆን ኖሮ ባልተወዛገቡና ግራ ባልተጋቡ ነበር።-- 4T 583, 584 (1881). {1MCP 311.2}1MCPAmh 254.4

    የተገኘውን እውቀት ተግባራዊ በሆነ ጥቅም ላይ ማዋል አልመቻል።--ወጣቶች ሆይ፣ ብዙ እውቀት አካብታችሁ ያንን እውቀት ተግባራዊ በሆነ ጥቅም ላይ ካላዋላችሁ ዓላማችሁን ስታችኋል። ስትማሩ ጸሎትንና መልካም የሆኑ ኃይማኖታዊ ዕድሎችን ችላ እስክትሉና ለነፍሳት ደህንነት ግድ የለሽ እስክትሆኑ ድረስ በጥናቶቻችሁ ላይ ተመስጣችሁ ከሆነ እና በክርስቶስ ትምህርት ቤት መማር አቁማችሁ ከሆነ፣ ብኩርናችሁን ለማይረባ የምስር ወጥ እየሸጣችሁ ነው። እየተማራችሁ ያላችሁበት ዓላማ ለአፍታ እንኳን ከእይታችሁ መሰወር የለበትም። የመማራችሁ ዓላማ መሆን ያለበት የበለጠውን ጠቃሚ እንድትሆኑና እስከሚቻላችሁ ድረስ ለሌሎች በረከት ለመሆን ችሎታዎቻችሁን ለማሳደግና ለመምራት ነው። {1MCP 311.3}1MCPAmh 255.1

    እውቀትን በማግኘታችሁ የራስ ፍቅራችሁን እና ሀላፊነቶችን ላለመሸከም ሰበብ የመፍጠር ዝንባሌአችሁን የምትጨምሩ ከሆነ ያለ ትምህርት ብትሆኑ ይሻል ነበር። የሆነ ሰው መስራት ያለበትን ሥራ ለመስራት ጥናታችሁንና ንባባችሁን ለመተው ዳተኛ በመሆን መጽሐፍት በእናንተና በተግባሮቻችሁ መካከል ጣልቃ እንዲገቡ እስከምትፈቅዱ ድረስ የምትወዱአቸውና ጣዖታችሁ የምታደርጉአቸው ከሆነ የመማር ፍላጎታችሁን መቆጣጠርና አሁን መስራት የማትፈልጓቸውን ነገሮች የመስራት ፍላጎት ማሳደግ አለባችሁ። በጥቂት የታመነ በብዙም የታመነ ይሆናል።--3T 223, 224 (1872). {1MCP 312.1}1MCPAmh 255.2

    የአካል እንቅስቃሴ ማጣትና ከመጠን በላይ የሆነ የአእምሮ ሥራ የሚያስከትሉአቸው ክፋቶች።--መላው አካል ለሥራ የተፈጠረ ነው፤ የአካል ኃይሎች በእንቅስቃሴ ጤናማ ሆነው ካልተጠበቁ በስተቀር የአእምሮ ኃይሎችን በከፍተኛ ደረጃ ለረዥም ጊዜ መጠቀም አይቻልም። በመማሪያ ክፍል ውስጥ ሊቀር የማይችል መስሎ የሚታየው የአካል እንቅስቃሴ አለመኖር ከሌሎች ጤናማ ካልሆኑ ሁኔታዎች ጋር በመደመር ለልጆች፣ በተለይም ደካማ የሆነ የአካል አቋም ላላቸው፣ ፈታኝ ቦታ ይሆንባቸዋል…። ብዙ ጊዜ በመማሪያ ክፍል ውስጥ የዕድሜ ልክ ሕመምን የሚያመጣ መሰረት መጣሉ የሚያስደንቅ አይደለም። ከአካል ክፍሎች ሁሉ እጅግ አደጋ የማይችለውና የመላው አካል ስርዓት የነርቭ ጉልበት የሚገኝበት አእምሮ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ይደርስበታል። ገና ሳያድግ ከመጠን በላይ እንዲሰራ ከመገደዱ የተነሣ፣ ይህም ጤናማ ባልሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ስለሚፈጸም፣ ብዙ ጊዜ አእምሮ ይደክምና ቋሚ የሆኑ ክፉ ውጤቶች ይከተላሉ።-- Ed 207, 208 (1903). {1MCP 312.2}1MCPAmh 255.3

    ሸክሞችንና ብርቱ ሥራን መራቅ (የሁለት ወጣቶች ልምምድ)።--እነዚህ ወጣቶች በቤታቸው ችላ የሚሉአቸው ተግባራት አሉአቸው። ግዴታቸው የሆኑትን ተግባራትን መቀበልንና የቤት ውስጥ ሀላፊነቶችን መሸከምን አልተማሩም። ልጆቿ እሷ እንድትሸከም መተው የሌለባቸውን በርካታ ሸክሞች የተሸከመች ታማኝና ተግባራዊ የሆነች እናት አለችላቸው። ይህን በማድረጋቸው እናታቸውን አላከበሩም። የአባታቸውን ሥራ እንደ እነርሱ ሥራ በማየት ሸክሞችን ባለመጋራታቸው እርሱን ማክበር እንደሚገባቸው ማክበርን ችላ ብለዋል። ተግባርን ሳይሆን ዝንባሌን ይከተላሉ። {1MCP 312.3}1MCPAmh 256.1

    ሸክምንና ብርቱ ሥራን በመሸሽ በሕይወታቸው የራስ ወዳድነትን መንገድ በመከተላቸው የተሳካ ሕይወት ለመምራት የሚያስችላቸውን፣ ማጣት የሌለባቸውን ጠቃሚ የሆነ ልምምድ ሳያገኙ ቀርተዋል። በትንንሽ ነገሮች ታማኝ የመሆን አስፈላጊነት አልተሰማቸውም፣ በመንገዳቸው ላይ በቀጥታ ተቀምጠው ባሉ ዝቅተኛና የተናቁ የሕይወት ተግባራት ለወላጆቻቸው እውነተኛ፣ ጥንቁቅና ታማኝ የመሆን ግዴታ እንዳለባቸውም አልተሰማቸውም። ለተግባራዊ ሕይወት እጅግ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ የተለመዱ የእውቀት ዘርፎች በላይ ተንጠራርተው ይመለከታሉ። --3T 221, 222 (1872). {1MCP 313.1}1MCPAmh 256.2

    መዝናኛና መደሰቻ።--በመዝናኛና መደሰቻ መካከል ልዩነት አለ። መዝናኛ፣ ስሙ እንደሚያመለክተው፣ እንደገና መፈጠር የሚል ትርጉም ስለሚሰጥ ብርታት ወደ መስጠትና ወደ መገንባት ያዘነብላል። ተራ ከሆኑ ጭንቀቶችና ሥራዎች በመለየት አካልንና አእምሮን ስለሚያድስ ጽኑ ወደሆነው የሕይወት ሥራ አዲስ ብርታት አግኝተን እንድንመለስ ያስችለናል። በሌላ በኩል፣ ሰዎች መደሰቻን የሚፈልጉት ደስታን ለማግኘት ስለሆነ ብዙ ጊዜ ከመጠን በላይ ያደርጉታል፤ ጠቃሚ ለሆነ ሥራ የሚያስፈልገውን ኃይል ስለሚወስድ ለሕይወት እውነተኛ ስኬት እንቅፋት ይሆናል። --Ed 207 (1903). {1MCP 313.2}1MCPAmh 256.3

    የማይረባ ደስታ።--መዝናኛዎቻችን የእርባና ቢስነትን መልክ በመውሰድ የማይረባ ደስታ የሚታይባቸው ትዕይንቶች መሆን የለባቸውም። ከእኛ ጋር ግንኙነት የሚፈጥሩትን ሊጠቅሙና ከፍ ሊያደርጉ በሚችሉበትና እንደ ክርስቲያኖች በእኛና በእነርሱ ዙሪያ እየተሸከረከሩ ያሉ ተግባሮችን ለማከናወን በተሻለ ሁኔታ ብቁ ሊያደርጉን በሚችሉበት ሁኔታ ልንተገብራቸው እንችላለን። --HR, July, 1871. (AH 493). {1MCP 313.3}1MCPAmh 256.4

    ቅንጦት ያለበት የዘመኑ ጭፈራ (ዳንስ)።--ዳዊት አክብሮት ባለበት ደስታ በእግዚአብሔር ፊት መደነሱን ደስታ ፈላጊዎች ቅብጠት ያለበትን ዘመናዊ ዳንስ ለመደነስ እንደ ማስረጃ ይጠቅሳሉ፣ ነገር ግን እንደዚህ ላለ መከራከሪያ ምንም መሰረት የለውም። በእኛ ዘመን መደነስ ከከንቱነትና ከእኩለ ሌሊት መፈንጠዝ ጋር ግንኙነት አለው። ጤንነትና ግብረገብ ለደስታ መስዋዕት ተደርገዋል። ወደ ዳንስ አዳራሽ የሚያዘወትሩ ሰዎች እግዚአብሔርን አያስቡም አያከብሩትምም፤ በእነርሱ ጉባኤዎች ጸሎት ወይም የምስጋና መዝሙር ቦታ የለውም። {1MCP 313.4}1MCPAmh 257.1

    ይህ ፈተና ወሳኝ መሆን አለበት። ክርስቲያኖች ቅዱስ ለሆኑ ነገሮች ያላቸውን ፍቅር የማዳከም ዝንባሌ ያላቸውንና በእግዚአብሔር አገልግሎት የምናገኘውን ደስታ ዝቅ የሚያደርጉብንን መደሰቻዎች መፈለግ የለባቸውም። የእግዚአብሔር ታቦት ከነበረበት በተንቀሳቀሰበት ወቅት እግዚአብሔርን ለማወደስ ጥቅም ላይ የዋለው ሙዚቃና ደስታ የተሞላበት ምስጋና ከዘመኑ የማይረባ ዳንስ ጋር ትንሽ መመሳሰል እንኳን የለውም። አንዱ እግዚአብሔርን ወደ ማስታወስ ስለሚያዘነብል ቅዱስ ስሙን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ነው። ሌላኛው ሰዎች እግዚአብሔርን እንዲረሱና እንዲያዋርዱት የሚያደርግ የሰይጣን መሳሪያ ነው። --PP 707 (1890). {1MCP 314.1}1MCPAmh 257.2

    በመደሰቻዎች ውስጥ እርካታን መሻት።--ጠላት በብዙ መንገዶች ከእግዚአብሔር ቃል ጥናት አእምሮዎቻችንን ለመመለስ ይሻል። ሥጋዊ ለሆነ ልብ ተፈላጊ የሚመስለውን እርካታ ከመደሰቻዎችና ደስታ ከሚሰጡ ነገሮች እንዲሹ ብዙዎችን ይመራል። ነገር ግን እውነተኛ የሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች ይህ ዓለም የሚሰጠውን ደስታ አይፈልጉም፤ ክርስቶስ በሚኖርበት ዘላለማዊ ከተማ ውስጥ ባለው ቤት የሚኖረውንና የዳኑት እግዚአብሔር ለሚፈልግባቸው ነገሮች ከመታዘዛቸው የተነሣ የታዛዥነትን ሽልማት በሚቀበሉበት ቦታ ያለውን ዘለቄታ ያለው ደስታ ይሻሉ። እነዚህ የዚህን ሕይወት ጊዜያዊ የሆነ፣ ርካሽ መደሰቻዎችን አይፈልጉም፣ ነገር ግን ዘለቄታ ያለውን የሰማይ ደስታ ይሻሉ። --MS 51, 1912. (HC 284.) {1MCP 314.2}1MCPAmh 257.3

    ሞኝ አስተሳሰቦችና የማይረቡ ንግግሮች።--ለሌሎች የእውነትን ዕንቁዎች ማቅረብ እንድትችሉ አእምሮዎቻችሁ ሊመረመሩ በማይችሉ በክርስቶስ ሙላቶች ላይ እንዲያተኩሩ ለምን አታደርጉም?...ሥራ-ፈትና እረፍት የለሽ መንፈስን እያሳየን፣ ስሜቶቻችንን ብቻ የሚያረካ፣ የሚያስደስተንን፣ ከንቱ ሳቅን የሚያመጣ ነገርን ያለማቋረጥ እየፈለግን ሳለ ይህን ማድረግ አይቻልም።…ሊመረመሩ የማይችሉ ሀብቶች እያሉልን አእምሮዎቻችንን እንደ እነዚህ ባሉ ነገሮች ላይ ማድረግ የለብንም። የእግዚአብሔርንና የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር ብልጽግና ማስተዋል ዘላለምን ይጠይቀናል። {1MCP 314.3}1MCPAmh 257.4

    ነገር ግን በማይረቡ ንባቦችና ስሜትን በሚቀሰቅሱ ታሪኮች የተጠመዱ ወይም ደስታን በመሻት የተያዙ አእምሮዎች በክርስቶስ ላይ ስለማያተኩሩ በእርሱ የፍቅር ሙላት መደሰት አይችሉም። በከንቱ ሀሳቦችና በማይረቡ ንግግሮች ደስታን የሚያገኝ አእምሮ ጠል ወይም ዝናብ እንደማያገኙ እንደ ጊልቦኣ ተራሮች የክርስቶስ ደስታ የሌለው ነው። -- RH, Mar 15, 1892. {1MCP 315.1}1MCPAmh 258.1

    የደስታ ሽክርክሪት።--የዛሬዎቹ ከተሞች በፍጥነት እንደ ሶዶምና ጎሞራ እየሆኑ ናቸው። በዓላት ብዙ ናቸው፤ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገቢ የሆኑ የሕይወት ተግባራትን እንዳያከናውኑ የደስታ ሽክርክሪት ወደ ራሱ እየሳባቸው ነው። ቀስቃሽ የሆኑ እስፖርቶች--ወደ ትያትር ቤት መሄድ፣ የፈረስ ግልቢያ፣ ቁማር፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣትና ፈንጠዝያ--እያንዳንዱን ስሜት ለተግባር ያነሳሳሉ።{1MCP 315.2}1MCPAmh 258.2

    ወጣቶች በዘመናዊነት ማዕበል ተወስደዋል። ደስታን አስደሳች ስለሆነ ብቻ ለመውደድ የሚማሩ ሰዎች ለፈተናዎች ጎርፍ በር ይከፍታሉ። ለማህበራዊ ድምቀትና ሀሳብ-የለሽ ለሆነ ደስታ ራሳቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ። ጠቃሚ የሆነ ሕይወትን ለመምራት ፍላጎትም ሆነ ችሎታ እስኪያጡ ድረስ ከአንድ ዓይነት የማይረባ ሕይወት ወደ ሌላኛው ይመራሉ።ሊደርሱባቸው የሚፈልጉአቸው መንፈሳዊ ምኞቶች ይቀዘቅዛሉ፤ መንፈሳዊ ሕይወታቸው ይጨልማል። ሁሉም የከበሩ የነፍስ ኃይሎች፣ ሰውን ከመንፈሳዊ ዓለም ጋር የሚያገናኙ ነገሮች ሁሉ ይረክሳሉ። --9T 89, 90 (1909). {1MCP 315.3}1MCPAmh 258.3

    የደስታ ግብዣዎች (ፓርቲዎች)።--ብዙዎች መደሰት ለጤናና ለደስታ አስፈላጊ ነው ብለው ስለሚያስቡ ወጣቶች በደስታ ግብዣዎች ላይ እንዲሳተፉ ይፈቅዳሉ፤ ነገር ግን በዚህ መንገድ ላይ ያሉ አደጋዎች ምንኛ ብዙ ናቸው! የደስታ ፍላጎትን ባረካን መጠን የበለጠውን ያድግና እየጠነከረ ይሄዳል። የሕይወት ልምምድ በአብዛኛው በደስታ ራስን ከማርካት የተሰራ ይሆናል። እግዚአብሔር እንድንጠነቀቅ ይነግረናል። ‹‹የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ›› (1ኛ ቆሮ. 10፡ 12)።--CT 347 (1913). {1MCP 315.4}1MCPAmh 258.4

    ከንቱነት (ትንሽ አስተሳሰብ) አደገኛ ነው።--ለወጣቶች የተሰጠው አንድ ምሳሌ ብቻ ነው፣ ነገር ግን ሕይወታቸው ከክርስቶስ ሕይወት ጋር የሚነጻጸረው እንዴት ነው? እውነትን እናምናለን የሚሉ ወንድና ሴት ወጣቶች በየቦታው የሚያሳዩትን የአስተሳሰብ ከንቱነት ስመለከት እደነግጣለሁ። በሀሳባቸው ውስጥ እግዚአብሔር ያለ አይመስልም። አእምሮዎቻቸው በማይረቡ ነገሮች ተሞልተዋል። ንግግራቸው ባዶና ከንቱ ነው። ለሙዚቃ ንቁ የሆኑ ጆሮዎች ስላሉአቸው ክርስቶስን እንዳይፈልጉ የትኞቹን የአካል ክፍሎች ለእንቅስቃሴ መቀስቀስ፣ አእምሮን መማረክና መቆጣጠር እንዳለበት ሰይጣን ያውቃል። ነፍስ ለመለኮታዊ እውቀት፣ በጸጋ ለማደግ ያላት መንፈሳዊ ናፍቆት ይጠፋል። --1T 496, 497 (1867). {1MCP 315.5}1MCPAmh 258.5

    ፍላጎትን ማሟላት አእምሮ ያለውን ኃይል ይቀማል።--የቤልሻጽርን ከንቱነት የመዘገበው ያው ምስክር በምንሄድበት ሁሉ ከእኛ ጋር አብሮ አለ። ወንድና ሴት ወጣቶች ሆይ፣ እግዚአብሔር እየተመለከታችሁ እንደሆነ ላትገነዘቡ ትችላላችሁ፤ የተፈጥሮ ልብን ስሜቶች ለመፈጸም፣ አዋራጅ የሆኑና ከንቱ የሆኑ ነገሮችን ለመፈጸም ነጻነት እንዳላችሁ ሊሰማችሁ ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን ለእነዚህ ሁሉ ነገሮች መልስ መስጠት አለባችሁ። የምትዘሩትን ያንኑ ስለምታጭዱ፣ የማይረባ ሕይወትን በመምራትና የምግብ ፍላጎትንና ስሜትን በማርካት አእምሮ ማግኘት የሚገባውን ምግብ በመቀማት ከቤታችሁ መሰረቱን እያስወገዳችሁ ከሆነ ‹‹ሥራህን አውቃለሁ›› ለሚለው መልስ ትሰጣላችሁ።--RH, Mar 29, 1892. {1MCP 316.1}1MCPAmh 259.1

    የጅምላ ደስታ አእምሮን ያቀጭጫል።--ለሥጋችን የሚሆነውን ምግብ በጥድፊያ መመገብ ለጤና ጎጂ እንደሆነ ሁሉ የደስታ ምስልን የያዘውን ነገር ሁሉ ተስገብግበን መዋጥ አእምሮ የቀረበለትን መንፈሳዊ ምግብ እንዳይቀበል በማድረግ ያቀጭጨዋል። ሰካራም የሆነ ሰው አንድ ብርጭቆ አስካሪ መጠጥን ለማግኘት እንደሚጓጓ ሁሉ አእምሮ ደስታን ለማግኘት ይጓጓል። ፈተናን መቋቋም የማይቻል ይሆናል። አቀራረቡ አርኪ ስላልሆነ የሰከነ አስተሳሰብ ጣዕም የለውም። የዘላለም ሕይወት ቃላትን ማንበብና ማጥናት በሚለው ሀሳብ ውስጥ ምንም የሚያስደስት ነገር የለም።--Lt 117, 1901. {1MCP 316.2}1MCPAmh 259.2

    አደገኛ የሆኑ መደሰቻዎች።--ለምስጢር ፀሎት፣ በጸሎት መሠዊያ ላይ ለሚደረግ መሰጠት እንቅፋት የሚሆን፣ ወይም በጸሎት ስብሰባዎች ላይ እንዳይሳተፉ የሚያደርግ መደሰቻ አደገኛ ነው። --3T 223 (1872). {1MCP 316.3}1MCPAmh 259.3

    የምግብ ፍላጎትን ማሟላት የአካልና የነፍስ ጤናን ይጎዳል።--ወጣት ሆይ፣ የድርጊት መርሆዎችህን በመምረጥና አእምሮህን ለተጽእኖዎቹ በማስገዛት ባህርይህን ለዘላለም እየመሰረትክ እንደሆነ ትገነዘባለህን? ምንም ነገር ከእግዚአብሔር መደበቅ አትችልም። ክፉ የሆኑ ልማዶችን በምስጢር ልትለማመድ ትችላለህ፣ ነገር ግን ይህ ድርጊትህ ከእግዚአብሔርና ከመላእክት አይደበቅም። እነርሱ እነዚህን ነገሮች የሚመለከቱአቸው ሲሆን አንተም እነርሱን እንደገና መገናኘት አለብህ። እግዚአብሔር አልተደሰተብህም፤ በመንፈሳዊ እውቀት አሁን ካለህበት የእድገት ደረጃ እጅግ ወደ ፊት ተራምደህ መገኘት ይጠበቅብሃል። {1MCP 317.1}1MCPAmh 259.4

    እግዚአብሔር ከሰጣችሁ መልካም ዕድሎችና አጋጣሚዎች ሁሉ ጋር የሚመጣጠን ሥራ የላችሁም። ለሌሎች መፈጸም የሚገቡአችሁ ተግባሮች ያሉአችሁ ሲሆን በተዛባ ሁኔታ የተስተዋለ ተግባር በተዛባ ሁኔታ ይሰራል። እናንተን ብቻ የሚጎዱ ሳይሆኑ በሌሎች ላይ የተሳሳቱ ልምምዶችን ለማጣበቅ የሚረዱ ስህተቶችና ጉድለቶች ይኖራሉ። ለአካልም ሆነ ለነፍስ ጤና ጎጂ የሆኑ የምትፈጽሙአቸው የአመጋገብ ልማዶች አሉአችሁ። ልማዶቻችሁ መሻትን መግዛት የማይታይባቸው፣ የዓለምን ልማዶችና ወጎች የተከተሉ ስለሆኑ የምግብ ፍላጎታችሁን ካለመግዛታችሁ የተነሣ ጤንነታችሁ ተጎድቶአል። አእምሮ ከመጨለሙ የተነሣ፣ ልማዶቻችሁና ተግባሮቻችሁ በተፈጥሮ ውስጥ ካለው የእግዚአብሔር ህግ ጋር እስኪስማሙ ድረስ ጥርት ያለ፣ ንጹህ አስተሳሰብ በፍጹም ሊኖራችሁ አይችልም። --Lt 36, 1887. {1MCP 317.2}1MCPAmh 260.1

    ፈተናዎችን ሽሹ።--ወደ ፈተና እንዳትገቡ ሽሹ። ፈተናዎች ሲከቡአችሁ ለፈተና ያጋለጡአችሁን ሁኔታዎች መቆጣጠር ስለማትችሉ እግዚአብሔር የገባላችሁን ቃል እንዲፈጽምላችሁ በመጠየቅ በመተማመንና ማስተዋል ባለበት ኃይል ‹‹ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ›› (ፊልጵስዩስ 4፡ 13) በማለት መናገር ትችላላችሁ። በእግዚአብሔር ዘንድ ለሁላችሁም ብርታት አለ። ነገር ግን ደካማነታችሁና ኃጢአተኛነታችሁ የማይሰማችሁ እስከሆናችሁ ድረስ ያ ብርታት እንደሚያስፈልጋችሁ በፍጹም አይሰማችሁም። {1MCP 317.3}1MCPAmh 260.2

    ኢየሱስ፣ ውድ አዳኝህ፣ በዘላለማዊ እውነት መድረክ ላይ ያለህን ቦታ አጥብቀህ እንድትይዝ አሁን ይጠራሃል። ከእርሱ ጋር አብራህ መከራን ብትቀበል በዘላለማዊ መንግስቱ የክብር ዘውድ ይጭንልሃል። ለእርሱ ሁሉን መስዋዕት ለማድረግ ፈቃደኛ ከሆንክ እርሱ አዳኝህ ይሆናል። ነገር ግን የራስህን መንገድ ከመረጥክ ዘላለማዊ ሽልማት ለማግኘት ጊዜ እስኪያልፍብህ ድረስ በጨለማ ውስጥ ትሄዳለህ። --3T 45, 46 (1872). {1MCP 317.4}1MCPAmh 260.3

    ቅዱስ ፍላጎትን አጎልብት።--ትክክል የሆነው ነገር ትክክል ስለሆነ ውደደውና ስሜቶችህን፣ ግምቶችህን በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን አብጠርጥረህ እወቅ። በስህተት አቅጣጫ የተመራ ፍላጎት ከተሸነፍክለት ወደ ሀዘን ይመራሃል። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተገናኘ ሁኔታ የተሰጡ ቃላቶችንና ገለጻዎችን ለመያዝ እየሞከርኩ ስለሆነ ብዕሬ ለአንዳፍታ ሲጠራጠር ትክክለኛ የሆኑ ቃላቶች ወደ አእምሮዬ ይመጣሉ። እንድታስታውለኝ እፈልጋለሁ። {1MCP 318.1}1MCPAmh 260.4

    በመንፈስ ቅዱስ ስለተቀደሰ ለእግዚአብሔር ክብር የሚያመጣ ፍላጎትን አጎልብት። ከሁለቱ የወይራ ቅርንጫፎች የሚመጣው ቅዱስ ዘይት በነፍስህ መሠዊያ ላይ ቅዱስ ብርሃንን እየሰጠ ይቀጣጠል። የእነዚህ የወይራ ቅርንጫፎች ሥራ መንፈስ ቅዱስን በልግስና መስጠትን ይወክላል። --Lt 123, 1904. {1MCP 318.2}1MCPAmh 261.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents