Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕረፍ 14—የአካል እንቅስቃሴ

    በመታዘዝ የሚሰራ የሥራ ሕግ።--ሰማያዊ ፍጡራን በሙሉ በማያቋርጥ ስራ ላይ ሲሆኑ፣ ጌታ ኢየሱስ፣ ተግባራዊ በነበረው የህይወት ሥራው፣ ለእያንዳንዱ ሰው ምሳሌ ሰጥቷል። እግዚአብሔር በሰማያት በመታዘዝ የመስራትን ሕግ መስርቷል። [ልብ ይበሉ፡- በመታዘዝ የሚሰራ ሥራ በጥንቃቄ ከተሞላ ትምህርት የበለጠ ዋጋ አለው። ሥራ የአካል ጤንነትን የሚያሻሽል ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ጋር እና ከዩኒቨርስ ጋር እንድንጣጣም ያደርገናል።] እርሱ የፈጠራቸው ፍጡራን በዝምታ ግን ባለማቋረጥ የተመደበላቸውን ሥራ ይሰራሉ። ውቅያኖስ በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ላይ ነው። ‹‹ዛሬ ታይቶ ነገ ወደ እቶን እሳት የሚጣል›› ሣር መስኮችን ውበት በማልበስ የተሰጠውን ስራ ይሰራል። ቅጠሎች የሚነካቸው እጅ ሳይታይ በንፋስ ይንቀሳቀሳሉ። ፀሐይ፣ ጨረቃና ክዋክብት የተሰጣቸውን ተልእኮ በመፈጸም ረገድ ጠቃሚና ግርማ ሞገስ የተላበሱ ናቸው። አካሉና አእምሮው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው ሰው እግዚአብሔር የሰጠውን ቦታ ለመሙላት መስራት አለበት። ሰው ሥራ ፈት መሆን የለበትም። ሥራ መፍታት ኃጢአት ነው። --Lt 103, 1900. (SpT Series B, No. 1, pp 29, 30.) {1MCP 115.1}1MCPAmh 96.1

    የአካል ፋብሪካ ሥራውን መስራት አለበት። ንጹህ፣ ቅዱስና ጤናማ ሆኖ የተፈጠረውን አዳምን በተመለከተ የእግዚአብሔርን እቅድ ተማሩ። አዳም ሥራ ተሰጥቶት ነበር። እግዚአብሔር የሰጠውን የአካል ክፍሎች መጠቀም ነበረበት። ሥራ ፈት መሆን አይችልም ነበር። አእምሮው መስራት ነበረበት፣ ነገር ግን ዝም ብሎ እንደ ማሺን መስራት አልነበረበትም። የአካል ፋብሪካ ሥራውን ይቀጥላል፤ ልብ በእንፋሎት ኃይል እንደሚሰራ ሞተር የተመደበለትን መደበኛ ሥራ በመስራት፣ ደምን ሳያቋርጥ ወደ ሁሉም የአካል ክፍሎች ለመግፋት ይመታል። በመላው ሕያው አካል ውስጥ ተንሰራፍቶ የሚታየው ተግባርና ተግባር ብቻ ነው። እያንዳንዱ የአካል ክፍል የተመደበለትን ሥራ መስራት አለበት። ሰው የአካል እንቅስቃሴ ሳያደርግ የሚቀጥል ከሆነ የአእምሮ ሥራም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ይሄዳል። --Lt 103, 1900. {1MCP 115.2}1MCPAmh 96.2

    የአካል እንቅስቃሴን ከቤት ውጭ (በቂ አየር ባለበት) አድርጉ።--ሁሉም የአካል ክፍሎች እንቅስቃሴ የሚሰጠውን ብርታት ሰጭ ተጽእኖ ይፈልጋሉ። በየዕለቱ ለጥቂት ሰዓታት የሚሰራ የእጅ ሥራ (የጉልበት ሥራ) የአካል ብርታትን በማደስ ለአእምሮ እረፍትና መዝናናት ይሰጣል። --4T 264, 265 (1876). {1MCP 116.1}1MCPAmh 96.3

    አየር ሁሉም ሊያገኙት የሚችሉት ሰማይ የሰጠው የከበረ ደጋፊ ሲሆን ወደ ሰውነታችሁ እንዳይገባ ካልከለከላችሁት በስተቀር ብርታት ሰጭ በሆነው ተጽእኖው ይባርካችኋል። እንኳን ደህና መጣህ ብላችሁ ተቀበሉት፣ ለእርሱ ያላችሁን ፍቅር አሳድጉ፣ እንዲህ ከሆነ ለነርቮች የከበረ አረጋጊ ይሆናል። አየር ንጹህ ሆኖ ለመቆየት ያለማቋረጥ መዘዋወር አለበት። ንጹህና ያልተበከል አየር ደም በአካል ክፍሎች ውስጥ ጤናማ በሆነ ሁኔታ እንዲዘዋወር ያደርጋል። አካልን በማደስ ብርቱና ጤናማ ከማድረጉ በተጨማሪ መረጋጋትንና ሰላምን የመስጠት ተጽእኖው በአእምሮ ላይ ይሰማል። የምግብ ፍላጎትን ይቀሰቅሳል፣ የምግብ መፈጨት ሂደት የተሳካ እንዲሆን ያደርጋል፣ ጤናማና ጣፋጭ እንቅልፍ እንዲኖር ያደርጋል። --1T 702 (1868). {1MCP 116.2}1MCPAmh 97.1

    አለመንቀሳቀስ ውጤታማ የበሽታ መንስኤ።--አለመንቀሳቀስ ውጤታማ የበሽታ መንስኤ ነው። የአካል እንቅስቃሴ የደም ዝውውርን ያፋጥናል ያመጣጥናልም፣ ነገር ግን ሥራ ስንፈታ ደም በነጻነት አይዘዋወርም፤ ከዚህ የተነሣ ለሕይወት አስፈላጊ የሆነ በውስጡ ያለ ለውጥ ሳይካሄድ ይቀራል። ቆዳም ሥራ ፈት ይሆናል። በጠንካራ እንቅስቃሴ የደም ዝውውር ቢነቃቃ፣ ቆዳ በጤናማ ሁኔታ ቢጠበቅ፣ እና ሳንባዎችም በቂ በሆነ ንጹህና ያልተበከለ አየር ቢመገቡ ኖሮ ቆሻሻዎች መወገድ የሚገባቸውን ያህል ይወገዱ ነበር። የዚህ ዓይነቱ የአካል ሥርዓት ቆሻሻ በሚያስወጡ የአካል ክፍሎች ላይ እጥፍ ጫና ከመፍጠሩም በላይ በሽታን ያስከትላል። --MH 238 (1905). {1MCP 116.3}1MCPAmh 97.2

    የአካል እንቅስቃሴን በጥንቃቄ መቆጣጠር።--ጥንካሬን ሳይበዘብዙ በአግባቡ በመጠቀም በደንብ ቁጥጥር የተደረገበት የአካል እንቅስቃሴ ውጤታማ የሆነ የፈውስ ወኪል ነው። --MS 2, 1870. {1MCP 117.1}1MCPAmh 97.3

    አእምሮ ከመጠን በላይ እንዳይሰራ ይከለክላል።--የጉልበት ሥራ የአእምሮ እድገትን አይከለክልም። በፍጹም አያደርግም። በጉልበት ሥራ የተገኙ ጥቅሞች ሰውን ሚዛናዊ በማድረግ አእምሮ ከመጠን በላይ እንዳይሰራ ይከለክላሉ። ልፋት ወደ ጡንቻዎች ይመጣና የደከመው አእምሮ እፎይታ እንዲያገኝ ያደርጋል። የጉልበት ሥራን መሥራት ሴትነትን አይወክልም የሚሉ የፈዘዙና የማይጠቅሙ ብዙ ልጃገረዶች አሉ። ነገር ግን ባሕሪያቸው እጅግ ግልጽ ከመሆኑ የተነሣ የእነዚህ ሰዎች እርግጠኛ ዋጋ ቢስነት የሚሰማቸውን ሰዎች ማታለል አይችልም።... {1MCP 117.2}1MCPAmh 97.4

    የተከበረች ሴት ለመሆን ደካማ፣ ረዳተ ቢስ፣ ከመጠን በላይ የለበሰች፣ ፈገግታ ያላት መሆን አይጠበቅም። ጤናማ አእምሮ እንዲኖር ጤናማ አካል ያስፈልጋል። ጤናማ አካል፣ አስፈላጊ ለሆኑ የቤት ውስጥ ስራዎች ተግባራዊ እውቀት መኖር፣ በደንብ የጎለበተ አእምሮ እንዳይኖር እንቅፋት አይሆንም፤ ለተከበረች ሴት ሁለቱም በከፍተኛ ደረጃ አስፈላጊ ናቸው። --3T 152 (1872). {1MCP 117.3}1MCPAmh 97.5

    ያለ አካል እንቅስቃሴ አእምሮ በትክክል መስራት አይችልም።--ጤናማ ለሆነ ወጣት ኃይለኛና ጠንካራ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ አእምሮን፣ አጥንትንና ጡንቻን ያጠነክራል። ይህ ከባድ ለሆነው የሀኪም ሥራ አስፈላጊ የሆነ ዝግጅት ነው። እንደዚህ ዓይነት የአካል እንቅስቃሴ ከሌለ አእምሮ በትክክል ስራውን መስራት አይችልም። ለኃይሎቹ ስፋት የሚሰጠውን ኃይለኛ፤ ፈጣን እርምጃ መሄድ አይችልም። ሰነፍ (የማይንቀሳቀስ) ይሆናል። እንደዚህ ዓይነት ወጣት እግዚአብሔር እንዲሆን እንዳቀደለት በፍጹም አይሆንም። እጅግ ብዙ ማረፊያ ቦታዎችን ከማዘጋጀቱ የተነሣ እንደረጋ (እንደማይፈስ) ኩሬ ይሆናል። የሚከበው ከባቢ አየር በሞራል ዝቅጠት የተሞላ ነው። --Lt 103, 1900. {1MCP 117.4}1MCPAmh 98.1

    የአካል እንቅስቃሴ ችላ ሲባል የአእምሮ ጥረትም ውስን ይሆናል።--በማያቋርጥ የአእምሮ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች፣ በጥናት ወይም በስብከት፣ እረፍትና ለውጥ ያስፈልጋቸዋል። ትጉህ ተማሪ የአካል እንቅስቃሴን ችላ በማለት ያለማቋረጥ አእምሮው በሥራ እንዲጠመድ ስለሚያደርግ የአካል ኃይሎች ይደክሙና የአእምሮ ጥረትም ይገደባል። ከዚህ የተነሣ ተማሪው በጥበብ ቢሰራ ኖሮ ማድረግ የሚችለውን ነገር ሳያደርግ ይቀራል። --GW 173 (1893). {1MCP 118.1}1MCPAmh 98.2

    የአካልንና የአእምሮን በሥራ መጠመድ አመጣጥን።--የአእምሮና የአካል ኃይሎች በሥራ መያዝ ከተመጣጠነ የተማሪ አእምሮ ይታደሳል። ግለሰቡ ከታመመ፣ ብዙ ጊዜ እንቅስቃሴ የአካል ክፍሎች ወደ ትክክለኛ ሁኔታ እንዲመለሱ ይረዳል። ተማሪዎች ከኮሌጅ ሲወጡ፣ ወደ ኮሌጅ ሲገቡ ከነበረው ይልቅ የተሻለ ጤናና የተሻለ የሕይወት ሕጎች መረዳት ሊኖራቸው ይገባል። ጤንነት እንደ ባሕርይ ሁሉ በቅድስና መጠበቅ አለበት።--CTBH 82, 83, 1890. (CG 343.) {1MCP 118.2}1MCPAmh 98.3

    የአካል እንቅስቃሴ የፈውስ ወኪል ነው።--ከጤና ችግር የተነሣ የደከሙ ሰዎች፣ ጊዜያቸውንና ትኩረታቸውን የሚይዝ ነገር በማይኖርበት ጊዜ፣ ሀሳባቸው በራሳቸው ላይ ስለሚያተኩር በመጥፎ ነገሮች ፍቅር የተለከፉና በቀላሉ የሚናደዱ ይሆናሉ። ብዙ ጊዜ አሁን ካሉበት ሁኔታ በከፋ ደረጃ እንዳሉና ሙሉ በሙሉ ምንም ነገር ማድረግ እንደማይችሉ እስከሚያስቡ ድረስ በመጥፎ ስሜቶቻቸው ላይ ያተኩራሉ። {1MCP 118.3}1MCPAmh 98.4

    በእነዚህ ሁኔታዎች ሁሉ በደንብ ቁጥጥር የተደረገበት የአካል እንቅስቃሴ ውጤታማ የሆነ የፈውስ ወኪል ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች ወደ ቀድሞ ጤንነት ለመመለስ አማራጭ የለውም። ፈቃድ ከእጅ ሥራ ጋር አብሮ ስለሚሄድ እነዚህ ከጤና ችግር የተነሣ የደከሙ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው የፈቃድ መነሳሳት ነው። ፈቃድ እንቅስቃሴ የሌለው በሚሆንበት ጊዜ ሀሳብ የተዛባ ስለሚሆን በሽታን መቋቋም አይቻልም። --MH 239 (1905). {1MCP 118.4}1MCPAmh 98.5

    ምንም ነገር አታድርግ የሚለው ሥርዓት አደገኛ ነው።--ምንም ነገር አታድርግ የሚለው ሥርዓት በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን አደገኛ ነው። አእምሮአቸውንና የአካል ኃይሎቻቸውን ከመጠን ባለፈ ሥራ የሚያጨናንቁ፣ ወይም በአካልና በአእምሮ የተሰበሩ ሰዎች፣ ጤንነታቸው እንዲመለስላቸው ከእንቅስቃሴ መታቀብ አለባቸው የሚለው ሀሳብ ትልቅ ስህተት ነው። አጠቃላይ እረፍት ለጊዜው አስከፊ ስህተትን የሚያስወግድባቸው አጋጣሚዎች አሉ፣ ነገር ግን ከጤና ችግር የተነሣ መዳከማቸው በተረጋገጠ ሰዎች ሁኔታ ይህ አስፈላጊ አይደለም። --MS 2, 1870. {1MCP 118.5}1MCPAmh 99.1

    ለአብዛኞቹ ከጤና ችግር የተነሣ ለደከሙ ሰዎች የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ እጅግ በጣም ትልቅ እርግማን ነው። ይህ ደግሞ በተለየ ሁኔታ ንጽህና በሌላቸው ልምምዶች ችግሮቻቸው ለተባባሰባቸው ሰዎች እውነት ነው። {1MCP 119.1}1MCPAmh 99.2

    ጠቃሚ በሆነ የስራ አቅጣጫ፣ አእምሮንና አካልን ሳያጨናንቁ፣ ቀላል ሥራን መስራት በሁለቱም ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ አለው። ለጡንቻዎች ብርታት ይሰጣል፣ የደም ዝውውርን ያሻሽላል፣ ከሕመም የተነሣ የደከመ ሰው በዚህ ሥራ በበዛበት ዓለም ውስጥ ሙሉ በሙሉ ዋጋ ቢስ አለመሆኑን ማወቅ የሚሰጠውን እርካታ እንዲያገኝ ያደርጋል። በመጀመሪያ ትንሽ ነገር ማድረግ ይችል ይሆናል፤ ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ብርታቱ እየጨመረ እንዳለ ስለሚያውቅ በዚያው ልክ የሚሰራው ሥራ መጠንም ይጨምራል። {1MCP 119.2}1MCPAmh 99.3

    ከአስር በሽተኞች መካከል ዘጠኙ፣ መሻታቸውን በመግዛት ቢመገቡና አስደሳችና ጤናማ የሆነ የአካል እንቅስቃሴን ቢያደርጉ ኖሮ ደህና ሆነው ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን ማዳን ሲችሉ፣ ብዙ ጊዜ ሀኪሞች የሚከታተሉአቸውን በሽተኞች ጤንነታቸው እንዲመለስላቸው በባህር ላይ እንዲጓዙ፣ ማዕድን ወዳለባቸው የውኃ ምንጮች እንዲሄዱ፣ ወይም የአየር ለውጥ ለማድረግ የተለያዩ ቦታዎችን እንዲጎበኙ ይመክራሉ።--Und MS 90. (See MH 240 [1905].) {1MCP 119.3}1MCPAmh 99.4

    የአካል እንቅስቃሴ ስልታዊ መሆን አለበት (በበሽታ ምክንያት ለደከመች እናት የተሰጠ ምክር)--ጌታ ለአንቺ ለማድረግ ጥያቄ የማያቀርበውን ሥራ አንቺ እንድትሰሪ ሰጥቶሻል። ስሜትን ከግምት ውስጥ ሳታስገቢ ከተፈጥሮ ሕግ ጋር በተጣጣመ ሁኔታ ከመርህ መውጣት አለብሽ። እግዚአብሔር በሰጠሽ ብርሃን ላይ መስራት መጀመር አለብሽ። ይህን ሁሉ በአንድ ጊዜ ማድረግ አትችይም ይሆናል፣ ነገር ግን እግዚአብሔር እንደሚረዳሽና እንደሚያበረታሽ በማመን በእምነት፣ በቀስታ በመራመድ፣ ብዙ መስራት ትችያለሽ። {1MCP 119.4}1MCPAmh 99.5

    በሌሎች ላይ ጥገኛ ሳትሆኚ በመራመድና በቤተ ሰብ ውስጥ ቀላል ልፋትን የሚጠይቁ ሥራዎችን በመስራት የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ ትችያለሽ። ማድረግ እንደምትችዪ ማወቅሽ ተጨማሪ ብርታት ይሰጥሻል። ለሌሎች በማቀድ ሂደት እጆቻችሁ የበለጠውን ቢሰሩና አእምሮአችሁ አነስተኛ ሥራ ቢሰራ ኖሮ የአካልና የአእምሮ ብርታታችሁ ይጨምር ነበር። አእምሮአችሁ ሥራ አልፈታም፣ ነገር ግን ሌሎቹ የአካል ክፍሎቻችሁ ተመጣጣኝ የሆነ ሥራ እየሰሩ አይደሉም። {1MCP 119.5}1MCPAmh 100.1

    የአካል እንቅስቃሴ፣ ወሳኝ የሆነ ጥቅም እንድታገኙበት፣ በስልት መከናወን እና የደከሙ የአካል ክፍሎች ከመጠቀማችሁ የተነሣ ብርታት እንዲያገኙ መደረግ አለባቸው። የእንቅስቃሴ ፈውስ [ማሸት] የአካል እንቅስቃሴን ማድረግ እስከማይችሉ ድረስ ለደከሙ ሕመምተኞች ትልቅ ጠቀሜታ አለው። ነገር ግን ሕመምተኞች በሙሉ በራሳቸው ጡንቻዎቻቸውን ለማንቀሳቀስ ችላ በማለት በመታሸት መደገፍና ጥገኛ መሆን ትልቅ ስህተት ነው። --3T 76 (1872). {1MCP 120.1}1MCPAmh 100.2

    ዛሬ እየታየ ያለው የሥነ-ምግባር ብልሽት ጎርፍ ያለ አግባብ ጥቅም ላይ የዋሉ አካሎችና አእምሮዎች ውጤት ነው።-- ዛሬ ዓለማችንን ጠራርጎ እየወሰደ ያለው የሥነ-ምግባር ብልሽት፣ ሰብአዊ ፋብሪካን ትክክል ባልሆነ ሁኔታ ያለ አግባብ የመጠቀም ውጤት ነው። ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች በእጃቸው መስራትን መማር አለባቸው። ያኔ አእምሮ መላው አካል እስኪጎዳ ድረስ የስራ ጫና አይኖርበትም። --Lt 145, 1897. {1MCP 120.2}1MCPAmh 100.3

    አእምሮና አካል በሥራ እንዲጠመዱ ማድረግ ንጹህ ያልሆኑ ሀሳቦችን ወደ መከላከል ያዘነብላል።-- የአካልና የአእምሮ ኃይሎችን ሚዛናዊ በሆነ ሁኔታ በሥራ እንዲጠመዱ ማድረግ ንጹህ ወዳልሆኑ ሀሳቦችና ተግባራት እንዳናዘነብል ይከላከላል። መምህራን ይህን መረዳት አለባቸው። ንጹህ ሀሳቦችና ተግባራት በአጠናን ሁኔታቸው ላይ እንደሚደገፍ መምህራን ተማሪዎችን ማስተማር አለባቸው። በማስተዋል የሚደረግ ተግባር በትክክለኛ ሀሳብ ላይ ይደገፋል። በእርሻ ሥራም ሆነ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የሚደረግ የአካል እንቅስቃሴ አእምሮን ተገቢ ካልሆነ በሥራ መጠመድ የሚከለክል ድንቅ ጠባቂ ነው። እግዚአብሔር የሰጠውን ኃይሎች ሁሉ መጠቀም የማይችል ማንኛውም ወንድ፣ ሴት፣ ወይም ልጅ ጤናውን መጠበቅ አይችልም። የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት አስተውሎ መጠበቅ አይችልም። እግዚአብሔርን ከሁሉ አብልጦና ባልንጀራውን እንደ ራሱ መውደድ አይችልም። --Lt 145, 1897. {1MCP 120.3}1MCPAmh 100.4

    ጥቂት የእጅ ስራ በየቀኑ።--አገልጋዮቻችን ብዙ የአካል ሥራ ቢሰሩ ኖሮ ጤንነትን በተመለከተ በረከቶችን እንደሚያጭዱ ብርሃን ተሰጥቶኛል።…በቀን ውስጥ ጥቂት የጉልበት ሥራ መስራት ለአካል ጤናና ለአእምሮ ጥራት አዎንታዊ አስፈላጊነት አለው። ከዚህ የተነሣ ደም ከአእምሮ ወደተለያዩ የአካል ክፍሎች ይሄዳል። --Lt 168, 1899. (Ev 660, 661.) {1MCP 121.1}1MCPAmh 101.1

    እያንዳንዱ ተማሪ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ አለበት።--እያንዳንዱ ተማሪ ከቀኑ የተወሰነውን ክፍል ለጉልበት ሥራ መለየት አለበት። ይህ ሲሆን ወጣቶች ብዙ ጊዜ የሥራ መፍታት ውጤት ከሆኑ በርካታ ክፋቶችና አዋራጅ ልምምዶች ይጠበቃሉ፣ በዚያው ልክ የስራ ልምድ ይዳብርና በራስ የመተማመን መንፈስ ይበረታታል። ይህ ከትምህርት የመጀመሪያ ዓላማ ጋር አብሮ ስለሚሄድ ሥራን፣ ትጋትንና ንጽህናን በማበረታታት ከፈጣሪ ጋር ወደ መጣጣም ያደርሰናል።--PP 601 (1890). {1MCP 121.2}1MCPAmh 101.2

    በዕብራውያን ትምህርት ቤቶች ይተገበር የነበረው የአካልና የኃይማኖት ሥልጠና ቢጠና ትርፋማ ሊሆን ይችላል። የዚህ ዓይነት ሥልጠና ያለው ጠቀሜታ መደነቅ የሚገባውን ያህል አልተደነቀም። አካልና አእምሮ የቀረበ ግንኙነት ስላላቸው ከፍተኛ ወደሆነ የግብረገብና የአእምሮ እውቀት ደረጃ ለመድረስ አካላችንን የሚቆጣጠሩ ሕጎች በደንብ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል። ጠንካራና ሚዛኑን የጠበቀ ባሕርይ ለማግኘት የአእምሮና የአካል ኃይሎች ሥራ ላይ መዋልና መጎልበት አለባቸው። እግዚአብሔር የሰጠንን ይህን አስደናቂ አካል በአግባቡ ከመያዝና ይህ አካል በጤናማ ሁኔታ እንዲቆይ የሚያደርጉ ሕጎችን ከማጥናት የሚበልጥ ምን ትምህርት ይኖራል? --PP 601 (1890). {1MCP 121.3}1MCPAmh 101.3

    የአካል እንቅስቃሴ ሕይወት ይሰጣል።--አካል እንቅስቃሴ የማያደርግ ከሆነ ደም እየተንቀረፈፈ ይፈሳል፣ የጡንቻዎች መጠንና ጥንካሬ ይቀንሳል።…የአካል እንቅስቃሴ እና ሰማይ ለሁሉም አትረፍርፎ የሰጣቸውን በረከቶች፣ አየርንና የፀሐይ ብርሃንን፣ በነጻ መጠቀም በበሽታ እጅግ ለመነመነ ሕመምተኛ ሕይወትና ብርታት ይሰጣል።...{1MCP 121.4}1MCPAmh 101.4

    ሥራ በረከት እንጂ እርግማን አይደለም። ተግቶ መሥራት ብዙዎችን፣ ወጣቶችንና አዛውንትን፣ ‹‹አሁንም የሆነ ማጭበርበርን ወይም ሥራ ፈት እጆችን ከሚያገኝ›› ከእርሱ ወጥመዶች ሊጠብቃቸው ይችላል። በታማኝነት የሚሰራ ሥራ ግለሰቡን የከበረ ሰው ስለሚያደርገው ማንም ሰው በሥራ አይፈር። እጆች እጅግ ተራ በሆነ ሥራ ላይ ሲጠመዱ አእምሮ ከፍ ባሉና ቅዱስ በሆኑ ሀሳቦች ይሞላል። --YI, Feb 27, 1902. (HC 223.) {1MCP 122.1}1MCPAmh 101.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents