Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 20—የቤት ከባቢ አየር

  የቤት ተጽእኖዎች ህብረተሰብን ይነካል።--የማሕበረሰብ፣ የቤተ ክርስቲያን እና የአገር ልብ ቤተሰብ ነው። የህብረተሰብ ደህንነት፣ የቤተ ክርስቲያን ስኬት፣ እና የአገር ብልጽግና በቤት ተጽእኖዎች ላይ ይደገፋል። --MH 349 (1905). {1MCP 174.1}1MCPAmh 143.1

  ባሕርይን ለመመስረት ውጤታማ ወኪሎች።--የእግዚአብሔር እቅድ በምድር ላይ ያሉ ቤተሰቦች በሰማይ ያለው ቤሰብ ምሳሌ እንዲሆኑ ነው። እንደ እግዚአብሔር እቅድ የተመሰረቱና የተመሩ የክርስቲያን ቤቶች ክርስቲያናዊ ባሕርይን ለመመስረትና የእርሱ ሥራ ወደ ፊት እንዲቀጥል ለማድረግ እጅግ ውጤታማ ከሆኑ ወኪሎች መካከል ናቸው።--6T 430 (1900). {1MCP 174.2}1MCPAmh 143.2

  አምልኮ በቤት።--በሁሉም መንገድ ከሰማያዊ አባታችን ጋር ለማስተዋወቅ ጥረት ያደረጉ ጻድቅ ወላጆች ነበሩኝ። በየጧቱና በየምሽቱ የቤተሰብ ጸሎት ነበረን። በቤተሰባችን ውስጥ በዝማሬ እግዚአብሔርን እናወድስ ነበር። በቤተሰባችን ውስጥ ስምንት ልጆች የነበርን ሲሆን ልባችንን ለኢየሱስ እንድንሰጥ ለማድረግ እያንዳንዱን ዕድል በተገቢ ሁኔታ ተጠቅመውበታል። --MS 80, 1903. {1MCP 174.3}1MCPAmh 143.3

  አንድነቱ ትልቅ ሲሆን ተጽእኖውም ትልቅ ይሆናል።--የቤተሰብ አባላት በቤት ውስጥ ባለው ሥራ የበለጠ አንድ ሲሆኑ አባት፣ እናት፣ ወንድና ሴት ልጆች ከቤት ውጭ የሚኖራቸው ተጽእኖም የበለጠውን ከፍ የሚያደርግና ጠቃሚ ይሆናል። --Lt 189, 1903. (AH 37.) {1MCP 174.4}1MCPAmh 143.4

  ሥልጣን ከጽናት ጋር።-- ሥልጣን ጽኑ በሆነ ጥብቅነት መጠበቅ አለበት፣ እንዲህ ካልሆነ ብዙዎች በማሾፍና በንቀት ይቀበሉታል። ወጣቶችን በተመለከተ ወላጆችና አሳዳጊዎች የሚጠቀሙአቸው ደግነት፣ በእርጋታ ማሳመንና ማሞላቀቅ የሚሉት ነገር በእነርሱ ላይ ሊመጡ ከሚችሉ አስከፊ ክፋቶች አንዱ ነው። በእያንዳንዱ ቤተሰብ ውስጥ ጽኑነት፣ መወሰን መቻል እና አዎንታዊ መስፈርቶች አስፈላጊ ናቸው። --PK 236 (1917). {1MCP 175.1}1MCPAmh 143.5

  ቤት የሚታይ ተጨባጭ ትምህርት ቤት።--የእግዚአብሔር ፍላጎት ቤተሰቦቻችን በሰማይ ያለው ቤተሰብ ምሳሌ እንዲሆኑ ነው። ወላጆችና ልጆች ራሳቸውን ከእርስ በርሳቸው ጋር እንደ እግዚአብሔር ቤተሰብ አባላት በመቁጠር በየዕለቱ ይህን በአእምሮአቸው ይያዙ። ያኔ ሕይወታቸው እግዚአብሔርን የሚወዱና ትዕዛዛቱን የሚጠብቁ ቤተሰቦች ሊኖራቸው የሚገባው ዓይነት ባሕርይ ምን እንደሚመስል ለዓለም የሚታይ ተጨባጭ ትምህርት የሚሰጥ ሕይወት ይሆናል። ክርስቶስ ይከበራል፤ የእርሱ ሰላም፣ ፀጋና ፍቅር የቤተሰቡን ክበብ እንደ ውድ ሽቱ ያውደዋል። --RH, Nov 17, 1896. (AH 17.) {1MCP 175.2}1MCPAmh 143.6

  የሰላም መርህ።--በነፍሳቸው ውስጥ ክርስቶስ የሰላም መርህ ከሆነ በቤት ውስጥ ደስታ-ቢስነት አይኖርም። የደግነት እጦት አይከሰትም። በዚያ ቦታ ሸካራ ወይም የሚያቆስል ንግግር አይኖርም። ለምን? ይህ የሚሆነው እኛ የንጉሳዊ ቤተሰብ አባላት፣ የሰማይ ንጉስ ልጆች፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እጅግ ጠንካራ በሆነ የፍቅር ገመድ-- በእምነት የሚሰራና ነፍስን የሚያነጻ ፍቅር--የታሰርን እንደሆንን ስለምናምንና በተግባር ስለምናሳይ ነው። ኢየሱስን ስለምትወዱ ራስ ወዳድነትን ሁሉ ለማሸነፍና እርሱ በደሙ ለገዛቸው ነፍሳት በረከት፣ መጽናኛ፣ ብርታትና ድጋፍ ለመሆን ያለማቋጥ በሥራ ላይ ትሆናላችሁ። {1MCP 175.3}1MCPAmh 144.1

  ከእኛ ጋር ሕያው ግንኙነት ለሌላቸው ሰዎች ከምንሰራ ይልቅ የክርስቶስን ፍቅር በቤተሰባችን ውስጥ ለማምጣት ተግተን የማንሞክርበት ምክንያት ምን እንደሆነ ማየት አልችልም፤ ነገር ግን በቤታችን ውስጥ ኃይማኖት ካለ፣ ከቤት ወደ ውጭ ይሰፋል። በሁሉም ቦታ ታገኙታላችሁ። ከእናንተ ጋር ወደ ቤተ ክርስቲያን ይዛችሁ ትሄዳላችሁ። ከሥራ ቦታችሁ ወጥታችሁ ስትሄዱ ይዛችሁት ትሄዳላችሁ። በምትሆኑበት ቦታ ሁሉ አብሮአችሁ ይሆናል። የምንፈልገው በቤት ውስጥ ኃይማኖትን ነው። የሚያስፈልገን ምሳሌው አድርጎ እንደሰጠን የክርስቶስ ሕይወት መንፈሳችንን፣ ሕይወታችንን እና ባሕርያችንን የሚቆጣጠር የሰላም መርህ ነው። --MS 36, 1891. {1MCP 175.4}1MCPAmh 144.2

  በተግባር የተገለጠ ፍቅር።--ከእያንዳንዱ የክርስቲያን ቤት ቅዱስ ብርሃን መብራት አለበት። ፍቅር በተግባር መታየት አለበት። በእያንዳንዱ የቤት ግንኙነት ውስጥ አሳቢነት ባለበት ቸርነት፣ ጨዋነትና ራስ ወዳድነት በሌለበት ደግነት ራሱን በማሳየት ወደ ውጭ መፍሰስ አለበት። ይህ መርህ ተግባራዊ የሚሆንባቸው ቤቶች--እግዚአብሔር የሚመለክባቸውና እውነተኛ ፍቅር የነገሰባቸው ቤቶች-- አሉ። ከእነዚህ ቤቶች የጧትና የምሽት ጸሎት እንደ ጣፋጭ እጣን በእግዚአብሔር ፊት ይወጣል፣ የእርሱ ምህረትና በረከትም በሚለምኑት ላይ እንደ ማለዳ ጤዛ ይወርዳል። --PP 144 (1890). {1MCP 176.1}1MCPAmh 144.3

  የቤት ክርስትና በሁሉም ቦታ ያበራል።--ቤት መሆን የሚገባውን ሆኖ እንዲገኝ የሚደረግ ጥረት--የሰማይ ቤት ምሳሌ እንዲሆን--ሰፋ ባለው ክበብ ላለው ሥራ ያዘጋጀናል። ለእርስ በርስ ገርነት ያለበትን አክብሮት በማሳየት የተወሰደ ትምህርት የእውነተኛ ኃይማኖትን መርሆዎች መማር ያለባቸውን ልቦች እንዴት መድረስ እንደምንችል እንድናውቅ ያስችለናል። ሁሉም፣ በተለይም ከጌታ ቤተሰብ መካከል በዕድሜ ልጅ የሆኑት፣ በጥንቃቄ መጠበቅ እንዲችሉ ቤተ ክርስቲያን ልታገኝ የምትችለው በደንብ ያደገ መንፈሳዊ ኃይል ያስፈልጋታል። በቤት ውስጥ የኖሩበት እውነት በውጭ አገርም አድልዎ በሌለበት ሥራ ራሱን ይገልጣል። በቤት ውስጥ ክርስትናን የሚኖር ሰው በሁሉም ቦታ ብሩህና የሚያበራ ብርሃን ይሆናል። --ST, Sept 1, 1898. (AH 38, 39.) {1MCP 176.2}1MCPAmh 144.4

  ሰብአዊ ፍጡራንን ወደ ላይ የማንሳት ራዕይ ቤት ውስጥ ይጀምራል።--ሰብአዊነትን ወደ ቀድሞ ሁኔታ መመለስና ወደ ላይ ከፍ ማድረግ በቤት ውስጥ ይጀምራል። የወላጆች ሥራ ለእያንዳንዱ ሌላ ሥራ መሰረት ነው። ህብረተሰብ የተመሰረተው ከቤተሰቦች ስለሆነ ሊሆን የሚችለው የእነዚህ ቤተቦች ራስ የሆኑት ያደረጉትን ነው። ‹‹የሕይወት መውጫ›› ከልብ ነውና (ምሳሌ 4፡ 23)። --MH 349 (1905). {1MCP 176.3}1MCPAmh 145.1

  ቤትን ውብ የሚያደርጉ ነገሮች።--ጨዋ (ረጋ ያለ) ባሕርይ፣ አስደሳች ንግግርና የፍቅር ተግባራት የልጆችን ልብ ከወላጆቻቸው ልብ ጋር በፍቅር የሀር ገመድ ስለሚያተሳስር በወርቅ ሊገዙ ከሚችሉ ውድ ጌጣጌጦች ይልቅ ቤትን የበለጠ ያስውቡታል። --ST, Oct 2, 1884. (ML 200.) {1MCP 177.1}1MCPAmh 145.2

  በቤት ውስጥ ንጽህና።--ሥርዓት የሰማይ ሕግ ስለሆነ ሕዝቡ የሰማይን አደባባዮች የሞላውን ሥርዓትና መጣጣም በቤቶቻቸው ውስጥ እንዲሰጡ ጌታ ይፈልግባቸዋል። እውነት በረቂቅ የተሰሩ እግሮቿን ንጽህና በጎደለው ወይም ቆሻሻ በሆነ መንገድ ላይ በፍጹም አታደርግም። እውነት ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን በፍጹም ኮስኳሳ ወይም ሸካራ ወይም ቆሻሻ አታደርግም። የሚቀበሉትን ሁሉ ከፍ ወዳለ ደረጃ ታነሳለች። በክርስቶስ ተጽእኖ ሥር የማያቋርጥ የማሳመር (የማሻሻል) ሥራ ይቀጥላል። . . . {1MCP 177.2}1MCPAmh 145.3

  የእሥራኤል ልጆች ለንጽህና ልምዶች ዋጋ እንዲሰጡ በጥንቃቄ የነገረው ዛሬም ቢሆን በሕዝቡ ቤቶች ውስጥ ምንም ዓይነት የንጽህና ጉድለትን አይቀበልም። እግዚአብሔር ማንኛውንም ዓይነት የንጽህና ጉድለት የሚመለከተው በጥላቻ ነው። በቤታችን ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ ንጹህና ጽዱ ካልሆነ በስተቀር እንዴት አድርገን እርሱን ወደ ቤታችን መጋበዝ እንችላለን? --RH, June 10, 1902. (CH 101.) {1MCP 177.3}1MCPAmh 145.4

  ቤት የሚሰራበት ቦታ።--ለልጆቻችሁ ከምታወርሱት ከማንኛውም ሀብት ይልቅ የጤናማ አካል፣ የጤናማ አእምሮና የከበረ ባሕርይ ሥጦታ ይሻላል። የሕይወት እውነተኛ ስኬት ምንን እንደሚያካትት የሚረዱ ሰዎች ወቅቱን የሚያውቁ ጠቢባን ይሆናሉ። ቤትን ሲመርጡ የሕይወትን ከሁሉ የተሻሉ ነገሮች በእይታቸው ውስጥ ያደርጋሉ። {1MCP 177.4}1MCPAmh 145.5

  የሰዎች ሥራ ብቻ በሚታይበት፣ የሚታዩና የሚሰሙ ነገሮች ያለማቋረጥ የክፉ ሀሳቦችን በሚያቀርቡበት፣ ብጥብጥና ውዝግብ ድካምንና ፊት መንሳትን በሚያመጡበት ቦታ ከመኖር ይልቅ የእግዚአብሔርን ሥራ ማየት ወደምትችሉበት ቦታ ሂዱ። በተፈጥሮ ውበት፣ ጸጥታና ሰላም ውስጥ የመንፈስ እረፍትን አግኙ። ዓይን በአሩንጓዴ መስኮች፣ በጥሻዎችና በኮረብታዎች ላይ ይረፍ። በከተሞች አቧራና ጭስ ወዳልተሸፈነ ሰማይ ተመልከቱና የሰማይን ብርታት ሰጭ አየር ተንፍሱ። ትኩረትን ከሚስብና ከንቱ ብክነትን ከሚያስከትል የከተማ ሕይወት በመለየት ከልጆቻችሁ ጋር አብራችሁ መሆን ወደምትችሉበት፣ ስለ እግዚአብሔር በስራዎቹ አማካይነት ልታስተምሩአቸው ወደምትችሉበትና ለሀቀኝነትና ጠቃሚ ለሆነ ሕይወት ልታሰለጥኑአቸው ወደምትችሉበት ቦታ ሂዱ።--MH 366, 367 (1905). {1MCP 177.5}1MCPAmh 146.1

  በጣም ጥሩ የሆነ የቤት ዕቃ ቤትን ቤት አያደርገውም።--ርኅራኄና ፍቅር ከሌለ፣ አራት ግድግዳዎችና ውድ የሆኑ የቤት ዕቃዎች፣ ከፋይ ምንጣፎች፣ ያሸበረቁ መስታወቶችና በጣም ውብ ፎቶግራፎች ቤትን ‹‹ቤት›› አያደርጉትም። የቤተሰብ ሕይወት ደስታ በማይታወቅበት ያሸበረቀ መኖሪያ ውስጥ ያ ቅዱስ ቃል አይገኝም።… {1MCP 178.1}1MCPAmh 146.2

  በርግጥ እንደዚህ ባለ ቤት ውስጥ ከሚታሰቡ ነገሮች መካከል የልጆች ምቾትና ደህንነት የመጨረሻዎቹ ናቸው። አምራ ለመታየትና ፋሽን ተከታይ የሆነ ህብረተሰብን ጥያቄ ለማሟላት ጊዜዋን በሙሉ በሰዋች እናት ችላ ተብለዋል። አእምሮዎቻቸው ሥልጠና ያላገኙ ናቸው፤ መጥፎ ልማዶችን ስለሚያገኙ እረፍት የለሾችና ዕርካታ የሌላቸው ናቸው። በቤቶቻቸው ውስጥ ምቾት ከሚነሱ ዕቀባዎች በቀር ደስታ ስለማያገኙ በተቻለ ፍጥነት ከቤተሰብ ክበብ ራሳቸውን ይለያሉ። የቤት ተጽእኖና በምድጃ ዙሪያ የሚሰጥ የደግነት ምክር ስለማይገድባቸው ያለ አንዳች ማመንታት ታላቁን ዓለም ይቀላቀሉታል። --ST, Oct 2, 1884. (AH 155.) {1MCP 178.2}1MCPAmh 146.3

  ስህተት መፈለግ ለሰይጣን በር ይከፍታል።--አባቶችና እናቶች ሆይ፣ ራሳችሁን ጠብቁ። በቤት ውስጥ ንግግራችሁ ያማረና የሚያበረታታ ይሁን። በክርስቶስ ፊት እንዳላችሁ አድርጋችሁ በመቁጠር ሁል ጊዜ በትህትና ተናገሩ። ስህተት መፈለግና መወንጀል አይኑር። እንደ እነዚህ ያሉ ቃላት ነፍስን ያቆስላሉ ያበልዛሉም። ለሰብአዊ ፍጡራን ኃይለኛ (ጎጂ) ቃላት መናገር ተፈጥሮአዊ ነው። ለዚህ ዝንባሌ የሚሸነፉ ሰዎች ሰይጣን ወደ ልባቸው እንዲገባና የሌሎችን ስህተቶችና ጉድለቶች ለማስታወስ ፈጣን እንዲሆኑ እንዲያደርጋቸው በር ይከፍቱለታል። በውድቀቶቻቸው ላይ ጊዜ ይወስዳሉ፣ ጉድለቶቻቸው በደንብ ይታያሉ፣ ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ ሰራተኛ እንደመሆኑ ተግባሩን ለመፈጸም የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ባለ ሰው ላይ መተማመን እንዳይኖር የሚያደርጉ ቃላት ይወረወራሉ። ብዙ ጊዜ አንድ ግለሰብ ተቀባይነት ማግኘት ሲገባው እንዳላገኘ ስለተሰማው ብቻ እምነት የማጣት (የጥርጣሬ) ዘሮች ይዘራሉ። --Lt 169, 1904. {1MCP 178.3}1MCPAmh 146.4

  የወላጅነት ጉድለቶች ተጽእኖ።--ለአንዳንድ ወንዶች ግልፍተኛና ራስ ወዳድ መሆን፣ የፈለጉትን በኃይል ለማግኘትና ሁል ጊዜ ሌሎችን ለማዘዝ መሞከር በማያሻማ ሁኔታ ተፈጥሮአዊ ይመስላል። ራስን የመቆጣጠርን ትምህርት በፍጹም ተምረው ስለማያውቁው ውጤቶቹ ምንም ቢሆኑ ምክንያታዊ ያልሆኑ ስሜቶቻቸውን አይቆጣጠሩም። እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች ሽልማታቸው ጓደኞቻቸው ታማሚና ተስፋ የቆረጡ ሆነው ማየትና ልጆቻቸው የእነርሱን ደስ የማያሰኙ ልዩ ባሕርያትን ተሸክመው ማየት ነው። --HL (Part 2) 36, 1865. (2SM 430.) {1MCP 179.1}1MCPAmh 147.1

  ግጭት ወዳለበት ቤት መላእክት አይሳቡም።--ጠብ ወደነገሰበት ቤት መላእክት አይሳቡም። እናቶችና አባቶች ስህተት መፈለግንና ማጉረምረምን ሁሉ ያቁሙ። ልጆቻቸው መልካም እና የፀሐይ ብርሃንንና ደስታን የሚያመጡ ቃላትን እንዲናገሩ ያስተምሩአቸው። እንደ ክርስቶስ ተማሪዎች አሁን ወደ ቤት ትምህርት ቤት አንገባምን? በቤት ውስጥ ተግባራዊ የሆነ እግዚአብሔርን መምሰልን አሳዩ። ይህን ስታደርጉ የምትናገሩአቸው ቃላት ደስታን ያመጡ እንደሆን ተመልከቱ። {1MCP 179.2}1MCPAmh 147.2

  ወላጆች ሆይ፣ ልጆቻችሁ ከሰማያዊ መላእክት ጋር እየተባበራችሁ እንደሆነ እንዲያዩ ራሳችሁን እየተቆጣጠራችሁ የቤተ ክርስቲያንን የጸጋ ሥራ በቤታችሁ ውስጥ ጀምሩ። በየቀኑ መለወጣችሁን እርግጠኞች ሁኑ። ራሳችሁንና ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር መንግስት ላለው ዘላለማዊ ሕይወት አሰልጥኑ። መላእክት ብርቱ ረዳቶቻችሁ ይሆናሉ። ሰይጣን ይፈትናችኋል፣ ነገር ግን አትሸነፉ። ጠላት አጋጣሚውን ሊጠቀምበት የሚችለውን አንድ ቃል እንኳን አትናገሩ። --MS 93, 1901. {1MCP 179.3}1MCPAmh 147.3

  በቤት ውስጥ የበለጠ እንግዶችን ለመቀበል የቀረበ ተማጽኖ።--ክርስቲያን ነን በሚሉ ሰዎች መካከል እንኳን እንግዳን መቀበል እየተተገበረ አይደለም። በራሳችን ሕዝብ መካከል እንግዳን ማስተናገድ እንደ መልካም ዕድልና በረከት ተደርጎ ሊሰጠው የሚገበው ቦታ አልተሰጠውም። ማህበራዊ ሕይወት እጅግ አነስተኛ ስለሆነ፣ ሳያፍሩ ወይም ሳይኩራሩ፣ በቤተሰብ ጠረጴዛ ላይ ለተጨማሪ ሁለት ወይም ሶስት ሰዎች ቦታ የመተው ዝንባሌ በፍጹም የለም። አንዳንዶች ‹‹እጅግ ብዙ ችግር›› ይፈጥራል ይላሉ። ‹‹የተለየ ዝግጅት የለንም፣ ግን ያለንን ነገር እንድትካፈሉ እንጋብዛችኋለን›› ብትሉ ኖሮ ችግር አይሆንም ነበር። እጋበዛለሁ ብሎ ያልጠበቀን እንግዳ ወደ ቤታችሁ መጋበዛችሁ ብቻውን እጅግ ሰፊ ዝግጅት አድርጋችሁ ከመጋበዝ የበለጠ አድናቆትን ያገኛል። --6T 343 (1900). {1MCP 179.4}1MCPAmh 147.4

  ቤትን የደስታ ቤት የሚያደርጉ ነገሮች።--ደስ የሚሉ ድምጾች፣ ረጋ ያሉ ባሕርያት፣ እና በሚደረጉ ነገሮች ሁሉ ውስጥ ራሱን የሚያሳይ ልባዊ የሆነ ፍቅር ከትጋት፣ ከንጽህናና ከቁጠባ ጋር ደሳሳ ጎጆን ውብ ከሆኑ ቤቶች የበለጠ ደስታ የሞላበት ያደርገዋል። ፈጣሪ እንዲህ ካለው ቤት ጋር ይስማማል። --ST, Oct 2, 1884. (AH 422.) {1MCP 180.1}1MCPAmh 148.1

  እውነተኛ የሆነ መሻሻልን ማዳበር።--በቤት ውስጥ እውነተኛ የሆነ መሻሸልን የማዳበር ትልቅ አስፈላጊነት አለ። ይህ ለእውነት ኃይለኛ የሆነ ምስክር ነው። የብልግናና የእብደት ቋንቋ መናገር በማንኛውም መልክ ቢገለጽ የተበላሸ ልብን ያመለክታል። መነሻው ሰማይ የሆነ እውነት ተቀባዩን በፍጹም አያዋርደውም፣ ኮስኳሳ ወይም ሸካራ አያደርገውም። እውነት የሚያሳድረው ተጽእኖ የሚያለሰልስና የሚያነጻ ነው። በልብ ውስጥ ተቀባይነትን ሲያገኝ ወጣቶችን አክባሪና ትሁት ያደርጋቸዋል። የክርስቲያን ትህትናን መቀበል የሚቻለው በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ብቻ ነው። ማስመሰል ወይም እውነተኛ ያልሆነ ማብረቅረቅ፣ እጅ መንሳትና የሽርደዳ ፈገግታ ማሳየት ትህትናን አያመለክትም። ይህ ዓለማውያን በሆኑ ሰዎች ዘንድ ያለ ትህትና ሲሆን እውነተኛ የሆነ የክርስቲያን ትህትና የሌለው ነው። {1MCP 180.2}1MCPAmh 148.2

  እውነተኛ መሻሻል፣ እውነተኛ ትህትና የሚገኘው ከክርስቶስ ወንጌል ተግባራዊ እውቀት ነው። እውነተኛ ትህትና፣ እውነተኛ የሆነ የታረመ ጸባይ የሚባለው ከፍተኛ ወይም ዝቅተኛ፣ ሀብታም ወይም ደሀ ሳይል ለሁሉም የሚታይ ደግነት ነው። --MS 74, 1900. (AH 422, 423.) {1MCP 180.3}1MCPAmh 148.3

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents