Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 22—ትምህርት ቤትና መምህር

    የአእምሮ ኃይሎችን ማንቃት።--እውነተኛ ትምህርት ባልተዘጋጀና በማይቀበል አእምሮ ውስጥ ትምህርት እንዲገባ ማስገደድ አይደለም። የአእምሮ ኃይሎች መንቃትና ፍላጎት መነሳሳት አለበት። ለዚህ የእግዚአብሔር የማስተማር ዘዴ ተሰጥቶናል። አእምሮን የፈጠረውና ሕጎቹን ያስቀመጠው በሕጎቹ መሰረት ለእድገቱ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ሰጠ። {1MCP 187.1}1MCPAmh 154.1

    በቤትና በቤተ መቅደስ፣ በተፈጥሮና በኪነ-ጥበብ ነገሮች፣ በሥራና በዓል በማክበር፣ በቅዱስ ሕንጻና በመታሰቢያ ድንጋይ፣ በዘዴዎችና በሥርዓቶች እንዲሁም ሊቆጠሩ በማይችሉ ምልክቶች፣ እግዚአብሔር ለእሥራኤል መርሆዎቹን በመግለጽና አስደናቂ የሆኑ ሥራዎቹን መታሰቢያ በመጠበቅ ትምህርቶችን ሰጣቸው። በዚያን ጊዜ፣ ጥያቄ ሲነሳ፣ የተሰጠው ትምህርት አእምሮንና ልብን ማረከ።--Ed 41 (1903). {1MCP 187.2}1MCPAmh 154.2

    ትምህርት ሕይወት ሰጭ ጉልበት ለመስጠት።--የትምህርት ከፍተኛው ሥራ ዝም ብሎ እውቀት ብቻ ማጋራት ሳይሆን አእምሮ ከአእምሮ ጋርና ነፍስ ከነፍስ ጋር ግንኙነት ሲፈጥሩ የሚገኘውን ሕይወት ሰጭ ጉልበት ማጋራት ነው። ሕይወትን የሚወልድ ሕይወት ብቻ ነው። --DA 250 (1898). {1MCP 187.3}1MCPAmh 154.3

    የአእምሮ ኃይሎች ከፍተኛ እድገት።--ወጣቶች የአእምሮ ኃይላቸው ወደ ከፍተኛ የእድገት ደረጃ መድረስ እንዳለባቸው ቢሰማቸው ልክ ነው። እግዚአብሔር ገደብ ያላበጀለትን ትምህርት እኛ አንገድብም። ነገር ግን ስኬቶቻችን ለእግዚአብሔር ክብርና ለሰብአዊ ዘር ጥቅም ካልዋሉ ምንም ዋጋ የላቸውም። በተግባራዊ ሕይወት ውስጥ ጥቅም ላይ በማይውሉ ግን ኃይለኛ ተግባርን በሚፈልጉ ትምህርቶች አእምሮን ማጨናነቅ መልካም አይደለም። --MH 449, 450 (1905). {1MCP 187.4}1MCPAmh 154.4

    የአንዳንድ ትምህርት ቤቶች እገዳዎች።--ብዙ ወጣቶች ከትምህርት ተቋማት ግብረገባቸው ዝቅ ብሎና አካላዊ ኃይሎቻቸው ደክመው ለተግባራዊ ሕይወት የሚሆን እውቀት ሳያገኙና ተግባሮቹን ለማከናወን ኃይላቸው ተንጠፍጥፎ ይወጣሉ። {1MCP 188.1}1MCPAmh 154.5

    እነዚህን ክፋቶች ሳይ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን በትምህርት ቤቶች ውስጥ ትምህርት ለማግኘት ሲባል በሞራልና በአካል ደካሞች መሆን አለባቸውን? ይህ መሆን የለበትም፣ መምህራንና ተማሪዎች የእግዚአብሔር ሕግጋት ለሆኑ ለተፈጥሮ ሕጎች ታማኞች ቢሆኑ ኖሮ እንዲህ መሆን አያስፈልግም ነበር። ወጣቶች ጠንካራና ሚዛናዊ የሆኑ ወንዶችና ሴቶች እንዲሆኑ ሁሉም የአእምሮና የአካል ኃይሎች ንቁ ወደሆነ እንቅስቃሴ መግባት አለባቸው። --ST, June 29, 1882. (FE 71.) {1MCP 188.2}1MCPAmh 154.6

    ለትምህርት ጥበቃ ሊደረግ ይገባል።--አእምሮ ከሚመገበው ነገር ጋር ተመሳሳይ ባሕርይ፣ መከሩ ከተዘራው ዘር ጋር ተመሳሳይ ተፈጥሮ ይኖረዋል። የወጣቶችን ትምህርት ከልጅነት ዕድሜያቸው ጀምሮ የመጠበቅን አስፈላጊነት እነዚህ እውነታዎች በበቂ ሁኔታ አያሳዩምን? ወጣቶች የእግዚአብሔርን እውነት በተመለከተ ግድ የለሽ ከሚሆኑ ይልቅ በተለምዶ ትምህርት ተብሎ ተቀባይነት ላገኘው ትምህርት እውቀት የለሽ ሆነው ማደግ አይሻልምን? --6T 194 (1900). {1MCP 188.3}1MCPAmh 155.1

    እግዚአብሔር ከሰው ጋር ያለው ግንኙነት ግልጽ ሊሆን ነው።-- እግዚአብሔር የማገናዘብ ኃይልን ለሰጠው ለእያንዳንዱ ሰብአዊ ፍጡር ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት ማስተዋል ከፍተኛ ጠቃሜታ አለው። በእያንዳንዱ እርምጃ ይህ የእግዚአብሔር መንገድ ነውን? በማለት መጠየቅ ለጠያቂው ለአሁንም ሆነ ለዘላለም መልካም ነው…። እያንዳንዱ ሰብአዊ ፍጡር የራሱን ባሕርይ ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር፣ ወደ መንግስቱ ለሚገቡና የሰማያዊው አገር ዜጎች ለሚሆኑ ሁሉ የባሕርይ መስፈርት ከሆነው ሕግ ጋር፣ እንዲያነጻጽር ልባዊ ጥሪ ልናቀርብ እንፈልጋለን። --MS 67, 1898. {1MCP 188.4}1MCPAmh 155.2

    ከሁሉ የሚበልጥ ትምህርት።--ንጹህ፣ የተሟላና ተለዋዋጭ ያልሆነ ክርስቲያናዊ ሕይወት ሳይንስ የሚገኘው የእግዚአብሔርን ቃል በማጥናት ነው። ይህ ማንኛውም ምድራዊ ፍጡር ሊያገኘው የሚችል ከሁሉም የሚበልጥ ትምህርት ነው። በትምህርት ቤቶቻችን ያሉ ተማሪዎች በእድገት መሰላል ላይ ለመውጣት፣ የክርስቲያንን መልካም ባሕርያት ለመለማመድ ተዘጋጅተው በንጹህ አስተሳሰብ፣ አእምሮና ልብ መውጣት እንዲችሉ ሊማሩት የሚገባው ትምህርት ይህ ነው። --MS 86, 1905. {1MCP 189.1}1MCPAmh 155.3

    የመምህር ልምዶች ተጽእኖ ያሳድራሉ።--የመምህር ልምዶችና መርሆዎች ከሥነ-ጽሁፍ ብቃቱ ይልቅ ትልቅ ጠቃሜታ እንዳላቸው መገንዘብ ያስፈልጋል። መምህሩ እውነተኛ ክርስቲያን ከሆነ፣ ከሌላው ትምህርት ጋር እኩል በሆነ መልኩ ተማሪዎቹ አካላዊ፣ አእምሮአዊ፣ መንፈሳዊና ግብረ ገባዊ ትምህርት ማግኘት አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማዋል። ትክክለኛ የሆነ ተጽእኖ ማሳደር እንዲችል በራሱ ላይ ፍጹም ቁጥጥር ሊኖረው ይገባል፣ ልቡ በአስተያየቱ፣ በቃላቱና በተግባሮቹ ሊታይ በሚችልበት መልኩ በተማሪዎቹ ፍቅር በደንብ መሞላት አለበት። የባሕርይ ጽናት ሊኖረው ይገባል፤ እንዲህ ሲሆን የተማሪዎቹን አእምሮ መቅረጽ ይችላል፣ ሳይንሶቹንም ሊያስተምራቸው ይችላል። {1MCP 189.2}1MCPAmh 155.4

    ወጣቶች በልጅነት ዕድሜያቸው የሚማሩት ትምህርት በአጠቃላይ ለሕይወት ዘመናቸው ባሕርያቸውን ይቀርጻል። ከልጆች ጋር የሚሰሩ ሰዎች የተማሪዎቻቸውን የአእምሮ ኃይሎች እንዴት እንደሚመሩና ከሁሉ በተሻለ ሥራ ላይ እንዴት እንደሚያውሉ ለማወቅ የአእምሮ ክህሎቶችን ሥራ ላይ በሚያውሉበት ሁኔታ በጣም ጥንቁቆች መሆን አለባቸው። --RH, July 14, 1885. {1MCP 189.3}1MCPAmh 156.1

    ከፍ ያሉ የአእምሮ ችሎታዎችን ተግባር ላይ ማዋል።--የወጣቶችን ትምህርት በተመለከተ ከፍ ያሉና የከበሩ የአእምሮ ኃይሎችን ተግባር ላይ ማዋል እንዲቻል የማስተማሪያ ዘዴን የተለየ ለማድረግ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። ወላጆችና በትምህርት ቤት ያሉ መምህራን በመጀመሪያ ራስን የመቆጣጠርን፣ የትዕግስትን፣ የመቻልን፣ የጨዋነትንና የፍቅርን ትምህርቶች ካልተማሩ በቀር በእርግጠኝነት ልጆችን ለማስተማር ብቁ አይደሉም። ለወላጆች፣ አሳዳጊዎችና መምህራን እንዴት ያለ ጠቃሚ ኃላፊነት ነው! እጅግ ጠቃሚ የሆኑ የአእምሮ ፍላጎቶችንና በማደግ ላይ ያለ የአእምሮ ችሎታን፣ እያደጉ ያሉ የወጣቶችን ሀሳቦችና ስሜቶች፣ እንዴት መምራት እንደሚቻል የሚገነዘቡ በጣም ጥቂቶች ናቸው። --RH, July 14, 1885. {1MCP 189.4}1MCPAmh 156.2

    በመንፈስ ቅዱስ መነሳሳት።--ከሰብአዊ አእምሮዎች ጋር መሥራት ከማንኛውም ሥራ ይልቅ እጅግ ጥንቃቄ የሚፈልግ ሥራ ስለሆነ መምህራን ሥራቸውን በትክክል መሥራት እንዲችሉ በመንፈስ ቅዱስ መነሳሳት አለባቸው።--MS 8, 1899. {1MCP 190.1}1MCPAmh 156.3

    የተሳሳተ/የተንኮል ሥራን መቋቋም።--የሌሎች ሰዎችን ስህተቶች ማጋለጥን እንደ መልካም ሥራ አድርገው ሊወስዱ ስለሚችሉ የማንኛውንም ተማሪ ስህተቶችና የተንኮል ሥራዎችን በሕዝብ ፊት እያስተዋወቃችሁ በፍጹም አታስተምሩአቸው። የአንድን ተማሪ ቅሬታዎች፣ ስህተቶችና ኃጢአቶች በትምህርት ቤት ፊት እያቀረባችሁ በፍጹም አታዋርዱት፡- ይህን በማድረጋችሁ ልቡን እንዲያደነድንና በክፋቱ እንዲጸና ታደርጉታላችሁ። ከእርሱ ጋር ለብቻው አብራችሁ ተነጋገሩና ጸልዩ፣ መምህራን ለሆናችሁ ለእናንተ ክርስቶስ ያሳያችሁን ያንኑ ገርነት አሳዩ። ማንኛውም ተማሪ ሌላኛውን ተማሪ እንዲተችና ስለ ስህተቶቹ እንዲናገር በፍጹም አታደፋፍሩ። እርሱን ለመፈወስ የክርስቶስን መንገድ በመከተል በተቻለ መጠን የኃጢአትን ብዛት ሸፍኑ። --MS 34, 1893. {1MCP 190.2}1MCPAmh 156.4

    ከሰብአዊ አእምሮዎች ጋር ለመስራት ሙሉ በሙሉ ብቁ መሆን።--እያንዳንዱ መምህር ለክርስቶስ ሲል ክርስቶስ በእምነት በልቡ ውስጥ እንዲያድርና እውነተኛ የሆነ፣ ራስን የካደ፣ ራስን መስዋዕት ያደረገ መንፈስ እንዲኖረው መሻት አለበት። አንድ ሰው ለማስተማር የሚያስችለው በቂ የሆነ ትምህርትና የሳይንስ እውቀት ሊኖረው ይችላል፣ ነገር ግን ከሰብአዊ አእምሮዎች ጋር ለመስራት ብልሃትና ጥበብ እንዳለው ተረጋግጦአልን? መምህራን በልባቸው ውስጥ የክርስቶስ ፍቅር የማይኖር ከሆነ ከልጆች ጋር ግንኙነት ለመፍጠርና እነዚህን ልጆችና ወጣቶች እንዲያስተምሩ በላያቸው የተጣለውን ከባድ ኃላፊነት ለመሸከም ገጣሚዎች አይደሉም። በውስጣቸው ከፍተኛ የሆነ ትምህርትና ስልጠና ስለሌለ ከሰብአዊ አእምሮ ጋር እንዴት መስራት እንዳለባቸው አያውቁም። በቀላሉ ቅርጽ ሊይዙ የሚችሉ የልጆችን አእምሮዎችና ባሕርያት ለመቆጣጠርና ለመግዛት ጥረት የሚያደርግ የራሳቸው የማይገዛ፣ ተፈጥሮአዊ ልብ መንፈስ ስላለ እንዲህ ዓይነቱ ትምህርት በአእምሮ ውስጥ በፍጹም ሊፋቁ የማይችሉ ሰንበሮችንና ጠባሳዎችን ትቶ ያልፋል። {1MCP 190.3}1MCPAmh 156.5

    መምህር ከሰብአዊ አእምሮ ጋር በሚሰራበት ጊዜ ኃላፊነት እንዳለበትና ጥንቁቅ መሆን እንዳለበት እንዲሰማው ካልተደረገ በቀር የእርሱ ትምህርት በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ጉድለት ያለበት ነው። በቤት ሕይወቱ የነበረው ስልጠና ባሕርይን የሚጎዳ ስለነበር ይህን ጉድለት ያለበትን ባሕርይና አያያዝ በእርሱ ቁጥጥር ሥር ባሉ ልጆች ውስጥ ማባዛት አሳዛኝ ነገር ነው። --CEd 145, 1893. (FE 260, 261.) {1MCP 191.1}1MCPAmh 157.1

    ልምድ ለሌላቸው ኃላፊነቶች አይሰጡም።--በባትል ክሪክ ያለው የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤት እንክብካቤ ሊደረግለት ከሚገባው የእግዚአብሔር የወይን ቦታ አንዱ አስፈላጊ ክፍል ነው። በእያንዳንዱ ዘርፍ የሚያስተምሩ መምህራን ሚዛናዊ የሆነ አእምሮና የተስተካከለ ባሕርይ እንዲኖራቸው ይጠበቅባቸዋል። ይህን ሥራ ከሰው አእምሮ ጋር እንዴት መስራት እንዳለባቸው በማያውቁ ወጣት ወንዶችና ሴቶች እጅ አሳልፋችሁ አትስጡ። ይህ ስህተት ስለነበር በእነዚህ ኃላፊነት ስር በሆኑ ልጆችና ወጣቶች ላይ ክፉ ነገር አምጥቶባቸዋል።. . . {1MCP 191.2}1MCPAmh 157.2

    በልጆችና በወጣቶች ውስጥ መሰራት ያለባቸው ሁሉም ዓይነት ባሕርያት አሉ። አእምሮዎቻቸው ሊቀረጹ የሚችሉ ናቸው። በመምህርቷ በኩል እንደ ችኮላና በጠንካራ ስሜት በቀላሉ መሸነፍን የሚመስሉ ነገሮችን ማሳየት አስተምራለሁ በምትላቸው ተማሪዎች ላይ ለመልካም ያላትን ተጽእኖ ያቋርጣል። ይህ ትምህርት ለልጆቹና ለወጣቶቹ በአሁኑ ሕይወት መልካም እንዲሆንላቸውና ለወደፊቱ የዘላለም ሕይወት የሚጠቅም ይሆናልን? ለእነርሱ መንፈሳዊ ሕይወት ስምረት ልናሳድርባቸው የሚገባ ትክክለኛ ተጽእኖ አለ። --MS 34, 1893. {1MCP 191.3}1MCPAmh 157.3

    ቁጡ (ግልፍተኛ) ለሆነ መምህር የተሰጠ ምክር።--ሰይጣን ባልተቀደሱ የባሕርይ መገለጫዎቹ አማካይነት እንደ ወኪሉ አድርጎ ነፍሳትን ለማጥፋት እንዳይጠቀም እያንዳንዱ መምህር ነቅቶ መጠበቅ ያለበት የራሱ የሆነ ልዩ የባሕርይ መገለጫ አለው። ለመምህራን ያለው ብቸኛው ደህንነት በክርስቶስ ትምህርት ቤት በየዕለቱ የእርሱን የዋህነትና የልብ ትህትና መማር ነው፤ ያኔ ራስ በክርስቶስ ይደበቅና በየዋህነት የክርስቶስን ቀንበር በመጫን በእርሱ ርስት እየሰራ እንደሆነ ይሰማዋል። {1MCP 191.4}1MCPAmh 158.1

    ከተማሪዎች ስህተቶችና ጥፋቶች ጋር ሲሰራ ሁል ጊዜ የተሻሉ ዘዴዎች ሥራ ላይ እንዳልዋሉ እንዳይ እንደተደረግሁ መናገር አለብኝ፤ ውጤቱም የነፍሳት ለአደጋ መጋለጥና የአንዳንዶች መጥፋት ነው። በመምህራን ውስጥ ያሉ ክፉ ንዴቶች፣ ጥበብ የጎደላቸው እንቅስቃሴዎች፣ የራስ ክብር መጠበቅ ክፉ ሥራ ሰርቷል። በእግዚአብሔር መንፈስ ቁጥጥር ሥር ካልሆነ ከሰብአዊ የንዴት ስሜት በበለጠ ሁኔታ ነፍስን መራር በማድረግና መልካም እንዲናቅ የሚያደርጉ ክፋቶችን በመደርደር በባሕርይ ላይ ሰይጣናዊ ሥራ የሚሰራ ክፋት፣ ዓለማዊነት ወይም ሰካራምነት የለም። ቁጣ፣ መነካት [መቀስቀስ]፣ መነሳሳት፣ በፍጹም ዋጋ አይኖራቸውም። {1MCP 192.1}1MCPAmh 158.2

    ክርስቲያን ነን ከሚሉ ሰዎች የግድ የለሽነት ባህርይ የተነሣ ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንዳይገቡ ተከልክለው ያሉ ኮብላይ ልጆች ምንኛ ብዙ ናቸው። ቅንዓት፣ ምቀኝነት፣ ኩራት፣ የልግስና ስሜት አለመኖር፣ የራስ ጽድቅ፣ በቀላሉ መናደድ፣ ክፉ ማሳብ፣ ጭካኔ፣ የፍቅር መጥፋት፣ ርኅራኄ አለመኖር--እነዚህ የሰይጣን ባህርያት ናቸው። መምህራን በተማሪዎች ባሕርይ ውስጥ እነዚህን ነገሮች ይጋፈጣሉ። ከእነዚህ ነገሮች ጋር መጋፈጥ አስቸጋሪ ነው፤ ነገር ግን ሰራተኛው እነዚህን ክፋቶች ለማስወገድ እየፈለገ ሳለ እርሱ ራሱ በብዙ አጋጣሚዎች ሊረዳቸው እየሞከረ ያሉ ተማሪዎችን ነፍስ ያበላሹ ተመሳሳይ ባሕርያትን አጎልብቷል። --Lt 50, 1893. {1MCP 192.2}1MCPAmh 158.3

    ሚዛናዊ የሆነ አእምሮ ያስፈልጋቸዋል።--በጌታ የወይን ቦታ በዚህኛው ክፍል የሚሰሩ መምህራን ራሳቸውን የሚገዙ፣ ቁጣቸውንና ስሜቶቻቸውን የሚቆጣጠሩና ለመንፈስ ቅዱስ የሚያስገዙ መሆን አለባቸው። ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ልምምድ ሳይሆን ሚዛናዊ የሆነ፣ የተስተካከለ ባሕርይ ያላቸው ለመሆናቸው ማረጋገጫ መስጠት አለባቸው። --CT 191 (1913). {1MCP 192.3}1MCPAmh 158.4

    ለመሻሻል ቁርጠኝነት አስፈላጊ ነው።--መምህር የሚፈለገውን ያህል ከፍተኛ የሆኑ የትምህርት ብቃቶችን እንዳያገኝ ዕድሎች ተገድበውበት ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ስለ ሰብአዊ ተፈጥሮ እውነተኛ ግንዛቤ ቢኖረው ኖሮ፣ ስለ ሥራው ትክክለኛ የሆነ ፍቅር፣ ሥራው ስላለው ስፋት አድናቆትና ለማሻሻል ቁርጠኝነት ቢኖረው ኖሮ፣ በትጋትና በትዕግሥት ለመስራት ፈቃደኛ ቢሆን ኖሮ፣ የተማሪዎቹን ፍላጎት በመረዳት ርኅራኄ ባለውና እድገትን በሚቀበል መንፈስ እርሱ ሊመራቸው በሚፈልገው ሁኔታ ወደ ፊትና ወደ ላይ ለመጓዝ እንዲከተሉት ያነሳሳቸዋል። --Ed 279 (1913). {1MCP 192.4}1MCPAmh 158.5

    የአእምሮ ኃይሎች ግማሹም ጥቅም ላይ አልዋለም።--የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና አካዳሚዎች መኖር አስፈላጊ ነው።…በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች የሰራተኞችን ፍላጎት የሚገልጹ ብዙ አስቸኳይ ጥሪዎች እየመጡ ናቸው። ወጣት ወንዶችና ሴቶች፣ በመካከለኛ የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎች እና በጌታ አገልግሎት ላይ መሰማራት የሚችሉ ሰዎች ሁሉ ለእነዚህ ጥሪዎች ምላሽ ለመስጠት ለመዘጋጀት ጥረት በማድረግ አእምሮአቸውን አንድ ማድረግ አለባቸው። እግዚአብሔር ከሰጠኝ ብርሃን፣ ራሳችንን ለተሻለ ሥራ ገጣሚ ለማድረግ በምናደረገው ጥረት የአእምሮ ኃይሎቻችንን መጠቀም ከሚገባን መጠን ግማሹን እንኳን በትጋት እየተጠቀምን እንዳልሆነ አውቃለሁ። --CT 209 (1903). {1MCP 193.1}1MCPAmh 159.1

    ተፈጥሮአዊውን ከመንፈሳዊው ጋር አዋህዱና ከፍ ወዳሉ ስኬቶች ድረሱ።--በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ በሚሰጡ ትምህርቶች ውስጥ ተፈጥሮአዊውና መንፈሳዊው መዋሃድ አለባቸው። የእርሻ ሥራዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርቶች የሚገልጹ ናቸው። ምድር የምትታዘዛቸው ሕጎች ገደብ የለሽ በሆነው በእግዚአብሔር ሁሉን በሚቆጣጠር ኃይል ሥር የመሆኑን እውነታ ይገልጣሉ። እነዚሁ መርሆዎች በመንፈሳዊውና በተፈጥሮአዊው ዓለም ውስጥ ይሰራሉ። እግዚአብሔርንና የእርሱን ጥበብ እውቀት የማግኘት ሂደት በፊታችሁ ሽባ ከሆነ፣ ወደ አንድ ጎን ካጋደለ፣ ሰው በክርስቶስ በማመን ዘላለማዊነትን ማግኘት እንዳይችል በማድረግ ለሰው ኃይል የሚሰጡ የማዳን ችሎታዎችን ሙት የሚያደርግ ትምህርት ይኖራችኋል። የተፈጥሮ ደራሲ የመጽሐፍ ቅዱስም ደራሲ ነው። ፍጥረትና ክርስትና አንድ አምላክ አላቸው። {1MCP 193.2}1MCPAmh 159.2

    እውቀትን በማግኘት ተግባር ላይ የሚሰማሩ ሰዎች ሁሉ በእድገት መሰላል ላይ ከፍተኛው ደረጃ ላይ ለመድረስ ማለም አለባቸው። በተቻላቸው ፍጥነት እስከሚችሉት ርቀት ድረስ ወደ ፊት መቀጠል አለባቸው፤ ለዘመናት ተደብቀው የቆዩ ምስጢሮችን መግለጥ በሚችል፣ ብቻውን በማይሞት በእርሱ ለሚያምኑ አእምሮዎች እጅግ በጣም ከባድ የሆኑ ችግሮችን ማቃለል በሚችል፣ ገደብ የለሽ እውቀት ባለው በእርሱ ላይ በመጣበቅ፣ ማንኛውም ሰው ሊቀርብ በማይችል ብርሃን ውስጥ የሚኖረውን እግዚአብሔርን ጥበባቸው በማድረግ፣ የሚማሩት የትምህርት መስክ ኃይላቸው ሊያካትት እስከሚችል ድረስ ሰፊ ይሁን። የክርስቶስ ህያው ምስክር፣ ጌታን ለማወቅ በመከተል፣ አወጣጡ እንደ ማለዳ የተዘጋጀ መሆኑን ያውቃል። ‹‹ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል›› (ገላትያ 6፡ 7)። በታማኝነትና ተግቶ በመስራት፣ ለአካል ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ከማድረግ ጋር፣ በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ እውቀትና ጥበብ ለማግኘት እያንዳንዱን የአእምሮ ኃይል በመጠቀም፣ የተሟላ ሰው ፍጹም ምሳሌ በሆነው በክርስቶስ እያንዳንዱ ነፍስ የተሟላ ይሆናል። --SpTEd April 22, 1895. (FE 375, 376.) {1MCP 193.3}1MCPAmh 159.3

    የእግዚአብሔርን ቃል እውነት የማያውቁ አእምሮዎችን ትክክለኛ የሆኑ ትምህርቶች ሊስቡ አይችሉም።--ነገር ግን የወደቀው ሰብአዊ ዘር አያስተውልም። የተፈጥሮ ሳይንስ የተፈጥሮን አምላክ መቆጣጠር እንዳለበት ያስባል። እውነትን ወይም የእግዚአብሔርን ቃል የማያውቁ አእምሮዎችን ትክክለኛ የሆኑ ትምህርቶች ሊስቡ አይችሉም። ልብና አእምሮ ለእግዚአብሔር አልፈው ሲሰጡ፣ ሰው እንደ ትንሽ ህጻን ለመማር ፈቃደኛ ሲሆን፣ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የትምህርት ሳይንስ ይገኛል። የዓለም ከፍተኛ ትምህርት ቧልት መሆኑ ተረጋግጦአል። መምህራንና ተማሪዎች ከከፍታቸው ሲወርዱና ከእርሱ ለመማር ወደ ክርስቶስ ትምህርት ቤት ሲገቡ፣ ሰዎች የሳይንስን ፍሬ ነገር እንዲያውቁ የሚያስችላቸው የከፍተኛ ትምህርት እውቀት መሆኑን ስለሚገነዘቡ ስለዚህ ትምህርት አስተውለው ይናገራሉ።--MS 45, 1898. {1MCP 194.1}1MCPAmh 160.1

    የሚታዩ የትምህርት መርጃዎች ያስፈልጋሉ።--ተጨባጭ የሆኑ ትምህርቶችን፣ ጥቁር ሰሌዳዎችን፣ ካርታዎችንና ፎቶዎችን መጠቀም እነዚህን [መንፈሳዊ] ትምህርቶች ለማስረዳትና በአእምሮአቸው ውስጥ እንዲይዙት ለማድረግ እንደ መርጃ መሳሪያ ያገለግላሉ። ወላጆችና መምህራን ሁልጊዜ የተሻሻሉ ዘዴዎችን መፈለግ አለባቸው። --Ed 186 (1903). {1MCP 194.2}1MCPAmh 160.2

    ከመጠን ያለፈ የተለያየ ዓይነት የአእምሮ ምግብን አትስጡ።--እግዚአብሔር የአእምሮ ኃይሎችን ንጹህና ጽዱ ሆነው እንዲጠበቁ ይፈልጋል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ከመጠን ያለፈ የተለያየ ዓይነት ምግብ ለአእምሮ ይሰጣል። ነገር ግን ለዚህ ትምህርት ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ማድረግና መጠቀም አይቻልም። አእምሮ አስፈላጊ ካልሆነ ሸክም ሁሉ ማረፍ አለበት። ወደ ዘላለም የሚሻገሩ ትምህርቶች፣ እዚህ ብቻ ሳይሆን በመጪው ሕይወትም ከፍተኛ ጥቅም ያላቸው፣ ለአካልና ለነፍስ ከሁሉ የተሻለ ትምህርት የሚሰጡ ትምህርቶች ናቸው። --MS 15, 1898. {1MCP 194.3}1MCPAmh 160.3

    ትምህርትና ተግባራዊ ሕይወት።--በተግባራዊው ሕይወት ውስጥ ጥቅም ላይ በማይውሉ ግን ጥልቅ የሆነ ጥናትን በሚፈልጉና በሚያለፉ የትምህርት ዓይነቶች አእምሮን ማጨናነቅ ጥሩ አይደለም። የዚህ ዓይነት ትምህርት ለተማሪው ኪሳራ ነው፤ ይህ የሚሆንበት ምክንያት እነዚህ ትምህርቶች ጠቃሚ ለሆነ ሕይወት ገጣሚ እንዲሆን ለሚያደርጉት እና የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ በቃልና በሕይወት ምሳሌነት መርዳት ላለበት ሰው ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ እንዲሰራ የተሰጡትን ሀላፊነቶች እንዲፈጽም ለሚያስችሉት ትምህርቶች ያለውን ፍላጎትና ዝንባሌ ስለሚያስወግዱ ነው። --MS 15, 1898. {1MCP 195.1}1MCPAmh 161.1

    ተግባራዊ ለሆነ ስልጠና ያለው ፍላጎት።--የላቲንና የግሪክ ጥናት፣ መላው ሰብአዊ አካልን በደንብ ከማጥናት ጋር ሲነጻጸር፣ ለራሳችን፣ ለዓለም እና ለእግዚአብሔር ያለው ፈይዳ እጅግ አነስተኛ ነው። በተግባራዊ ሕይወት ውስጥ ጠቃሚዎች እንድንሆን ከሚያደርጉን የተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ጋር መተዋወቅን ችላ በማለት መጻሕፍትን ማጥናት ኃጢአት ነው። ለአንዳንዶች መጽሐፍትን በቅርበት ማንበብ ከንቱ ሕይወት መምራት ነው። የአካል ሥራን አለመስራት አእምሮ እጅግ ብዙ በሆነ ስራ ላይ እንዲጠመድ ወደ ማድረግ ይመራል። ይህ የሰይጣን የሥራ ቦታ ይሆናል። ስለምንኖርበት ቤት እውቀት የሌለው ሕይወት በፍጹም ሁለንተናዊ ሕይወት ሊሆን አይችልም። --Lt 103, 1897. {1MCP 195.2}1MCPAmh 161.2

    የክፍል መማሪያ መጻሕፍትና የሀሳብ ንድፎች። [ምዕራፍ 13 ላይ ‹‹የአእምሮ ምግብ›› የሚለውን ርዕስ ይመልከቱ።]--ተናጋሪው ግርማ ሞገስ ባለው ድምጽ እንዲህ በማለት ቀጠለ፡- ‹‹በእነዚህ መናፍቅ በሆኑ ደራሲዎች ዘንድ እውነተኛ ለሆነ ከፍተኛ ትምህርት አስፈላጊ ነው ብለህ ሰዎች እንዲያነቡት አስተያየት የምትሰጥበትን ነገር ታገኛለህን? የእነርሱን እውነተኛ ባሕርይ የማያውቁ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲያጠኑት ሀሳብ ትሰጣለህን? ስህተት የሆኑ የአስተሳሰብ ልምዶች፣ አንድ ጊዜ ተቀባይነት ካገኙ፣ አእምሮን በብረት የእጅ መዳፍ ውስጥ የሚያደርጉ አምባገነን ኃይል ይሆናሉ። እነዚህን መጻሕፍት የተቀበሉና ያነበቡ በርካታ ሰዎች በፍጹም ባያዩአቸውና በእነርሱ ፈንታ የመለኮታዊ መምህርን ቃላት ተቀብለው ቢሆን ኖሮ ሰዎችን ለድነት ጠቢባን በሚያደርጉ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ባሉ መለኮታዊ እውነቶች እውቀት እጅግ ልቀው ይገኙ ነበር። እነዚህ መጻሕፍት በሺሆች የሚቆጠሩትን ሰይጣን አዳምንና ሔዋንን ወደ መራበት--እግዚአብሔር እንዳያውቁት ወደከለከላቸው እውቀት-- መርተዋቸዋል። በአስተምሮዎቻቸው አማካይነት ተማሪዎች የእግዚአብሔርን ቃል በመተው ወደ ተረት ዞረዋል።›› --RH, Mar 12, 1908. {1MCP 195.3}1MCPAmh 161.3

    ሰፊ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ መርሆዎች ጽንሰ-ሀሳቦችን መቆጣጠር አለባቸው። [ምዕራፍ 11 ላይ ‹‹የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና አእምሮ›› የሚለውን ክፍል ያንብቡ።]--አእምሮ የመለኮታዊ መገለጥን እውነቶች ለማወቅ ካልተማረ እና ልብ የክርስቶስን ወንጌል አስተምህሮዎች ካልተቀበለ በቀር ትምህርት ግቡን ያልመታ መሆኑ በእያንዳንዱ ተማሪ አእምሮ ውስጥ መስረጽ አለበት። ሰፊ በሆኑ የእግዚአብሔር ቃል መርሆዎች ቦታ ተራ ሀሳቦችን የሚቀበልና ጊዜና ሀሳብ ተራ በሆኑ፣ በማይጠቅሙ ነገሮች ላይ እንዲውል የሚያደርግ ተማሪ አእምሮው ቀጭጮና ደካማ ሆኖ ያገኘዋል፤ የእድገት ኃይልን ያጣል። አእምሮ የዘላለም ሕይወትን የሚመለክቱ ጠቃሚ እውነቶችን እንዲረዳ መሰልጠን አለበት። --Lt 64, 1909. {1MCP 196.1}1MCPAmh 162.1

    ሰብአዊ ፋብሪካን (አካልን) የሚመሰርቱ ክፍሎችን በተሻለ ሁኔታ መጠቀም።--መምህራን ጌታ እንዲማሩት የሚፈልግባቸውን ትምህርቶች እየተማሩ ቆይተው ቢሆን ኖሮ ሂሳቡ በሆነ ሰው የሚከፈል ወይም ከባድ ዕዳ ተሸክመው ከኮሌጅ የሚወጡ ተማሪዎች አይኖሩም ነበር። ወጣት የሆነ ሰው የሚጠበቅበትን ነገር ለመክፈል ገንዘብ ለማግኘት ሳይፈልግ ብዙ አመታትን መጻሕፍትን ለማጥናት ጊዜውን እንደሚሰዋ መምህራን እያወቁ ምንም ሳያደርጉ ሲቀሩ ከሥራቸው ግማሹን እንኳን እየሰሩ አይደሉም። እያንዳንዱ ጉዳይ መመርመር አለበት፣ እያንዳንዱ ወጣት በትህትናና ፍላጎት በማሳየት ተጠይቆ የገንዘብ ሁኔታው መረጋገጥ አለበት። {1MCP 196.2}1MCPAmh 162.2

    እጅግ ጠቃሚ ሆነው በፊቱ ከተቀመጡ ጥናቶች መካከል አንዱ እግዚአብሔር የሰጠውን የማሰብ ችሎታ ከአካል ኃይሎች ጋር፣ ከአእምሮ፣ ከአካልና ከእግር ጋር በተጣጣመ ሁኔታ እንዲሰራ ማድረግ ነው። አንድ ሰው ማንነቱን በተገቢ ሁኔታ መጠቀም መማር የሚቻል እጅግ ጠቃሚ ትምህርት ነው። የአእምሮ ሥራ ሰርተን እዚያው ማቆም የለብንም፣ ወይም የአካል ሥራን ሰርተን እዚያው ማቆም የለብንም፤ ነገር ግን ሰብአዊ አካልን (ፋብሪካን) የሚሰሩ የተለያዩ ክፍሎችን--አእምሮን፣ አጥንትን፣ ጡንቻን፣ ራስንና ልብን-- በተሻለ ሁኔታ መጠቀም መቻል አለብን። ይህን እንዴት ማድረግ እንደሚችል የማያውቅ ማንኛውም ሰው ለአገልግሎት ብቁ (ገጣሚ) አይደለም። --Lt 103, 1897. {1MCP 197.1}1MCPAmh 162.3

    መምህራን በመዝናኛ ተግባር ላይ ይተባበራሉ።--እዚህ በእስዊዘርላንድ ብንኮርጃቸው ጥሩ ናቸው ብዬ የማስባቸውን አንዳንድ ነገሮች አያለሁ [ማስታወሻ፡- ይህ የተጻፈው ደራሲዋ አውሮፓን ስትጎበኝ ከ1885-1887 ዓ.ም ነው።] --ተማሪዎች ለጨዋታ በሚወጡበት ጊዜ መምህራን ከተማሪዎቹ ጋር አብረው ይወጡና እንዴት ራሳቸውን ማስደሰት እንዳለባቸው ከማስተማራቸው በተጨማሪ ማንኛውም ዓይነት ሥርዓተ አልበኝነት ወይም ስህተት እንዳይከሰት ለማድረግ በቅርበት ይሆናሉ። አንዳንድ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን ወደ ውጭ ይወስዱአቸውና አብረው ረዥም የእግር ጉዞ ያደርጋሉ። ይህን ድርጊታቸውን ወድጄዋለሁ፤ ልጆቹ በፈተና ለመሸነፍ ያላቸው እድል ትንሽ እንደሆነ አስባለሁ። መምህራኑ ልጆች በሚጫወቱት እስፖርት ላይ የሚሳተፉና የሚቆጣጠሩአቸው ይመስላል። {1MCP 197.2}1MCPAmh 162.4

    ልጆች ሁል ጊዜ የማይታመኑ ስለሆኑ የሚያደርጉትን ማድረግ እንደማይችሉ ሊሰማቸው ይገባል የሚለውን ሀሳብ በማንኛውም መንገድ ቢሆን መደገፍ አልችልም። ነገር ግን መምህራን በልጆች መደሰቻዎች ላይ ይሳተፉ፣ ከእነርሱ ጋር አንድ ይሁኑ፣ እነርሱ ደስተኛ እንዲሆኑ እንደሚፈልጉም ያሳዩአቸው፣ ይህ ልጆቹ በራሳቸው እንዲተማመኑ ያደርጋል። ፍቅርን በማሳየት ልንቆጣጠራቸው እንችል ይሆናል፣ ነገር ግን ይህ ጥብቅ በሆነ፣ በማይታጠፍ ጭካኔ በምግብ ሰዓታቸውና በመደሰቻ ሰዓቶቻቸው መሆን የለበትም። --5T 653 (1889). {1MCP 197.3}1MCPAmh 163.1

    በተማሪዎች ላይ እንደምትተማመንባቸው አሳይ።--ጠቢብ መምህር፣ ከተማሪዎች ጋር ሲሰራ፣ መተማመንን ለማበረታታትና ክቡር የመሆንን ስሜት ለማጠናከር ይሻል። ልጆችና ወጣቶች ሲታመኑ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ። ብዙዎች፣ ትንንሽ ልጆችም ቢሆኑ፣ ከፍተኛ የሆነ የክብር ስሜት አላቸው፤ ሁሉም በመታመንና በአክብሮት እንዲያዙ ይመኛሉ፣ ይህ መብታቸው ነው። የሚከታተላቸው ሰው በሌለበት መውጣትና መግባት እንደማይችሉ እንዲሰማቸው መመራት የለባቸውም። ጥርጣሬ ሞራልን በመግደል ለመከልከል የሚሹአቸውን እነዚያኑ ክፋቶች ይፈጥራል። ከተማሪዎቻቸው ጋር ግንኙነት ያላቸው መምህራን ክፉ ነገር ይሆናል ብሎ እንደሚጠብቅ ሰው ያለማቋረጥ ነቅቶ ከመጠበቅ ይልቅ እረፍት የለሽ አእምሮ እንዴት እንደሚሰራ ይገነዘቡና ክፉን የሚቃወሙ ተጽእኖዎችን ለመፍጠር መስራት ይጀምራሉ። ወጣቶች እንደሚታመኑ እንዲሰማቸው ከመራችሁ ለመታመን የተገቡ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የማይፈልጉ ጥቂቶች ይሆናሉ።--Ed 289, 290 (1903). {1MCP 197.4}1MCPAmh 163.2

    ተማሪዎች በመምህር ላይ መታመናቸው ጠቃሚ ነው።--መምህር ለሥራው ተገቢ መሆን አለበት። ከአእምሮዎች ጋር ለመስራት ጥበብና ብልሃት ሊኖረው ይገባል። ሳይንሳዊ እውቀቱ ምንም ያህል ትልቅ ቢሆን፣ በሌሎች የትምህርት መስኮች ያሉት ብቃቶች ምንም ያህል የላቁ ቢሆኑም፣ የተማሪዎቹን አክብሮትና እምነት ማግኘት ካልቻለ ጥረቶቹ ከንቱ ይሆናሉ። --Ed 278, 279 (1903). {1MCP 198.1}1MCPAmh 163.3

    ኋላ ቀሮችንና ተስፋ የማይጣልባቸውን መርዳት።--ለተማሪዎችህ በጎነትን፣ ፍቅርን፣ ገር የሆነ አሳብነትን ካሳየህ ያንኑ የዘራሀውን ታጭዳለህ። መምህራን ጨካኝ፣ ወቃሽ፣ ሁል ጊዜ ሌሎችን ለማዘዝ የሚሞክሩ፣ ስለ ሌሎች ሰዎች ስሜት የማይገዳቸው ከሆኑ ያንኑ መልሰው ይቀበላሉ። የራሱን ክብርና ስብዕና መጠበቅ የሚፈልግ ሰው የሌሎችን ክብርና ስብዕና መስዋዕት ላለማድረግ መጠንቀቅ አለበት። ይህ ደንብ እጅግ ስልቹ፣ እጅግ ልጅ እና እጅግ ስህተተኛ ለሆኑ ተማሪዎችም በቅድስና መጠበቅ አለበት። {1MCP 198.2}1MCPAmh 164.1

    ከእነዚህ ደስ ከማይሉ ወጣቶች ጋር ጌታ በግልጽ ምን እንደሚያደርግ አታውቅም። እግዚአብሔር ባለፉት ጊዜያት ለእርሱ ታላቅ ሥራ እንዲሰሩ እንደ እነዚህ ያሉ ናሙናዎችን ተቀብሏል፣ መርጦአልም። በልብ ውስጥ የሚሰራ የእርሱ መንፈስ በግልጽ የደነዘዙትን የአካል ኃይሎች በብርታትና በትጋት እንዲሰሩ በማነሳሳት እንደ ኤሌክትሪክ ባትሪ ሰርቷል። ጌታ በእነዚህ ባልተሞረዱ፣ ደስ በማያሰኙ፣ ባልተጠረቡ ድንጋዮች ውስጥ ሞገድን፣ ማዕበልንና ከእቶን እሳት የሚወጣውን የሙቀት ፈተና መቋቋም የሚችል ውድ ብረት ተመለከተ። ሰው እንደሚያይ እግዚአብሔር አያይም፣ ሰው እንደሚፈርድ እግዚአብሔር አይፈርድም--እርሱ ልብን ይመረምራል።--MS 2, 1881. {1MCP 198.3}1MCPAmh 164.2

    ስልቹ የሆነ ተማሪን ለመርዳት መስራት።--መምህራን ከአዋቂ ወንዶችና ሴቶች ጋር ሳይሆን ከልጆች ጋር እየሰሩ መሆናቸውን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ሁሉንም ነገር መማር ያለባቸው ልጆች ስለሆኑ አንዳንዶች ከሌሎች ይልቅ መማር እጅግ ይከብዳቸዋል። ስልቹ የሆነ ተማሪ ከሚሰጠው በላይ ብዙ ማበረታቻ ይፈልጋል። መምህራን ከእነዚህ በተፈጥሮ ለማዘዝና በሥልጣናቸው ራሳቸውን አጉልተው ለማሳየት ከሚፈልጉ ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹን ስህተቶቻቸውን ሳያልፉ በጭካኔ ሲይዙ፣ ሌሎችን በመምረጥ አብልጠው የሚወዱአቸውን በመያዝ አድልዎ ሲያሳዩ ሀላፊነት በተሰጣቸው የተለያዩ አእምሮዎች ላይ ውዝግብንና የአለመገዛት ሁኔታን ይፈጥራል። --CEd 154, 1893. (FE 269, 270.) {1MCP 199.1}1MCPAmh 164.3

    የመማሪያ ክፍል ከባቢ አየር በተማሪዎች ላይ ተጽእኖ ያሳድራል።--ክርስቲያን ነን የሚሉ የአብዛኞቹ ሰዎች ኃይማኖታዊ ሕይወት ክርስቲያን እንዳልሆኑ የሚያሳይ ነው…። በውርስ ያገኙአቸውና ያሳደጉአቸው ባሕርያት በሌሎች አእምሮዎች ላይ ሞትን እያመጡ ሳለ እንደ ክቡር ብቃቶች ተደርገው ተወስደዋል። ግልጽና ቀላል በሆኑ ቃላት ሲገለጽ ራሳቸው ባቀጣጠሉት የእሳት ፍንጣቂዎች እየተራመዱ ናቸው። ሁኔታዎች የሚገዙትና የሚቆጣጠሩት ኃይማኖት አላቸው። ማንኛውም ነገር እነርሱን በሚያስደስት መንገድ የሚንቀሳቀስ ከሆነ እና የማይገዙና ክርስቶስን የማይመስሉ ተፈጥሮአቸው እንዲገለጡ የሚያደርጉ አናዳጅ ሁኔታዎች ከሌሉ፣ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉ፣ ደስ የሚሉና ቀልብ የሚስቡ ናቸው። በቤተሰብ ውስጥ ወይም ከሌሎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ውስጥ ሰላማቸውን የሚያበላሹና ቁጣቸውን የሚቀሰቅሱ ነገሮች ሲከሰቱ፣ እንደ መምህራን በዕለታዊ ሥራቸው ላይ ከመጠመዳቸው በፊት የእርሱን ጸጋ በመለመን እያንዳንዱን ሁኔታ በእግዚአብሔር ፊት ቢያስቀምጡና ጥያቄአቸውን ማቅረባቸውን ቢቀጥሉ ኖሮ፣ ሥራቸውን ከመጀመራቸው በፊት በልባቸው የሚኖረውን የክርስቶስን ኃይል፣ ጸጋና ፍቅር ለራሳቸው ቢያውቁ ኖሮ፣ ከእነርሱ ጋር የእግዚአብሔር መላእክት ወደ መማሪያ ክፍል ይመጡ ነበር። {1MCP 199.2}1MCPAmh 164.4

    ነገር ግን ወደ መማሪያ ክፍል በቁጣና በተረበሸ መንፈስ ከሄዱ ነፍሳቸውን የሚከበው የሞራል ከባቢ አየር በእነርሱ እንክብካቤ ሥር ባሉ ልጆች ላይ አሻራውን እያሳረፈ ስለሆነ ልጆቹን ለማስተማር ገጣሚ በመሆን ፈንታ እነርሱ ራሳቸው የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርቶች የሚያስተምራቸው ሰው ያስፈልጋቸዋል። --CEd 149, 150, 1893. (FE 265, 266.) {1MCP 200.1}1MCPAmh 165.1

    ትዕግስትና ከሁኔታዎች ጋር የመስማማት ክህሎት ያስፈልጋል (ለመምህር የተሰጠ ምክር)።--ትዕግስትና ከሁኔታዎች ጋር የመስማማት ክህሎት ስለሌለህ እንደ መምህር ስኬታማ መሆን አትችልም። ከሰብአዊ አእምሮ ጋር መስራትም ሆነ እውቀትን በተሻለ ሁኔታ እንዴት ማጋራት እንደምትችል አታውቅም። አንተ እንዲሆንልህ የምትጠብቀው ነገር ሳይሆን ከቀረ ትዕግስትህ ያልቃል። ለመማር እያንዳንዱ መልካም ዕድል ነበረህ፣ ነገር ግን ጠቢብ መምህር አይደለህም። ደነዝ በሆኑ አእምሮዎች ውስጥ ሀሳቦችን ማስረጽ ለአንተ የማይመች ነገር ነው። በወጣትነትህ ሥነ-ሥርዓትን መያዝና ትዕግስት ያስፈልግህ ነበር። ነገር ግን በእርምት ሥር ስትሆን ያሳየኸው መንፈስ ሕይወትህን አበላሽቶአል።--Lt 117, 1901. {1MCP 200.2}1MCPAmh 165.2

    ወላጆች ከመምህራን ጋር መተባበር አለባቸው።--ችላ የተባለ መስክ ችላ የተባለ አእምሮን ይወክላል። ወላጆች ይህን ጉዳይ በተለየ ብርሃን ወደ ማየት መምጣት አለባቸው። ከመምህር ጋር መተባበር፣ ጥበብ ያለበትን ቅጣት ማደፋፈር፣ እና ልጆቻቸውን እያስተማረ ላለ ሰው አብዝተው መጸለይ ኃላፊነታቸው እንደሆነ ሊሰማቸው ይገባል። ልጆችን በማስጨነቅ፣ በመዝለፍ፣ ወይም ተስፋ በማስቆረጥ አትረዱአቸውም፤ ከምታጎለብቱት መንፈስ የተነሣ እንዳያምጹና እንዲታዘዙ፣ ደግነት እንዲያሳዩና የሚወደዱ እንዲሆኑ ለመርዳት ድርሻችሁን መወጣትም አትችሉም። --MS 34, 1893. {1MCP 200.3}1MCPAmh 165.3

    የኃይማኖታዊ ማህበረሰብ ኃላፊነት።--ለወጣቶች ተገቢ የሆነ ትምህርት ከመስጠት የሚበልጥ አስፈላጊ ሥራ የለም። ሰይጣን እነርሱን ከክንዳችን መንጭቆ እንዳይወስዳቸው በመዋጋት ልንጠብቃቸው ይገባል። ወጣቶች ወደ ኮሌጆቻችን ሲመጡ ለነፍሳት ግድ ወደማይላቸውና ወደማያውቁአቸው ሰዎች እንደመጡ እንዲሰማቸው ማድረግ የለብንም። አንድ ቀን መልስ እንደሚሰጡ ተሰምቶአቸው ለነፍሶቻቸው ነቅተው የሚጠብቁ አባቶችና እናቶች በእሥራኤል መኖር አለባቸው። {1MCP 200.4}1MCPAmh 166.1

    ወንድሞችና እህቶች ሆይ፣ ግድ እንደማይላችሁ ወይም ሀላፊነት እንደማይሰማችሁ ሆናችሁ ውድ ከሆኑ ወጣቶች ራሳችሁን አታግልሉ። ለረዥም ጊዜ ክርስቲያን ነን ስትሉ የነበራችሁ በትዕግትና በደግነት በትክክለኛ መንገድ ላይ ለመምራት መሥራት ያለባችሁ ሥራ አለ። እነርሱ በእድሜ የሚያንሱ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባላት፣ በደሙ የተገዙ ስለሆኑ እንደምትወዱአቸው አሳዩአቸው። --RH, Aug. 26, 1884. (FE 89, 90.) {1MCP 201.1}1MCPAmh 166.2

    ችኮ ልብና ጠማማ ባህርይ ያላቸውን መጋፈጥ።--አዳኛችን ሰፊና ሁሉን የሚያካትት ሰብአዊነት ነበረው። ልጆችን ይወድ ስለነበር በጭካኔ ይያዝ የነበረው ትንሽ ልጅ በሚሰማው ረዳተ ቢስነት ልቡ ተነክቶ ነበር። ሰብአዊ ስቃይ የሚያመጠው እጅግ ደካማው ጩኸት ወደ ጆሮው ይደርስ የነበረው በከንቱ አልነበረም። ወጣቶችን የማስተማር ኃላፊነትን የሚወስድ እያንዳንዱ ሰው ችኮ ልቦችን፣ ጠማማ ባሕርይን ስለሚጋፈጥ በእያንዳንዱ ልጅ ውስጥ የእግዚአብሔርን የግብረገብ ምስል ለመመለስ ከእግዚአብሔር ጋር መተባበር አለበት። ኢየሱስ፣ ውዱ ኢየሱስ--ጠቅላላው የፍቅር ምንጭ በእርሱ ነፍስ ውስጥ ነበር። --CEd 149, 1893. (FE 265.) {1MCP 201.2}1MCPAmh 166.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents