Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ሐኪሞችና አገልጋዮች ራሳቸውን እንዲክዱ ተጠርተዋል

    በዚህ ጧት እንድጽፍልህ እና ሁሉንም ሰዎች በእኩል እያስተናገድክ ለመሆንህ እርግጠኛ እንድትሆን እንዳሳስብህ ተሰምቶኛል፡፡ አንዳንድ ሀኪሞች እየወሰዱት ባለው ሊጎዳቸው በሚችል መንገድ አንተም ተሳታፊ መሆንህ አደጋ እንዳለው እንድነግርህ መመሪያ ተሰጥቶኛል፡፡ ለወንጌል አገልጋዮችና ለሀኪሞች እያንዳንዱን ቀጣይነት ያለው ጥቅም በመስጠት ለማደፋፈር የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን፣ ነገር ግን ማለፍ ከሚገባን በላይ መሄድ የለብንም፡፡ የሎማ ሊንዳ ጤና ማሰልጠኛ ተቋም የጤና ሀላፊ ሆኖ የሚሰራ ሀኪም ለማግኘት ጥረት እያደረግን ሳለን አንድ ልምድ ያለው ሀኪም የሆኑ ሁኔታዎች ከተሟሉ ለመምጣት ተስማማ፡፡ የሆነ ያህል ገንዘብ ከተከፈለው እንደሚመጣና ከዚያ ያነሳ ደሞዝ የሚከፈለው ከሆነ እንደማይመጣ ገለጸ፡፡ ሌላ ሰው ለማግኘት እጅግ ከባድ መስሎ ስለታያቸው አንዳንዶች ይህን ሀኪም የጠየቀውን ሰጥተን እንዲመጣ መጋበዝ አለብን ብለው አሰቡ፡፡ ነገር ግን ለወንድም ጄ ኤ ባርደን እንዲህ አልኩት፣ «ሌሎች ስራቸውን በታማኝነት እየሰሩ ያሉ ሰራተኞች አነስተኛ ደሞዝ እየተከፈላቸው ሳለ ይህን ሀኪም መቅጠርና ይህን ያህል ብዙ ደሞዝ መክፈል ትክልል አይሆንም፡፡ ይህ ፍትህ ስላልሆነ እንደዚህ ዓይነት ልዩነት ማድረግን ጌታ እንደማይቀበለው ነግሮኛል፡፡” Amh2SM 198.4

    ጌታ በአገልግሎት ውስጥ ራስን መካድ እንዲኖር እየጠራ ስለሆነ ይህ ግዴታ ሀኪሞችንና አገልጋዮችን በእኩል የሚገዛ ነው፡፡ ከፊታችን ገንዘብ የሚፈልግ ትልቅ ሥራ ስላለ እና ለዚህ ሥራ የሚያስፈልጉ ነገሮች እጥረት ስላለ ከፍተኛ ደሞዝ ሳይጠይቁ የሚሰሩ ወጣት አገልጋዮችንና ሀኪሞችን ወደ አገልግሎት መጥራት አለብን፡፡ ለከፍተኛ ደሞዝ በመስገብገብ መንፈስ ጌታ ደስተኛ አይደለም፡፡ ልቦቻቸው ለእግዚአብሔር የተቀደሱና በዚህ ምድር ላይ ከተራመዱ ሀኪሞች ሁሉ ትልቁ ከሆነው ሀኪም ወደ ፊት የመጓዝን ትዕዛዝ የሚቀበሉ ሀኪሞችንና የወንጌል አገልጋዮችን እንፈልጋለን፡፡ ብዙ ሰራተኞች የወንጌልን ዘር በመዝራት ሥራ መሰማራት እንዲችሉ የእርሱን ራስን የመካድ ሕይወት ይመልከቱና በደስታ መስዋዕትነት ይክፈሉ፡፡ ሁሉም በዚህ መንፈስ ቢሰሩ የሚያስፈልገው ደሞዝ አነስተኛ ይሆን ነበር፡፡ Amh2SM 199.1

    በዚህ ነጥብ ላይ አንዳንዶች ወድቀዋል፡፡ ተቀባይነት ያለው አገልግሎት እንዲያቀርቡ እግዚአብሔር ባርኳቸዋል፣ ነገር ግን የቁጠባን፣ ራስን የመካድን እና ከእግዚአብሔር ጋር በትህትና የመሄድን ትምህርቶች ለመማር ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ ከፍተኛ ደሞዝ እንዲከፈላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ስላገኘ በገቢ አጠቃቀማቸው ላይ አባካኝ ሆነዋል፤ ሊኖራቸው የሚገባውን መልካም ተጽእኖ ማሳደር ስላልቻሉ የሚያበለጽገው የእግዚአብሔር እጅ ከእነርሱ ጋር አልነበረም፡፡…በእግዚአብሔር ሥራ ላይ ከመሰማራታቸው በፊት ከፍተኛ የሆነ ደሞዝ በሚጠይቁ ሰዎች ላይ እጅግ ትልቅ የሆነ እምነት ከመጣል ተጠንቀቁ፡፡--Letter 330, 1906.Amh2SM 199.2