Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    «ከፍተኛ ደሞዝ አትጠይቅ”

    ባይህና አብሬህ ባወራ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተሰጠውን ምሳሌ እንድትቀዳ ጥልቅ ምኞት አለኝ፡፡...Amh2SM 201.1

    ዶ/ር ደብሊዩ ሆይ፣ ከፍተኛ የሆነ ደሞዝ እንዳትቀበል እማጸንሃለሁ፡፡ ይህን ካደረግክ ሌሎች የአንተን ምሳሌ ይከተላሉ፤ ይህ ከተፈቀደ ደግሞ ብዙም ሳይቆይ የጤና ማሰልጠኛ ተቋሙ ገቢ ለደሞዝ ክፍያ ብቻ ይውልና በውጭ አገሮች ለሚካሄደው ሚስዮናዊ ሥራ ምንም ገንዘብ አይኖርም፡፡ Amh2SM 201.2

    ይህን የምጽፍልህ ስለምን እየተናገርኩ እንደሆነ ስለምረዳ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እየተናገረ ነው፡፡ እኔና ባለቤቴ በዚህ ልምምድ ውስጥ አልፈናል፣ ከፍተኛ የሆነ ደሞዝ ባለመጠየቃችን፣ ነገር ግን ራስን በመካድና መስዋዕት በማድረግ ለመስራት ፈቃደኞች በመሆናችን ጌታ በጸጋው ብልጽግና ባርኮናል፡፡ ራስን የመካድ መንገድን ብትከተል ለሌሎች ምሳሌ ትሆንና ያ ድርጊትህ ለስራው በረከት ይሆናል፡፡ በ---በምትሰራው ሥራ ከሁሉም በላይ ውጤታማ የሆነ ስብከት የሰበክኸው በራስህ ቤተሰብ ውስጥ ለእውነት መርሆዎች በመኖርህና ለሥራው ያለህን ልባዊ የሆነ መሰጠት ባሳየህ ጊዜ ነበር፡፡ ይህን ስል ምን እየተናገርኩ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ Amh2SM 201.3

    በወንጌል አገልጋይና በሀኪም ደሞዝ መካከል ከዚህ በፊት ከነበረው የበለጠ እኩልነት መኖር አለበት፡፡ አገልጋዮቻችን ለቤተ ክርስቲያን አባላት በልግስና የመስጠትን ምሳሌ እንዲያሳዩ ስለሚጠበቅባቸው ደሞዛቸው ብዙ የገንዘብ እርዳታ ማድረግ የሚያስችላቸው መሆን አለበት፡፡--Letter 372, 1907.Amh2SM 201.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents