Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለመነሳትና የተባረካችሁ ብሎ ለመጥራት

    በኒው ዮርክ አደምስ ማዕከል ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ላይ ቤቱን ለሞላ ሕዝብ ተናገርኩ፡፡…በዚህ አጋጣሚ በዕድሜ አንጋፋ የሆኑ የእግዚአብሔርን አገልጋዮች በመገናኘታችን ተደስተን ነበር፡፡ ከሶስተኛው መልአክ መልእክት መነሳት ጀምሮ አሁን ወደ ሰማኒያ አመት እየተጠጋ ካለው ከአንጋፋው ፍሬዴሪክ ዊለር ጋር እንተዋወቅ ነበርን፡፡ ከአንጋፋዎቹ ኤች ኤች ዊልኮክስ እና ቻዝ ኦ ቴይለር ጋር ደግሞ ላለፉት አርባ ዓመታት እንተዋወቅ ነበርን፡፡ እነዚህ ቀደምት አርማ ተሸካሚዎች እና እኔንም ጨምሮ እያረጀን መሆናችንን እድሜያችን እየተናገረ ነው፡፡ እስከ መጨረሻው ታማኞች ከሆንን ጌታ የማያረጀውን የሕይወት አክሊል ይሰጠናል፡፡ Amh2SM 223.1

    በእድሜ የገፉ አርማ ያዦች አይጠቅሙም ተብለው ወደ ጎን የሚጣሉ አይደሉም፡፡ በሥራው ውስጥ ከዮሐንስ ሥራ ጋር ተመሳሳይ የሆነ የሚጫወቱት ሚና አላቸው፡፡ እንዲህ ማለት ይችላሉ፡- «ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፣ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን፡፡ሕብረታችንም ከአብ ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው፡፡ ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን፡፡ ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፡- እግዚአብሔር ብርሐን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህቺ ናት፡፡ ከእርሱ ጋር ሕብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትም አናደርግም፤ ነገር ግን እርሱ በብርሐን እንዳለ በብርሐን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ሕብረት አለን፣ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” (1ኛ ዮሐ. 1፡ 1-7)፡፡ Amh2SM 223.2

    ይህ መልእክት ዮሐንስ በእርጅና እድሜው፣ ወደ አንድ መቶ አመት ገደማ ሆኖት ሳለ፣ ያስተላለፈው መልእክት መንፈስና ሕይወት ነበር፡፡ አርማ ተሸካሚዎች ባንዲራዎቻቸውን አጥብቀው ይዘዋል፡፡ የጦር መሣሪያቸውን እስከሚያስቀምጡ ድረስ የእውነትን ባንድራ የያዘውን እጃቸውን እያላሉ አይደሉም፡፡ ያረጁ ተዋጊዎች ድምፆች አንድ በአንድ ዝም ይላሉ፡፡ ቦታቸው ክፍት ነው፡፡ ከሞቱ በኋላ አናያቸውም፣ ነገር ግን ሥራቸው ስለምትከተላቸው ሞተው ሳሉም ይናገራሉ፡፡ ስለ ሥራቸው ብለን ከፍተኛ ክብር በመስጠት አሁን ያሉትን ጥቂት በዕድሜ የገፉ ተጓዦችን በጣም በፍቅር እንያዛቸው፡፡ ኃይሎቻቸው እየደከሙና እየዛሉ ሳሉ የሚናገሩት ዋጋ ያለው ነገር ነው፡፡ ቃሎቻቸው እንደ ከበረ ምስክርነት ዋጋ ይሰጣቸው፡፡ ወጣቶችና አዲስ ሰራተኞች የሸበቱ ፀጉሮችን ዋጋ መስጠት አለባቸው፤ በማንኛውም መንገድ ቢሆን ቸል ማለት የለባቸውም፡፡ ነገር ግን ተነስተው የተባረካችሁ ናችሁ ይበሏቸው፡፡ እነርሱ ራሳቸው እነዚህ ሰዎች ለፍተው ወዳቀኑት ሥራ እንደገቡ መገንዘብ አለባቸው፡፡ መልእክቱን በማስተላለፍ የመጀመሪያዎች ለነበሩት በአማኞች ልብ ውስጥ እጅግ ብዙ ፍቅር እንዲኖራቸው እንመኛለን፡፡ Manuscript 33, 1890.Amh2SM 223.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents