Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ፈር ቀዳጆችን ለማክበርና ከፍተኛ ክብር ለመስጠት

    ከቀድሞዎቹ አርማ ተሸካሚዎች መካከል ጥቂቶች አሁንም በሕይወት አሉ፡፡ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እነዚህን ፈር ቀዳጆች እንዲያከብሩና ከፍተኛ ክብር እንዲሰጧቸው ጥልቅ ፍላጎት አለኝ፡፡ እነርሱን ወደ እናንተ የምናቀርባቸው ችግር ምን እንደሆነ እንደሚያውቁ ሰዎች አድርገን ነው፡፡ መልእክቱ በተላለፈበት በቀድሞዎቹ ቀናት ጉልህ ሚና የተጫወቱትንና ፈተና፣ መከራ እና ብዙ ችግሮችን የተሸከሙትን ሰዎች እያንዳንዱ አማኝ እንዲያከብር እንድነግር ታዝዣለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች የሸበቱት በአገልግሎት ነው፡፡ ሽልማታቸውን የሚቀበሉበት ጊዜም ሩቅ አይሆንም፡፡…Amh2SM 226.3

    ለእውነት ጥብቅና በመቆም የሸበቱ አገልጋዮች ሕግን ደግፈው ምስክርነታቸውን በመሸከም ታማኝና እውነተኛ ሆነው እንዲቆሙ ጌታ ይሻል፡፡ Amh2SM 227.1

    የተፈተኑ የእግዚአብሔር አገልጋዮች አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎች መደረግ የለባቸውም፡፡ ሥራው ከባድ በነበረበት ወቅት ጌታቸውን ያገለገሉ፣ ቁጥራችን ትንሽ በነበረበት ወቅት ድህነትን የታገሱትና በእውነት ፍቅር ታማኝ ሆነው የቆሙት ሁልጊዜ መከበርና ትልቅ የሆነ ከፍተኛ ክብር ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ በኋላ ወደ እውነት የመጡት ሰዎች እነዚህን ቃላት ልብ ይበሉ፡፡ ሁሉም ይህን ማስጠንቀቂያ ልብ እንዲሉ እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ Letter 47, 1902.Amh2SM 227.2