Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ከሚያስጨንቁ ሸክሞች መላቀቅ

    ከባድ ሸክም የተሸከሙ ሰዎች ከዚያ በመለየት ለጥቂት ጊዜ ማረፍ ጥበብ ነው፡፡ እነዚህ ታማኝ ሠራተኞች ከእያንዳንዱ የሚያስጨንቅ ሸክም ማረፍ አለባቸው፡፡ እንደ መምህራን የሚሰሩት ሥራ መደነቅ አለበት፡፡ ሌሎችን ለማስተማር በሚያደርጉት ጥረት ጌታ ራሱ ይተባበራቸዋል፡፡ ትግሉን በዕድሜ ወጣት ለሆኑት መተው አለባቸው፤ የወደ ፊት ሥራ ጠንካራ በሆኑ ወጣቶች መሰራት አለበት፡፡ ሥራው በእምነታችን ጀማሪና ፈጻሚ በሆነው ቁጥጥር ሥር ነው፡፡ እርሱ ዕድሉ ላላቸው ሰዎች ብቃትን መስጠት ይችላል ይሰጣቸዋልም፡፡ የእርሱን ጦርነቶች መዋጋት የሚችሉትን ያስነሳል፡፡ ሥራውን በፍጹም ለዕድል አይተውም፡፡ ይህ ሥራ ታላቅና ክቡር ስለሆነ ወደ ፊት መሄድ አለበት፡፡Amh2SM 228.1

    በሥራው ውስጥ ያሉ አባቶች የቀረላቸውን ብርታት ከባድ ሸክሞችን ለመሸከም እንዲጠቀሙ የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም፡፡ ወጣቶች መሸከም የሚችሉትን እያንዳንዱን ኃላፊነት በወንድነት ስሜት በመሸከም መልካሙን የእምነት ገድል በጀግንነት ይጋደሉ፡፡ ምንም ያህል ፍላጎት ቢኖራቸውም እጅግ ጠቢባን ሰዎች ማድረግ ከሚችሉት የበለጠ ጌታ ሥራውን እንዲሰሩ እነማንን እንደሚመርጥ ያውቃል፡፡ ወጣቶች ታላላቅ ተቃውሞዎችን እንዲዋጉለት ለመምራት በልባቸው ውስጥ መንፈሱን የሚያስቀምጥ እግዚአብሔር ነው፡፡ በመሆኑም ከሰማይ ለተገለጠለት እውነት የተሰጡትን ችሎታዎች ሁሉ በመጠቀም ከዚህ በፊት ይደግፋቸው የነበሩትን ክህደቶች የተዋጋውን የተርሴሱን ጳውሎስ ያነሳሳው እሱ ነው፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ዛሬ ከዚህ በፊት ጳውሎስ ከተጋፈጣቸው ችግሮች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ችግሮችን ይጋፈጣሉ፡፡ አሁን የእውነትን ባንዲራ ከፍ አድርገው እያነሱ ካሉት መካከል አንዳንዶች በዚህ ልምምድ ውስጥ አልፈዋል፡፡ የእውነት መከታ ሆነው መቆም የሚችሉት እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ተማሪዎች ሆነው ከቀጠሉ እግዚአብሔር የሕጉን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ሊጠቀምባቸው ይችላል፡፡Amh2SM 228.2