Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ቅዱሳን እንደሆኑና እንደታተሙ መናገር

    በ1850 ዓ.ም ባለቤቴና እኔ ቨርሞንትን፣ ካናዳን፣ ኒው ሀምሻዬርን እና ማይኔን ጎበኘን፡፡ ስብሰባዎች ይደረጉ የነበሩት በግለሰብ ቤቶች ነበር፡፡ ያኔ ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች ጋ መድረስ እጅግ ከባድ ነበር፡፡ የ1844 ዓ.ም ተስፋ መቁረጥ የብዙዎችን አእምሮ ግራ ስላጋባ ስለ ጉዳዩ ምንም ዓይነት ማብራሪያ እሽ ብለው አይሰሙም ነበር፡፡ የማያምኑና ትዕግሥት የለሾች ነበሩ፣ ብዙዎች ያለፈውን የዳግም ምጻት ልምምድ በጽኑ በመቃወም የአመጸኝነት ባሕርይ የሚያንጸባርቁ ይመስሉ ነበር፡፡ ሌሎች የዚህን ያህል ርቀት ለመሄድ ባይደፍሩም እግዚአብሔር የመራቸውን መንገድ አይቀበሉም ነበር፡፡ እነዚህ አቋማችንን ከትንቢታዊ ታሪክ ጋር የሚያጣጥሙትን መከራከሪያዎች ከእግዚአብሔር ቃል ለመስማት ደስተኞች ነበሩ፡፡ እጅግ መራራ የነበረባቸውን የተስፋ መቁረጥ ማብራሪያ ሲሰሙ በእርግጠኝነት እግዚአብሔር እንደመራቸው ተመለከቱና በእውነት ሀሴት አደረጉ፡፡ ይህ ያለፈውን ልምምዳችንን ከማይቀበሉ ሰዎች ዘንድ እጅግ የመረረ ተቃውሞ አስነሳ፡፡ {2SM 26.4}Amh2SM 26.4

    ነገር ግን እንደተቀደሱ፣ ኃጢአት እንደማይሰሩ፣ እንደ ታተሙና ቅዱሳን እንደሆኑ እና ግምታቸውና ሀሳባቸው ሁሉ የእግዚአብሔር አእምሮ እንደሆነ በሚናገሩ ክፍሎች ውስጥ ገና የምንጋፈጠው አስከፊ ነገር አለ፡፡ ትጉህ ነፍሳት በእነዚህ ወግ አጥባቂዎች የማስመሰል ቅድስና (ኃይማኖተኛነት) ተታለዋል፡፡ እነዚህ የተታለሉ ሰዎች ሰንበትን እንዲቀበሉ ሰይጣን በብልጠት ሰርቷል፡፡ ይህን ያደረገበት ምክንያት የእውነትን አንዱን ክፍል እንደሚያምኑ ስለሚናገሩ እነርሱ በሚያሳድሩት ተጽዕኖ በሕዝብ ላይ እጅግ ብዙ የሆኑ ስህተቶችን ለማጨቅ ነው፡፡ ሰዎች እነዚህን አቋም የሌላቸውንና ምክንያታዊ ያልሆኑ ሰዎችን ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶችን እንደሚወክሉ አድርገው በመጠቆም አማኞችን እንዲጠሉ ለማድረግ ለራሱ መልካም ዓላማም ይጠቀምባቸዋል፡፡ እነዚህ ክፍሎች በሕዝብ ላይ ሰብዓዊ መፈተኛዎችን አስቀምጠዋል፣ ክርስቶስ እንዲሸከሙት ያልሰጣቸውን መስቀሎችም አዘጋጅተዋል፡፡ {2SM 27.1}Amh2SM 27.1

    ሕመምተኞችን እንደሚፈውሱና ተአምራት እንደሚሰሩ ይናገሩ ነበር፡፡ ሰይጣናዊ የሆነ የአስማት ኃይል ነበራቸው፤ ሆኖም የሰዎችን ሀሳብ የሚያጥላሉ፣ አምባገነኖች፣ ጨካኞችና ጨቋኞች ነበሩ፡፡ እነዚህን ጽንፈኞች በመገሰጽ ታማኝ የሆኑ ሕዝቦቹ የሥራቸውን እውነተኛ የሆነ ጠባይ ማየት እንዲችሉ ዓይናቸውን ለመክፈት ጌታ እንደ መሳሪያዎች ተጠቀመብን፡፡ ከዚህ የሰይጣን ማታለያ በተላቀቁ ልቦች ውስጥ ደስታና ሰላም መጣ፣ ከዚያም ከሰይጣን የመናፍቅነት ትምህርትና ማታለያዎቹ በተቃራኒ እግዚአብሔር በፊታቸው የእውነትን ብርሃንና እውነት የሚያፈራውን የከበሩ ፍሬዎች በማስቀመጡ የእሱን የማይሳሳት ጥበብ በመመልከት እግዚአብሔርን አከበሩ፡፡ ከእነዚህ ማታለያዎች በተቃራኒ እውነት በምድር ቆሻሻ መካከል እንዳለ የጠራ ወርቅ አበራ፡፡ --The Review and Herald, Nov. 20, 1883. {2SM 27.2}Amh2SM 27.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents