በባሕርያችን ውስጥ ሥነ ሥርዓትን ጠብቆ ማቆየት
1844 ዓ.ም ካለፈ በኋላ በአድቬንቲስቶች ውስጥ ጽንፈኝነት ገባ፡፡ እየመጣ የነበረውን ክፉ ለመከላከል እግዚአብሔር ማስጠንቀቂያ ሰጠ፡፡ በአንዳንድ ወንዶችና ሴቶች መካከል ከልክ ያለፈ ቅርርብ ነበር፡፡ እግዚአብሔር የሚቀበለውን የባሕርይ መስፈርት ለማሟላትና ያለ ነቁጣ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም ማንኛውም እንዲህ ያለ ነገር ሳይኖር ለመገኘት መድረስ ያለብንን ቅዱስ የሆነ የእውነት ደረጃ እና መጠበቅ ያለብንን የባሕርይ ንጽህና በፊታቸው አቀረብኩላቸው፡፡ በተለየ ሁኔታ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዳላቸው እየተናገሩ ሳለ ሀሳባቸው እጅግ በረከሰ መስመር እየሄደ ለነበሩ ወንዶችና ሴቶች ከእግዚአብሔር ዘንድ ከባድ የሆኑ ነቀፌታዎች ተሰጥተው ነበር፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መልእክት ተንቆና ተቀባይነት አጥቶ ነበር፡፡ . . . {2SM 29.1}Amh2SM 29.1
አሁንም ቢሆን ከአደጋ ነጻ አይደለንም፡፡ የማስጠንቀቂያ መልእክትን ለዓለም በማስተላለፍ ሥራ ላይ የሚሰማራ እያንዳንዱ ነፍስ እምነቱን እንዲክድ የሚጠይቀውን መንገድ እንዲከተል ለብቻው ይፈተናል፡፡ {2SM 29.2}Amh2SM 29.2
ከእርስ በርሳችን ጋር በምናደርጋቸው ግንኙነቶች ከክፋት ጋር አነስተኛ ቅርበት እንኳን ላለው ለማንኛውም ነገር ቢሆን ፊት ላለመስጠትና ለመኮነን እንደ ሰራተኞች አንድ መሆን አለብን፡፡ እምነታችን ቅዱስ ነው፤ ሥራችን የእግዚአብሔርን ሕግ ክብር የሚያረጋግጥ እንጂ ማንንም ሰው በሀሳብና በባሕርይ ወደ ዝቅተኛ ደረጃ የማምጣት ባሕርይ ያለው አይደለም፡፡ እውነትን እንደሚያምኑና እንደሚያስተምሩ የሚናገሩ፣ ግን የራሳቸውን ስህተት እና ብልጭልጭ ሀሳቦች ከእውነት ጋር ቀላቅላው የያዙ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ነገር ግን እኛ መቆም ያለብን ከፍ ያለ መድረክ አለ፡፡ በክርስቶስ ያለውን እውነት እንዳለ ማመንና ማስተማር አለብን፡፡ የልብ ቅድስና በፍጹም ወደ እርኩስ ተግባራት አይመራም፡፡ እውነትን እንደሚያስተምር የሚናገር ሰው ከወጣት እና ካገቡት ሴቶች ጋር አብሮ ለመሆን የሚያዘነብል ከሆነ፣ በሰውነታቸው ላይ እጁን የሚያሳርፍ ከሆነ ወይም እጅግ በቀረበ ሁኔታ ከእነርሱ ጋር የሚነጋገር ከሆነ እሱን ፍሩት፡፡ ንጹህ የሆኑ የእውነት መርሆዎች በነፍሱ ውስጥ አልተሰሩም፡፡ እንደ እነዚህ ያሉት ከክርስቶስ ጋር አብረው ሠራተኞች አይደሉም፤ እነሱ በክርስቶስ አይደሉም፣ ክርስቶስም በውስጣቸው አላደረም፡፡ እግዚአብሔር ሥራቸውን ከመቀበሉ በፊት አጠቃላይ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል፡፡ {2SM 29.3}Amh2SM 29.3
ሰማያዊ መነሻ ያለው እውነት ተቀባዩን በፍጹም አያዋርደውም፣ በአነስተኛ ደረጃም ቢሆን ተገቢ ወዳልሆነ መቀራረብ በፍጹም አይመራውም፤ ከዚህ በተቃራኒ አማኙን ይቀድሰዋል፣ ፍላጎቱን ያስተካክልለታል፣ ከፍ ያደርገዋል ያከብረዋልም፣ ከኢየሱስ ጋር የቀረበ ግንኙነት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ጳውሎስ መልካም የሆነውን ክፉ አድርገው እንዳይናገሩ ክፉ ከሚመስል ነገር እንድንታቀብ የሰጠውን ትዕዛዝ ወደ መጠበቅ ይመራዋል፡፡ -- The Review and Herald, Nov. 10, 1885. {2SM 30.1}Amh2SM 30.1
[ቀድሞ ስለነበረው ወግ አጥባቂነት የበለጠ መረዳት ከፈለጉ ላይፍ እስከችስ የሚለውን መጽሐፍ ገጽ 85-94ን፣ ቴስቲሞኒስ ፎር ዘ ቸርች አንደኛው መጽሐፍ ገጽ 71-73ን፣ ስምንተኛው መጽሐፍ ገጽ 291 እና 292ን፣ ጎስፕል ወርከርስ ገጽ 316 እና 317ን ያንብቡ፡፡] {2SM 30.2}Amh2SM 30.2