Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ብዙ ሳይቆይ ሕይወታቸው ለሚደመደም ለሌሎች ሰዎች የተሰጠ መልእክት

    ምንም እንኳን ከእናንተ ርቀን ብንገኝም እናዝንላችኋለን፡፡ ተስፋ አትቁረጡ፣ ነገር ግን «ጠይቁ ይሰጣችኋል» (ሉቃስ 11፡ 9) የሚለውን ተስፋ ተጠማጠሙ፡፡ የመፈወስ ሥራን መሥራት የሚችል፣ መጨረሻን ከመጀመሪያው የሚያውቅ፣ ልጁ በትንሳኤ ማግስት እንድትነሳ አሁን እንድትሞት ቢፈቅድ ተስፋ አትቁረጥ፡፡ «የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም» በል፡፡…ባለቤትህ በሥቃይ ውስጥ ብትወድቅም የወደፊት ሕይወት መኖሩን አስታውስ፡፡ የመጨረሻው መለከት ክርስቶስን የተቀበሉትን፣ በእርሱ ያመኑትን እና ለድነት በእርሱ የታመኑትን ይጠራቸዋል፡፡ Amh2SM 255.1

    ውድ እህቴ ሆይ፣ እንጸልይልሻለን፡፡ ርኅራኄያችን ከአንቺ ጋር ነው፡፡ የአንቺን ጉዳይ ለታላቁ ሀኪም እናቀርባለን፡፡ ይህ እንደተደረገ እረዳለሁ፡፡ ለአሁንም ሆነ ለዘላለማዊ ሕይወት የሚጠቅም እንደሆነ ከተመለከተ መባረክና መፈወስ የሚችለውን የእርሱን እጅ አጥብቀሽ ያዢ፡፡ ወንድሜና እህቴ ሆይ፣ አሁን ሁለታችሁም በሕይወት ሳላችሁ በእምነት የእግዚአብሔርን ቃል ክቡር ተስፋዎች ለራሳችሁ ለማድረግ ይህን ውድ ጊዜ ውሰዱ፡፡ ሁለታችሁም ለኃጢአት ሁሉ ይቅርታን በትህትና እንደሚፈልጉ ሰዎች ራሳችሁን በማቅረባችሁ አምላክን አመሰግናለሁ፡፡ Amh2SM 255.2

    ክቡር አዳኛችን ለዓለም ኃጢአት ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠት ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ እንደሚያድን ቃል ገብቷል፡፡ «በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲሆንለት እንጂ ማንም እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከሚሰጥ ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዷልና» (ዮሐ. 3፡ 16)፡፡ የዘላለም ሕይወትን የማግኛ ቅድመ ሁኔታዎች እነዚህ ናቸው፡፡ እነዚህን ነገሮች ከተከተልሽ ብትሞቺም ብትኖሪም ተስፋሽ እርግጠኛ ነው፡፡ ነፍስን በሚያድን አዳኝ ታመኚ፡፡ ረዳተ-ቢስ ነፍስሽን በእርሱ ላይ ከጣልሽ እሱ ይቀበልሻል፣ ይባርክሻል፣ ያድንሻልም፡፡ ብቻ እመኚ፡፡ በሙሉ ልብሽ ተቀበይው፣ የሕይወት አክሊል እንድታገኚ እንደሚፈልግም እወቂ፡፡ ይህ ትልቁና ልባዊ ጥያቄሽ ይሁን፡፡ ሙሉ በሙሉ ለእርሱ ራስሽን አሳልፈሽ ስጪ፣ እርሱ ከእያንዳንዱ ብክለት ያነጻሽና የክብር ዕቃ ያደርግሻል፡፡ በበጉ ደም ታጥበሽ ነጭ ትሆኚያለሽ፡፡ በመሆኑም ድልን ታገኚያለሽ፡፡… በእምነት አጥብቀሽ ያዢ፡፡ --Letter 45, 1905.Amh2SM 255.3