Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በጌታ የሚሞቱ ሙታን የተባረኩ ናቸው

    በእናት ሞት ምክንያት የተሰጠ ማጽናኛ

    ውድ እህት፣

    የእናትሽን ሞት በተመለከተ ደብዳቤውን አንብቤያለሁ፣ ልነግርሽ የምችለው “በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁአን ናቸው” (ራዕይ 14፡ 13) የሚለውን ነው፡፡ ለረዥም ጊዜ እናትሽ በጣም ደክማ ቆይታለች፡፡ ያለመሰልቸት ተጠንቅቀሽላታል፡፡ አሁን ፊቷን ማየት አለመቻልሽ ታላቅ ሀዘን ሊሆንብሽ ይችላል፡፡ አጠገብሽ የምንኖር ቢሆን ኖሮ ተለይና ትንሽ እረፊ እንልሽ ነበር፡፡ ነገር ግን ያሉብሽ ሀላፊነቶች ጊዜሽን የሚፈልጉ ናቸው፡፡ በጌታ ታመኚ እልሻለሁ፡፡ Amh2SM 261.2

    የእናትሽ ሞት በጣም ይሰማሻል፤ ነገር ግን እኔ የማዝነው ለሞቱት ጸድቃን ሳይሆን በሕይወት ላሉት እንደሆነ እነግርሻለሁ፡፡ እናትሽን የቀበርሽው የእግዚአብሔር መለከት ሲነፋ ከመቃብር እንደምትነሳ ሙሉ በሙሉ ተስፋ በማድረግ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡…የምትወጂያቸውን ሰዎች መቅበር ማለት ምን ማለት እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ አባቴ፣ እናቴ፣ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ባለቤቴና ከልጆቼ ሁለቱ በመቃብር ተኝተው ይገኛሉ፡፡ በሕይወት ያለነው እህቴ ሜሪ፣ እኔና ሁለቱ ልጆቼ ነን፡፡--Letter 98, 1903.Amh2SM 261.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents