Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በልዩ ትንሳኤ ይጠራሉ

    ሚስትንና እናትን ላጡ ባልና ልጆች የተሰጡ የማጽናኛ ቃላት

    ውድ ወንድም ሆይ፡

    ምን እንደምልህ አላውቅም፡፡ የባለቤትህ ሞት ዜና ለእኔ መሸከም ከምችለው በላይ ነበር፡፡ ማመን አቅቶኝ ነበር፣ አሁንም ማመን ያቅተኛል፡፡ እግዚአብሔር ባለፈው የሰንበት ምሽት አሁን የምጽፍልህን እይታ ሰጠኝ፡፡…Amh2SM 263.2

    እንደታተመች፣ በእግዚአብሔር ድምጽ ከሙታን በመነሳት በምድር ላይ እንደምትቆም እና ከአንድ መቶ አርባ አራት ሺሆች (144000) ጋር እንደምትሆን አየሁ፡፡ ለእሷ ማዘን እንደሌለብን አየሁ፤ እሷ በመከራ ጊዜ ታርፋለች፣ እኛን የሚያሳዝነን ነገር ቢኖር የእሷ በአጠገባችን አብራ አለመሆን ብቻ ነው፡፡ የእሷ ሞት መልካም ውጤት እንደሚያመጣ አይቻለሁ፡፡ Amh2SM 263.3

    ኤፍን እና ሌሎች ልጆችን የማስጠነቅቀው ኢየሱስን ለመገናኘት እንዲዘጋጁ ነው፣ ያ ከሆነ ለዘላለም ላለመለየት ከእናታቸው ጋር እንደገና ይገናኛሉ፡፡ ልጆች ሆይ፣ እሷ ከእናንተ ጋር ሳለች የሰጠቻችሁን ማስጠንቀቂያዎች በመታዘዝ ስለ እናንተ ወደ እግዚአብሔር የጸለየቻቸው ጸሎቶች ሁሉ በመሬት ላይ እንደተደፋ ውኃ ሆነው እንዳይቀሩ አታደርጉምን? ኢየሱስን ለመገናኘት ተዘጋጁ፣ ያኔ ሁሉም ነገር ደህና ይሆናል፡፡ ልባችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ፣ ኢየሱስን እንደምትወዱት እስካላወቃችሁ ድረስ ለአንድ ቀን እንኳን አትረፉ፡፡ Amh2SM 263.4

    ውድ ወንድም ሆይ፣ እግዚአብሔር ወገብህን እንዲያስታጥቅህ እና የደረሰብህን ኪሳራ መቋቋም እንድትችል ብርታት እንዲሰጥህ ጸልየናል፡፡ እግዚአብሔር አብሮህ በመሆን ይደግፍሃል፡፡ እምነት ብቻ ይኑርህ”….Amh2SM 263.5

    ተስፋ እንደሌላቸው አትዘን፡፡ መቃብር ይዟት የሚቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው፡፡ ውድ ወንድም ሆይ፣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ስለምታገኛት እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፣ ደስም ይበልህ፡፡ የእግዚአብሔር በረከቶች በአንተና በቤተሰብህ ላይ እንዲያርፉ መጸለያችንን አናቋርጥም፡፡ እግዚአብሔር ፀሐይህና ጋሻህ ይሆናል፡፡ በዚህ ጥልቅ በሆነ መከራህና ፈተናህ ውስጥ በአጠገብህ ይቆማል፡፡ ፈተናውን ታገስና ክርስቶስ ሲገለጥ ከትዳር አጋርህ ጋር የክብር አክሊል ትቀበላለህ፡፡ እውነትን አጥብቀህ ከያዝክ ከእሷ ጋር ግርማ፣ ክብር፣ የማይሞት አካል እና የዘላለማዊ ሕይወት ዘውድ ይደረግላችኋል፡፡--Letter 10, 1850.Amh2SM 263.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents