በመድሃኒቶች አሰጣጥ ላይ የተሰጠ ምክር
እምብዛም አይፈለጉም፡- አጠቃቀማችሁ አነስተኛ ይሁን፡፡ የመድሃኒት ሕክምና በአጠቃላይ እንደሚደረገው ከሆነ እርግማን ነው፡፡ ሰዎች ከመድሃኒቶች እንዲርቁ አስተምሯቸው፡፡ የመድሃኒት አጠቃቀማችሁ አነስተኛ ይሁንና የበለጠውን በንጽህና ዘዴዎች ተደገፉ፤ ከዚያ በኋላ ተፈጥሮ ለእግዚአብሔር ሐኪሞች፡- ለንጹህ አየር፣ ለንጹህ ውኃ፣ ተገቢ ለሆነ የሰውነት እንቅስቃሴ እና ንጹህ ለሆነ ህሊና ምላሽ ትሰጣለች፡፡ ሻይን፣ ቡናን እና ሥጋን የሚጠቀሙ ሰዎች መድሃኒቶች እንደሚያስፈልጓቸው ይሰማቸዋል፡፡ ነገር ግን ብዙዎች የጤና ሕጎችን ቢታዘዙ ኖሮ አንዲት የመድሃኒት ቅንጣት ሳይጠቀሙ ጤንነታቸው ይመለስላቸው ነበር፡፡ Counsels on Health, p. 261 (1890).Amh2SM 281.4
የመድሃኒቶች አጠቃቀማችሁን ለመቀነስ እሹ፡- ሐኪሞች የመድሃኒቶችን አጠቃቀም ከመጨመር ይልቅ የበለጠውን ለመቀነስ መሻት አለባቸው፡፡ ዶክተር ኤ ወደ ጤና ስብሰባ በመጣች ጊዜ የንጽህና እውቀቷንና ልምምዷን ወደ ጎን በመተው ለእያንዳንዱ ሕመም ጥቂት አደገኛ የሆኑ መድሃኒቶችን ሰጥታ ነበር፡፡ ይህ እግዚአብሔር የሰጠው ብርሃን ተፃራሪ ነው፡፡ ስለዚህ መድሃኒቶችን በማንኛውም መልክ ቢሆን እንዳይጠቀሙ ሲማሩ የነበሩት ሕዝቦቻችን የተለየ ትምህርት እየተቀበሉ ናቸው፡፡ Letter 26a, 1889 (To a prominent physician in institutional work).Amh2SM 282.1
ጠንካራ መድሃኒቶች ጥቅም ላይ መዋል የለባቸውም፡- የሐኪም የመጀመሪያው ጥረት መሆን ያለበት ታማሚዎችና በሥቃይ ውስጥ ያሉ ሰዎች በሽታን ለመከላከል መከተል ስላለባቸው መንገድ ማስተማር ነው፡፡ ትልቅ ጠቃሚ ሥራ ሊሰራ የሚችለው ልንደርስ የምንችላቸውን አእምሮዎች በሙሉ ሥቃይንና በሽታን፣ የተሰበረ የሰውነት አቋምንና ያለ ጊዜ መሞትን ለመከላከል መከተል ያለባቸውን መንገድ እንዲያውቁ ለማድረግ ጥረት በማድረጋችን ነው፡፡ ነገር ግን የአካልና የአእምሮ ኃይሎቻቸውን በሥራ እንዲጠመዱ የሚያደርገውን ሥራ ለመሥራት ግድ የማይላቸው ሰዎች ሕመሙን ከማስታገስ ይልቅ በሰብዓዊ አካል ውስጥ ከሁለት እጥፍ ለበለጠ ክፋት መሰረት የሚጥለውን መድሃኒት ለማዘዝ ይዘጋጃሉ፡፡Amh2SM 282.2
ግንዛቤን ግልጽ በሆኑ እውነታዎች በማብራት፣ የበሽታ ባሕርይንና እንዴት መከላከል እንደሚቻል በማሳየት፣ እና መድሃኒቶችን መጠቀምን እንደ ብቸኛ አማራጭ አድርጎ የመውሰድን አደገኛ ልምምድ በማሳየት ዝናውን ለአደጋ የማጋለጥ የሞራል ድፍረት ያለው ሐኪም ሥራው ዳገት ያለበት ቢሆንም እሱም ይኖራል ሌሎችም እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡… ይህ ሐኪም ተሃድሶ አምጭ ከሆነ ትክክል ያልሆኑትንና አጥፊ የሆኑ የራስ ፍላጎቶችን መፈጸምን በተመለከተ፣ ስለ አለባበስ፣ ስለ ምግብና ስለ መጠጥ፣ በስሜት፣ በአካልና በአእምሮ ኃይሎች ላይ አጥፊ ተጽእኖ ያለውን በአንድ የተወሰነ ጊዜ ውስጥ ብዙ ሥራን ለመሥራት ራስን ማስጨነቅን በተመለከተ በግልጽ ይናገራል፡፡…Amh2SM 282.3
ትክክለኛ የሆኑ ልምዶች፣ በብልጠትና አካልን በሚጠብቅ ሁኔታ ሲተገበሩ ለበሽታ መንስኤ የሆኑ ነገሮችን ያስወግዳሉ፣ ያኔ ጠንካራ የሆኑ መድሃኒቶች እንደ ብቸኛ አማራጭ አይወሰዱም፡፡ ብዙዎች በተቻለ መጠን ተፈጥሮአዊ ያልሆኑ ሁኔታዎችን የሚያመጡ ተፈጥሮአዊ ያልሆኑ ፍላጎቶችን በመፈጸም ደረጃ በደረጃ ወደ ፊት ይቀጥላሉ፡፡ Medical Ministry, pp. 221, 222 (General Manuscript entitled “Sanitariums,” 1887).Amh2SM 283.1
በአጠቃላይ ሥራ ላይ እንደዋለ ከሆነ፡- የመድሃኒት ሕክምና፣ በአጠቃላይ ሥራ ላይ እየዋለ ባለበት ሁኔታ፣ እርግማን ነው፡፡ Healthful Living, p. 246 (1888).Amh2SM 283.2
በጥበብ ከተሰጠ አደገኛነቱ አነስተኛ ነው፡- መድሃኒቶችን አትስጡ፡፡ መድሃኒቶች በጥበብ ቢሰጡ ኖሮ በተለምዶ እየሆነ ያለውን ያህል አደገኛ እንደማይሆኑ እውነት ነው፣ ነገር ግን በብዙዎች እጅ ውስጥ የእግዚአብሔርን ንብረት የሚጎዱ ይሆናሉ፡፡ Letter 3, 1884 (To Workers at St. Helena Sanitarium).Amh2SM 283.3
ሙሉ በሙሉ ማስወገድ፡- ተቋሞቻችን የተቋቋሙት የመድሃኒቶችን አጠቃቀም ሙሉ በሙሉ በመተው ሕመምተኞችን በንጽሕና የጤና አጠባበቅ ዘዴ ለማከም ነው፡፡ …መድሃኒቶቻቸውን በመስጠት፣ አካልን በጭካኔ በማከም፣ ለሰብአዊ ሕይወት እጅግ አነስተኛ አክብሮት ያላቸው ሰዎች ለእግዚአብሔር መስጠት ያለባቸው አሰቃቂ የሆነ ተጠያቂነት አለባቸው፡፡ በማናውቃቸው በተለያዩ ስሞች የተዘጋጁትን መርዘኛ መድሃኒቶች ወደ ሆዳችን ውስጥ በማስገባት ከአለማወቃችን የተነሳ የእግዚአብሔርን ሕንፃ ብናፈርሰው ይቅርታ አናገኝም፡፡ እነዚህን የመሳሰሉትን የሐኪም ትዕዛዞች እምቢ ማለት የእኛ ሀላፊነት ነው፡፡ Amh2SM 283.4
በአውስትራሊያ በሽታዎች ተፈጥሮ ራሷ በምትሰጣቸው ነገሮች የሚፈወሱበትንና ሰዎች ሲታመሙ እንዴት ራሳቸውን ማከም እንዳለባቸው የሚማሩበትን፤ ለጤና ተስማሚ የሆነ ምግብን በመጠን መመገብን የሚማሩበትን፤ እንደ ቡና፣ ሻይ፣ ወይን ጠጅ እና አነቃቂ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ እንዳይጠቀሙ የሚማሩበትን እና የሞቱ እንስሳትን ሥጋ እንዳይጠቀሙ የሚማሩበትን የጤና ተቋም ለመገንባት እንሻለን፡፡ Temperance, pp. 88, 89 (General manuscript, 1896).Amh2SM 283.5
በጣም ተስማሚ የሆነ ሁኔታ፡- መድሃኒቶችን ማከፋፈልን መተው፡- የሰው አካል አሰራርን በእውነተኛ መልኩ ስትረዱት የመድሃኒት ወጪያችሁ እጅግ አነስተኛ ይሆንና በመጨረሻ መድሃኒቶችን ማከፋፈልን ሙሉ በሙሉ ትተዋላችሁ፡፡ በሥራው ውስጥ በመድሃኒት ሕክምና የሚደገፍ ሐኪም አደጋ የማይችለውን የሰብአዊ አካል ፋብሪካ እንደማይገነዘብ ያሳያል፡፡ በአካል ውስጥ በሕይወት ዘመን ሁሉ የአጥፊነት ባሕርዩን በፍጹም የማያጣውን ዘር እያስገባ ነው፡፡ ይህን የምነግራችሁ ዝም ለማለት ስለማልደፍር ነው፡፡ የመድሃኒት ሕክምናን በመስጠት አካልን በጭካኔ መጉዳት እስከማንችል ድረስ ክርስቶስ ለሰው ድነት እጅግ ብዙ ዋጋ ከፍሏል፡፡ Amh2SM 283.6
ከዓመታት በፊት ሕመምተኞችን ያለ መድሃኒት የሚያክሙ ተቋማት መቋቋም እንዳለባቸው ጌታ ገልጾልኛል፡፡ ሰው የእግዚአብሔር ንብረት ስለሆነ በዚህ ሕያው መኖሪያ ላይ የሚደርስ ውድመት፣ በሰው አካል ውስጥ በሚዘሩ የሞት ዘሮች አማካይነት የሚፈጠረው ስቃይ፣ እግዚአብሔርን የሚያበሳጭ ነገር ነው፡፡ Medical Ministry, p.229 (To a leading physician and his wife, 1896).Amh2SM 284.1