Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወጣት ሰው ወጪን እንዲቀንስና እንዲቆጥብ ተመከረ

    በሁሉም ነገር ወጪን እንዳልቀነስክ ግልጽ ነው፤ ወጪን ቀንሰህ ቢሆን ኖሮ ጥበብ ከተሞላበት ቁጠባ የተነሳ አሁን ማንኛውንም ወጣት የሚያስመሰግን የሆነ የሚታይ ነገር ይኖርህ ነበር፡፡ በየሳምንቱ ከምታገኘው ደሞዝህ የተወሰነውን ማስቀመጥና በየሳምንቱ የማይነካ የተወሰነ ገንዘብ መቆጠብ መመሪያህ መሆን አለበት፡፡…..Amh2SM 330.1

    በንግድ ትጋት፣ ደስታን ከመፈለግ መታቀብ፣ ጤናን አደጋ ላይ እስካልጣለ ድረስ መቸገርም ቢሆን፣ በአንተ ሁኔታ ባለ ወጣት በደስታ መደረግ ያለበት ነገር ነው፤ ሕመም ቢያጋጥምህ በሌሎች እርዳታ እንዳትደገፍ የማይነካ ጥቂት ተቀማጭ መኖር አለበት፡፡ አሁን ትርፍ ሊያስገኝልህ የሚችለውን ብዙ ሀብት አለአስፈላጊ በሆነ ሁኔታ አባክነሃል፡፡Amh2SM 330.2

    ከውስን ደሞዝህ እንኳን ቢሆን ለማንኛውም አስገዳጅ ሁኔታ የሚሆን የተቀመጠ ገንዘብ ሊኖርህ ይችል ነበር፡፡ ዋጋው እየጨመረ በሚሄድ ብዙ መሬት ላይ መዋል ይችል ነበር፡፡ ነገር ግን ወጣት ሰው ከሚያገኘው ገቢ የመጨረሻውን ዶላር እስኪጠቀም ድረስ መሄድ ታላቅ ስኬት ማጣትን እና ማስተዋል አለመቻልን ያሳያል፡፡Amh2SM 330.3

    ሟች የሆኑ ሰዎች አስፈላጊ ነገሮችን ማግኘት ያለባቸው አካላት፣ ራሶች እና ልቦች ስላሏቸው በዓለም ውስጥ ተገቢ የሆነ ቦታ ለመያዝ ለአካል የሆነ ነገር መሰጠት አለበት፡፡ ይህ መሆን ያለበት የዓለምን መስፈርቶች ለማሟላት አይደለም፣ በርግጥ አይደለም፤ ነገር ግን በዓለም ውስጥ መልካም ተጽዕኖ ለማሳደር ፍቅር፣ ርህራኄ እና ገርነት ያለበት የጋራ ወንድማማችነት መተግበር አለበት፡፡ Letter 41, 1877.Amh2SM 330.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents