Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 43—ተአምራዊ ፈውስ

    አደጋ ሊያጋጥመው የሚችልበት ሁኔታ

    ለሕሙማን የሚደረግ ጸሎትን በተመለከተ ብዙ የሚያወዛግቡ ሀሳቦች ቀርበዋል፡፡ «ጸሎት የተደረገለት ሰው መድሃኒት ሳይጠቀም ለእግዚአብሔር ክብር እየሰጠ በእምነት መሄድ አለበት» የሚል ሰው አለ፡፡ ይህ ሰው በጤና ተቋም ውስጥ የሚሰራ ከሆነ ተቋሙን በአስቸኳይ ለቆ መውጣት አለበት፡፡ Amh2SM 345.1

    እነዚህ ሀሳቦች ስህተት መሆናቸውን እና ተቀባይነት ካገኙ ወደ ብዙ ክፋቶች እንደሚመሩ አውቃለሁ፡፡Amh2SM 345.2

    በሌላ በኩል በጸሎት ውጤታማነት ላይ እምነት ማጣት እንደሆነ ተደርጎ ትርጉም ሊሰጠው ስለሚችል ምንም ነገር ለማለት አልሻም፡፡Amh2SM 345.3

    የእምነት መንገድ ያለው በእብሪት መንገድ አጠገብ ነው፡፡ ሁልጊዜ ሰይጣን ወደ ስህተት መንገድ ሊመራን ይሻል፡፡ እምነት በውስጡ የሚይዛቸውን ነገሮች በተመለከተ የተሳሳተ መረዳት ግራ እንደሚያጋባና ተስፋ እንደሚያስቆርጥ ያያል፡፡ ወንዶችና ሴቶች ነገሮችን በተሳሳተ አቅጣጫ እንዲመለከቱ ሲያሳምናቸው ይደሰታል፡፡Amh2SM 345.4

    ለሕመምተኞች መጸለይ የምችለው በአንድ መንገድ ብቻ ነው፡- «ጌታ ሆይ ፈቃድህ ከሆነ፣ ለእንተ ክብር የሚያመጣ እና ለሕመምተኛው ደግሞ የሚጠቅም ከሆነ ከስቃዩ እንድትፈውሰው እንጸልያለን፡፡ የእኛ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም፡፡» Amh2SM 345.5

    ነህምያ በጌታ ፊት በማዘን ባለቀሰ እና በጸለየ ጊዜ ሥራው እንደተከናወነለት አድርጎ አልቆጠረም፡፡ ጸሎት ብቻ አልጸለየም፡፡ ተማጽኖንና ጥረትን በመቀላቀል ሰራ፡፡Amh2SM 346.1

    ምክንያታዊ የሆኑ ፈውሶችን ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ መጠቀም እምነትን መካድ አይደለም፡፡ Manuscript 31, 1911.Amh2SM 346.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents