Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከአሳሳች ተጽእኖዎች እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል

    ብዙ ጊዜ ሰይጣን ክፉ ለማድረግ ኃይለኛ ወኪል የሚያገኘው የአንድ ሰው አእምሮ በሌላ ሰው አእምሮ ውስጥ ተጽእኖ ማሳደር በሚችልበት ኃይል ውስጥ ነው፡፡ ይህ ተጽእኖ እጅግ አሳሳች ከመሆኑ የተነሳ በእሱ እየተቀረጸ ያለ ሰው አብዛኛውን ጊዜ ኃይሉን አይገነዘበውም፡፡ ባሪያዎቹ በሰይጣን ማታለያ ሥር እንዳይሆኑ ስለዚህ ክፋት ማስጠንቀቂያ እንድሰጥ እግዚአብሔር አዞኛል፡፡ ጠላት ጎበዝ ሰራተኛ ስለሆነ የእግዚአብሔር ሕዝብ ያለማቋረጥ በእግዚአብሔር መንፈስ ካልተመሩ በስተቀር ሊጠመዱና ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡Amh2SM 352.2

    በሺሆች ለሚቆጠሩ አመታት ሰይጣን በሰብአዊ አእምሮ ባሕርያት ላይ ሙከራ እያደረገ ከመኖሩ የተነሳ እንዴት እንደሚያውቀው በደንብ ተምሯል፡፡ በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ ብልጠት በተሞላበት አሰራሮቹ ሰብዓዊ አእምሮን ከራሱ አእምሮ ጋር እያገናኘ በራሱ ሀሳቦች እየሞላቸው ነው፤ ይህን ሥራ እየሰራ ያለው እጅግ አሳሳች በሆነ መንገድ ስለሆነ የእርሱን አመራር እየተቀበሉ ያሉ ሰዎች በእርሱ ፈቃድ እየተመሩ እንደሆነ አያውቁም፡፡ ታላቁ አሳሳች ከእርሱ ድምፅ በስተቀር የማንም እንዳይሰማ የወንዶችንና የሴቶችን አእምሮዎች ለማወዛገብ ተስፋ ያደርጋል፡፡Amh2SM 352.3

    ክርስቶስ ለጴጥሮስ ከፊቱ ስላለው የፈተናና የሥቃይ ጊዜያቶች በገለጠለት ጊዜ ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ «አይሁን ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይድረስብህ” (ማቴ. 16፡ 22)፡፡ ያኔ አዳኙ እንዲህ በማለት ገሰጸው፣ «አንተ ሰይጣን ወደ ኋላዬ ሂድ» (ማቴ. 16፡ 23)፡፡ የፈታኙን ሚና እንዲጫወት ሰይጣን በጴጥሮስ አማካይነት እየተናገረ ነበር፡፡ ሰይጣን በዚያ ቦታ እንደሚገኝ ጴጥሮስ ባይጠራጠርም የአታላዩን በዚያ ቦታ መኖር ለይቶ ማወቅ ስላልቻለ ክርስቶስ ጴጥሮስን በገሰጸው ጊዜ እየተናገረ የነበረው ለትክክለኛው ጠላት ነበር፡፡Amh2SM 353.1

    በአንድ አጋጣሚ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ እየተናገረ እና ወደ ይሁዳ እያመለከተ እንዲህ አለ፣ «ከእናንተ አንዱ ሰይጣን ነው» (ዮሐ. 6፡ 70)፡፡ ብዙ ጊዜ አዳኙ በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ጠላቱን የተጋፈጠው በሰብአዊ መልክ፣ ሰይጣን እንደ እርኩስ መንፈስ ሰዎችን ሲቆጣጠራቸው ነበር፡፡ ሰይጣን ዛሬም የሰዎችን አእምሮዎች ይቆጣጠራል፡፡ የእግዚአብሔርን ሥራ እየሰራሁ ሳለሁ በተደጋጋሚ በክፉ የተያዙ ሰዎችን ያገኘሁ ሲሆን ክፉ መንፈስን በጌታ ስም ገስጫለሁ፡፡ Amh2SM 353.2

    ሰይጣን ሰብአዊ አእምሮን የሚቆጣጠረው በኃይል አይደለም፡፡ ሰዎች ተኝተው ሳሉ ጠላት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንክርዳድ ይዘራል፡፡ ጠላት የኃጢአት ሥራውን የሚሰራው ሰዎች በመንፈሳዊ እንቅልፍ ውስጥ ሳሉ ነው፡፡ በልብ ውስጥ የተዘራውን መልካም ዘር በእርሱ ቁጥጥር ሥር ካሉት የሚለቅመው «ሳያስተውሉት» ነው (ማቴ. 13፡ 19)፡፡ ወንዶችና ሴቶች በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሳሉ፣ መንፈሳዊ ሕይወታቸው ያለማቋረጥ በእግዚአብሔር መንፈስ በማይመገብበት ጊዜ፣ ሰይጣን የራሱን መንፈስ ሊሞላባቸው ይችላል፤ የእሱን ሥራ እንዲሰሩ ሊመራቸውም ይችላል፡፡…Amh2SM 353.3

    እግዚአብሔር ማረጋገጫ የማይሰጠው እያንዳንዱ ተግባር ከሕይወታችን እንዲወገድ እማጸናለሁ፡፡ ወደ ምድር ታሪክ መዝጊያ እየተቃረብን ነን፤ በየቀኑ ጦርነቱ የበለጠውን እየከረረ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ Letter 244, 1907.Amh2SM 353.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents