Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    የገጠር ቦታዎች መጠጊያ

    ነፍሳትን በማዳን ተግባር ውስጥ ልጆቻቸውን ማሰልጠን ጠቃሚ ሥራ መሆኑን ወላጆች ይገንዘቡ፡፡ በገጠር ቦታዎች መሰራት ያለባቸውን ሥራዎች በመስራት ነርቭንና ጡንቻን የሚያሳድጉና የአካል ጤናን የሚሰጡ ብዙ፣ ጠቃሚ እንቅስቃሴዎች ይገኛሉ፡፡ መልእክቴ ልጆቻችንን ለማስተማር «ከከተማ ውጡ» የሚል ነው፡፡Amh2SM 355.2

    እግዚአብሔር ለመጀመሪያ ወላጆቻችን መሬትን እንዲያርሱና የአትክልት ቦታን እንዲንከባከቡ መመሪያ በሰጣቸው ጊዜ የእውነተኛ ትምህርትን መንገድ ሰጣቸው፡፡ የእግዚአብሔርን መስፈርቶች ባለመታዘዝ ኃጢአት ከገባ በኋላ ምድር በኃጢአት ምክንያት ከመረገምዋ የተነሣ አረምና አሜካላ ስላበቀለች መሬትን በማረስ የሚሰራ ሥራ እጅግ በዛ፡፡ መሬትን የማረስ ሥራን ታላቁ መምህር ራሱ ባርኮታል፡፡Amh2SM 355.3

    ወንዶችንና ሴቶችን ወደ ከተማ መሳብና ሰይጣን የሚፈለስፋቸውን አዳዲስ ነገሮች እና መዝናኛዎች፣ እያንዳንዱን ዓይነት ስሜት እንዲያገኙ ማድረግ የሰይጣን ዓላማው ነው፡፡ ዛሬ በምድር ላይ ያሉት ከተማዎች ከውኃ ጥፋት በፊት እንደነበሩት ከተማዎች እየሆኑ ናቸው፡፡…Amh2SM 355.4

    ማስጠንቀቂያ የሚሰጣቸው እነማን ናቸው? እንደገና «ከከተማዎች ውጡ» እንላለን፡፡ ወደ ኮረብታዎችና ተራራዎች መሄድን እንደ ትልቅ እጦት አድርጋችሁ አትመልከቱ፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድና መንገድ ለመማር ከእርሱ ጋር ለብቻችሁ የምትሆኑበትን ያንን መለየት ፈልጉ፡፡…Amh2SM 355.5

    ሕዝባችን መንፈሳዊነትን መፈለግን የሕይወታቸው ሥራ እንዲያደርጉ አደፋፍራቸዋለሁ፡፡ ክርስቶስ በደጅ ነው፡፡ «ከተማዎችን ለቃችሁ ወደ ገጠራማ ቦታዎች እንድትሄዱ መጠራታችሁን ለሕይወት አስፈላጊ የሆነ ነገርን እንደመነፈግ አድርጋችሁ አትመልከቱ፡፡ ለሚቀበሉት በዚህ ቦታ ብዙ በረከቶች ይጠብቋቸዋል፡፡ የተፈጥሮ ቦታዎችን፣ የፈጣሪን ሥራዎች በመመልከት፣ የእግዚአብሔርን የእጅ ሥራ በማጥናት፣ በማይታይ ሁኔታ ወደዚያ ምሳሌ ትለወጣላችሁ” የምልበት ምክንያት ይህ ነው፡፡ Manuscript 85, 1904.Amh2SM 356.1